Connect with us

Business

በአዲስ አበባ ጉድለት የተገኘባቸው 19 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ

FanaBC

Published

on

በአዲስ አበባ ጉድለት የተገኘባቸው 19 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ

በአዲስ አበባ በቂ የማለማመጃ ተሽከርካሪዎች ካለማቅረብ ጀምሮ ሌሎች ጉድለቶች የተገኙባቸው 19 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ።

በሀገሪቱ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች መካከል 80 በመቶው በአሽከርካሪዎች የብቃት ማነስ ምክንያት የሚከሰት መሆኑን የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ለችግሩ የማሰልጠኛ ተቋማቱ ብቃት ማነስ ምንጭ ሲሆን፥ በቂ የማለማመጃ ተሽከርካሪ ማቅረብ አለመቻልን ጨምሮ ትምህርት ላልወሰደ ተለማማጅ በገንዘብ መንጃ ፈቃድ እስከ መስጠት የደረሰ ህገ ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ ስለመኖራቸው ሰልጣኞች ያነሳሉ።

በአዲስ አበባ 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን፥ የአዲስ አበባ አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣንም ባደረገው ግምገማ ጉድለቶች ማግኘቱን ገልጿል።

በድንገተኛ ፍተሻ እና በየሁለት አመቱ ከሚካሄደው ግምገማ በተገኘው ውጤትም መሰረት ከ66ቱ ተቋማት መካከል 19 እንዲዘጉ መደረጉን፥ የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ፉፋ ተናግረዋል።

በጊዜያዊነት አሽከርካሪዎችን ከማሰልጠን ከታገዱት 19 ተቋማት መካከል አስራ አምስቱ ለሁለት ወራት ቀሪዎቹ አራት ተቋማት ደግሞ ለሶስት ወራት አገልግሎት እንዳይሰጡ ተወስኗል።

ተቋማቱ እንዲህ አይነት እርምጃ የተወሰደባቸው ከማሰልጠኛ ተሸከርካሪ አቅርቦት ጀምሮ ሌሎች በርካታ ጉድለቶች ስለተኙባቸው መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።

በጊዜያዊነት እንዲዘጉ የተወሰነባቸው ተቋማት የተቀመጠውን መስፈርት ማሟላታቸው እስከሚረጋገጥ እና የተወሰነባቸው የቅጣት ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ምንም አይነት ስልጠና መስጠትም ሆነ አዲስ ሰልጣኞችን መቀበል አይችሉም።

ተቋማቱ በእጃቸው ያለውን ሰልጣኞች ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላም እንደ ቅጣታቸው መጠን ለሁለት እና ሶስት ወራት ይዘጋሉም ነው ያሉት።

በጊዜያዊነት እንዲዘጉ ከተደረጉት ተቋማት በተጨማሪም ለ34 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የመጀመሪያ እና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ከ34ቱ ተቋማት ውስጥም ሰባቱ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው 27ቱ ደግሞ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ነው የተሰጣቸው።

READ  ከቡና የወጪ ንግድ ቅሌት ጋር በተያያዘ በወንጀል የተጠረጠሩ ላኪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ባለስልጣኑ በዙር ካደረጋቸው ግምገማዎች በተጨማሪም ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን መነሻ በማድረግ እና ተቋማቱ ላይም ክትትል በማድረግ፥ 47 ያህል ሰልጣኞችን ህጋዊ ባልሆነ መልኩ እና ስልጠናቸውን ሳያጠናቅቁ ለፈተና ሊያስቀምጡ የሞከሩ ሶስት ተቋማት ላይም እርምጃ ወስዷል።

በዚህም ኬቢ ቁጥር ሶሰት 40 ሰልጣኝ፣ ይሄነው ማስተዋል 2 ሰልጣኝ እንዲሁም ፎርዊል 5 ሰልጣኞችን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሊያስፈትኑ ሲሉ ተይዘው ላልተወሰነ ጊዜ አንዲዘጉ ተደርጓል።

በዙር ግምገማውም ሆነ በተጨማሪ ክትትል እርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት በተሰጣቸው ደብዳቤ መሰረት፥ የተገኘባቸውን ክፍተት እስከተሰጣቸው ወር ድረስ ካስተካከሉ ወደ ስራቸው የሚመለሱ ሲሆን ማስተካከል ባልቻሉት ላይ ግን እርምጃው የሚቀጥል ይሆናል።

