በትግራይ ክልል አሸንዳን እንደ አንድ የጎብኚ መስህብ የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

0
በትግራይ ክልል አሸንዳን እንደ አንድ የጎብኚ መስህብ የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
በዘንድሮው የአሸንዳ በዓል ላይ ከ60 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሰሜናዊቷ ኮከብ ይታደማሉ፡፡

በዘንድሮው የአሸንዳ በዓል ላይ ከ60 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሰሜናዊቷ ኮከብ ይታደማሉ፡፡

በትግራይ ክልል በየዓመቱ ከሚከበሩ ባህላዊና መንፈሳዊ ኩነቶች አንዱ የአሸንዳ በዓል ነው፡፡ በዓሉ በብዙ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ቢከበርም በመቐለ የሚከናወነው ሥርዓት ግን ግዙፉ የልጃገረዶች ኩነት እየሆነ መጥቷል፡፡

የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት የአሸንዳን በዓል በክልሉ እንደሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች ሁሉ ተናፋቂ የመስህብ ሀብት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

ባለፉት ተከታታይ አምስት ዓመታትም ለኩነቱ ትኩረት ተሰጥቶ እንደ አንድ የፌስቲቫል ቱሪዝም መዳረሻነት እየለማ ነው፡፡ ዘንድሮም በተመሳሳይ መልኩ የ2009 ዓ.ም. የአሸንዳ በዓልን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ለማካሄድ ዝግጅቱ ማለቁን ነው ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው መረጃ የሚያስረዳው፡፡

በዓሉን ለመታደምም አንጋፋ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ሚዲያዎች ሰሜናዊቷ ኮከብ መቐለ ይከትማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እስከአሁን በአለው መረጃ ከ60 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የ2009 ዓ.ም. የአሸንዳን በዓል በመቐለ ከተማ በመታደም ይዘግቡታል፡፡

ለጋዜጠኞቹ በመቐለ እና አካባቢዋ እንዲሁም በተወሰኑ የትግራይ አካባቢዎች የቤተሰባዊ ትውውቅ ጉዞ መርሐ ግብርም እንደተዘጋጀ ነው ያገኘነው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን እንደ ፍቼ ጨምበላላ፣ መስቀልና ገዳ ሥርዓት ሁሉ በስሜን ኢትዮጵያ የሚከበሩትን የአሸንዳ፣ ሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የመሳሰሉ ተመሳሳይ የጋራ እሴቶች በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የጥናት ስራውን እየሰራ እንደሚገኝ ባለፈው ዓመት ተገልጾ ነበር፡፡ DIRETUBE

 

READ  ብሔራዊ የጋራና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ

NO COMMENTS