ኤፍ ቢ ሲ

Continue Reading

Africa

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን ተገለጸ

Published

on

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት በቴክኒክ ደረጃ በሶስትዮሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ውይይት ወቅት ያልተቋጩ ጉዳዮች ዙሪያ በሶስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመግባባት መንፈስ ላይ የተመሰረተ ገንቢ ውይይት ተደርጎ በስኬት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም በተመለከተ ካላት በጋራ ተጠቃሚነት፣ ፍትሐዊነት፣ምክንያታዊነት እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች በመነሳት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ አገራት ጋር ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

እንደ አቶ መለስ ገለጻ የሶስቱ አገራት የውሃ ሚ/ሮች ቀጣይ ውይይታቸውን በቅርቡ በሚገለጽ ጊዜና ቦታ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን ትናንት (ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም.) የተደረገው ውይይት በበለጠ መግባባትና በግልጽ ወንድማማችነት መንፈስ የተካሄደ ነበር።

የሶስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ጋባዥነት ያደረጉት ጉብኝት ታሪካዊ እንደሆነም አቶ መለስ ተናግረዋል።

ለዚህም ማሳያዎቹ በአገሮቹ መካከል ግልጽነትና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር እድል መፍጠሩ፣ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ መሬት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማየት ማስቻሉ፣ ከጉብኝቱ በኋላ ከግድቡ የቴክኒክ ጉዳዮች አንጻር ሚኒስትሮቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በፕሬጀክቱ ጽ/ቤት በኩል የተሰጠውን አርኪ ማብራሪያ መጥቀስ ይቻላል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ ይህንን ጉብኝት በማዘጋጀቷ አመስግነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶቹ በኩል በ 2009 በጀት ዓመት አራት ነጥብ ዘጠኝ ስምንት (4.98) ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቦንድ ሸጧል፡፡ ከፍተኛው ተሳትፎ የተገኘውከመካከለኛ ምስራቅ ነው። በ2010 ዓ.ም የበጀት ዓመት አምስት ነጥብ አንድ (5.1)ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ታቅዷል፡፡

የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተሟሟቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አትዮጵያውያን በግድብ ግንባታ በገንዘብ የማይተመን የአርበኝነት መንፈስ እየተረባረቡ ናቸው።

READ  የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት

ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብጽና ሱዳን ጋር በወንድማማችነት መንፈስ ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች፣ ይህም ትብብር ብቸኛው አማራጭ ነው ብላ ስለምታምን ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 09 ቀን 2010 ዓ.ም.

 

Continue Reading

Business

ኒቪያ አዲስ የውበት መጠበቂያ ምርቱን በሸራተን አዲስ አስተዋወቀ

Published

on

ኒቪያ አዲስ የውበት መጠበቂያ ምርቱን በሸራተን አዲስ አስተዋወቀ

አዲስ ኒቪያ ንትፕሮቴክት ኤንድ ኬር ዲዮዶራ

ሰውነትን ካላስፈላጊ የላብ ጠረን የሚጠብቅ እና ለቆዳ ተስማሚ ሆኖ የተዘጋጀው አዲስ ፕሮቴክት ኤንድ ኬር የተሰኘ የኒቪያ ዲዮድራንት በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ይህ አዲሱ ዲዮድራንት ከኒቪያ ምርቶች በልዩ ሁኔታ ከሚወደደው የኒቪያ የሰውነት ክሬም ግብኣቶች በመጠቀም የተዘጋጀ ሲሆን የራሱን ልዩ ማዓዛም እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ አዲሱ የኒቪያ ዲዮድራንት ሰውነትን ለ48 ሰዓት ካላስፈላጊ የሰውነት ጠረን የሚጠብቁ እና ለሰውነት ቆዳ ተስማሚ የሆኑ ግብዓቶችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡

አንዳንድ ዲዮድራንቶች ካላስፈላጊ የሰውነት ጠረን የሚከላከሉ ወይም የሰውነት ቆዳ ላይ ጉዳት የማያደርሱ ብቻ ሆነው ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡ በአሁን ወቅት ሴቶች ካላስፋጊ የሰውነት ጠረን የሚጠብቃቸው እንዲሁም በብብታቸው ቆዳ ላይ ጉዳት የማያስከትል ዲዮድራንት መጠቀምን ይሻሉ፡፡ ብብት በምላጭ፣ በሙቀት ወይም ጠባብ የሆኑ አልባሳትን በማዘውተር በሚፈጠር ወበቅ ከሌላው ሰውነታችን በተለየ ሁኔታ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል፡፡

በተጨማሪም በተደጋጋሚ በሚደርስበት ጉዳት መጥቆር እና የቆዳ ቀለም መቀየር ሊከሰት ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ለብብት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅብን፡፡ ይህም ሆኖ አላስፈላጊ የሰውነት ጠረንን፣ የሰውነት ማሳከከን እና የቆዳ መቆጣትን በመፍራት ብቻ ዲዮድራንትን መጠቀም ማቆም አማራጭ አይሆንም፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች ሁሌም ካጠገባችን እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤ ለዚህም ነው ሰውነትን ካላስፈላጊ የሰውነት ጠረን የሚጠብቅ እና የሰውነት ቆዳ ላይ ጉዳት የማያደርስ አዲሱ ኒቪያ ዲዮድራንት ትክክለኛ አማራጭ የሚሆነው፡፡

25 ዓመታትን ባስቆጠረ የዲዮድራንት አሰራር ልምድ ባላቸው ጠበብቶቹ በመታገዝ ኒቪያ የሰውነታችንን ቆዳ በተገቢ ሁኔታ የሚንከባከብ እና እንዲሁም 48 ሰዓት ከአላስፈላጊ ጠረን የሚጠብቅ ዲዮድራንት ለተጠቃሚዎች ያቀረበ ሲሆን ልዩ በሆኑ የኒቪያ ክሬም ግብአቶች ሰውነትን ከጉዳት የሚጠብቅ እና ልዩ ግሩም መዓዛ የሚያጎናፅፍ ነው፡፡

READ  አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ | ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት

ኒቪያ ፕሮቴክት ኤንድ ኬር ዲዮድራንት ተጠቃሚዎች በኒቪያ ክሬም የሚያውቁትን ለሰውነት ተስማማሚነት በዚህም ዲዮድራንት ላይ የሚያገኙ ሲሆን ይህም ማለት ኒቪያ ክሬም የሚሰጠንን የመታደስ ስሜት፣ የሰውነት ጥራት፣ እና እንክብካቤ ጥቅሞች በተመሳሳይ ሁኔታ በአዲሱ የኒቪያ ዲዮድራንቶች ላይ እናገኛቸዋለን፡፡ አዲሱ የኒቪያ ዲዮድራንት ከሎሚ እና ግሩም መዓዛ ካለው ባርግሞት ከተሰኘ ፍሬ የተዘጋጀ ሲሆን ለተጠቃሚዎች በራስ የመተማመን ስሜትን ከመታደስ ስሜት ጋር ይሰጣል፡፡ የሰውነት ቆዳን ልስላሴ እና ጤንነት ለመጠበቅ ሮዝ አበባ እና የኦሊቭ ዝርያ ያለው ጃዝሚን የተሰኘ የአበባ አይነት ከሌሎች የእፅዋት ዘሮች በግብዓትነት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ዘጠኝ እንስቶች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከዘጠኙ እንስቶች ስምንቱ ከተቻ የተዘረዘሩትን ስለ አዲሱ የኒቪያ ዲዮድራንት ይህን አረጋግጠዋል፡-

  • ልዩ በሆነው መዓዛ እና በውስጡ በያዘው የኒቪያ ክሬም ግብኣቶች የሰውነት ቆዳ ጤንነት እና ውበትን ጠብቆ ለ48 ሰዓት በአግባቡ ከአላስፈላጊ የሰውነት ጠረን ይከላከላል፡፡
  • ምንም አይነት የአልኮል ግብኣት እና ሰውነትን የማቃጠል ባህሪ የሌለው በተለይ ለብብት ቆዳ ተስማሚ ነው፡፡
  • በሰውነት ላይ የሚገኝን ላብ በቶሎ በመምመጥ የደረቅ ሰውነት ስሜት የሚያጎናፅፍ
  • በሰውነት ላይ እርጥበት የማይተው

ኒቪያ ፕሮትክት ኤንድ ኬር ዲዮድራንት

 

  • ልዩ በሆነው መዓዛ እና በውስጡ በያዘው የኒቪያ ክሬም ግብኣቶች የሰውነት ቆዳ ጤንነት እና ውበትን ጠብቆ ለ48 ሰዓት በአግባቡ ከአላስፈላጊ የሰውነት ጠረን ይከላከላል፡፡
  • ምንም አይነት የአልኮል ግብኣት እና ሰውነትን የማቃጠል ባህሪ የሌለው በተለይ ለብብት ቆዳ ተስማሚ ነው፡፡
  • በልዩ ሁኔታ በተመረጡ ግብአቶች አማካኝነት ለሰውነት ተስማሚ ሆኖ የተሰራ
  • የሰውነትን ልስላሴ በመጠበቅ እና ምቾት ባለው ሁኔታ ሰውነትን በተስማሚ ሁኔታ በማድረቅ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ንፁህ የመሆን ስሜትን ይሰጣል፡፡
  • በመድኃኒት ቅመማ መስፈርት ለሰውነት ቆዳ ተስማሚ መሆኑ የተረጋገጥ
READ  ድርቅ በደቡብ ኦሞ ዞን

 

በሮል እና በስፕሬ መልክ ለወንድም ለሴትም የተዘጋጀ ሲሆን ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ኮስሞቲክስ መሸጫዎች እና ሱፐርማርኬቶች በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

DIRETUBE

Continue Reading

Business

የስኳር እጥረት ለማቃለል ከውጭ የተሸመተው ስኳር ጅቡቲ ወደብ ደርሷል ተባለ

Published

on

በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የስኳር እጥረት ለማቃለል ከውጭ የተሸመተው ስኳር ጅቡቲ ወደብ ደርሷል ተባለ

በዚህ ሣምንት ስኳሩን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝም ጨረታውን ካሸነፉ ሁለት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር መስማማቱን የስኳር ኮርፖሬሽን ለሸገር ተናግሯል፡፡

ካለፈው ሚያዚያ ወር 2009 ዓ.ም በኋላ በተለያየ ምክንያት እንደውጥኔ ስኳር ማምረት አልቻልኩም ያለው ኮፖሬሽኑ ከነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ የስኳር አቅርቦት ችግር አጋጥሞኛል ብሏል፡፡

የአቅርቦት ችግሩን ለማቃለልም ከዓለም ገበያ 700 ሺ ኩንታል ስኳር ለመሸመት ጨረታ ወጥቶ እንደnበር ይታወሣል፡፡

ከአልጄሪያ የተሸመተው 366 ሺ ኩንታል ስኳርም ከትናንት በስቲያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ስኳሩን ወደ መሐል ሀገር ለማጓጓዝም ጨረታውን ያሸነፉ ሁለት የማጓጓዣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተሰናድተዋልም ብለዋል፡፡

ከ700 ሺ ኩንታል ስኳሩ ቀሪው ከታይላንድ የተሸመተው 334 ሺ ኩንታል ስኳር በባህር ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ መጀመሩንም ሰምተናል፡፡

በተያያዘም በኬንያ ተልኮ በሞያሌ ጠረፍ ረዘም ላለ ጊዜ የቆየው 44 ሺ ኩንታል ስኳር ተጓጉዞ ሙሉ በሙሉ ወደ ወንጂ መድረሱንም ሰምተናል፡፡

ስኳሩ ለምግብነት እንደሚውልና እንደማይውልም ፍተሻ እየተደረገለት መሆኑን አቶ ጋሻው ነግረውናል፡፡

ስኳሩ መንገድ ላይ ባሳለፈው ዘለግ ያለ ጊዜ እንዳልተበላሸ ከተረጋገጠም ለህብረተሰቡ እንደሚከፋፈል ከአቶ ጋሻው ሰምተናል፡፡

ባለፈው ዓመት የግንቦት ወር የስኳር ኮርፖሬሽን ለኬንያ 100 ሺ ኩንታል ስኳር ለመላክ ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ 44 ሺ ኩንታል ስኳር ተጭኖ ወደ ኬንያ መንገድ ከጀመረ በኋላ በተፈጠረ አለመግባባት ከ50 ቀናት በላይ ፀሐይና ወበቅ ሲፈራረቅበት ቆይቶ መመለሱ ይታወሣል፡፡

READ  ድርቅ በደቡብ ኦሞ ዞን
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close