ምላሽ (Replay) – በያሬድ ነጋሽ

0
ምላሽ (Replay
ኡሁን ላይ ምን አክለህ ይሆን ? ምን አይነትስ ሰው ሆነህ ይሆን ? ለሚለው የሎዛ አስተያየት (comment) የተመለሰ ምላሽ (Replay)….

ምላሽ (Replay) | በያሬድ ነጋሽ@DireTube

ኡሁን ላይ ምን አክለህ ይሆን ? ምን አይነትስ ሰው ሆነህ ይሆን ? ለሚለው የሎዛ አስተያየት (comment) የተመለሰ ምላሽ (Replay)….
ምላሽ (Replay)
ሎዛ የልጅነት ጊዜ ምስሌ ከህሊናሽ ሊጠፋ ትንንሽ ትውስታ ብቻ እንደቀሩሽ አስተያየትሽ ነግሮኛል፡፡ እኔም ግን በተመሰሳይ ትላንት በሚያስታውስ መልኩ ዛሬዎችሽን ባያቸው ደስተኛ ነኝ ፡፡ በአስተያየትሽ ከጠየቅሽኝ ጥያቄ ጋር ይለያይ ወይንም አይለያይ ባላውቅም አንድ ነገር ላጫውትሽ ወደድኩ ፡፡

ምን መሰለሽ አሁን ላይ ምን አይነት ገጽታ እንዳለኝ በተለያዩ መንገዶች ፎቶዬን ልኬ እንድታይኝ ላደርግ እችል ነበር፡፡እንደውም አሁን ላይ እንደሚደረገው ከሄድኩበት የውጪ ሀገር ፣ ካለሁት መዝናኛ ስፍራ ፣ ካገኘኋቸው አለም አቀፍ ዝነኛ ሰዎች ጋር ወይንም ካለሁበት መልካም ከሚመስሉ የሂወቴ ገጽታ ላይ ሆኜ የተነሳሁትን ፎቶ ፌስ ቦክ ላይ ፖስት ባደርገው አንቺን ጨምሮ ለብዙዎች መገለጥ ይቻለኛ ነበር፡፡እንዲህ እንዳላደርግ ግን ጽኑ ምክንያት አለኝ፡፡

ሎዛ ልክ ከከፍተኛ ተቋም ትምህርቴን ጨርሼ እንደተመረኩ ቢያንስ ለ2 አመታት ያክል ስራ አላገኘሁም ነበር፡፡ በወቅቱ ስራ እንዳልያዝኩ ከሚያስታውሱኝ ነገሮች መካከል ፌስ ቡክ ዋነኛው ነበር፡፡ እንዴት መሰለሽ …….በዛን ወቅት አብረውኝ አንድ ዶርም ተምረን የተመረቅን ልጆች ያሉበትን የህይወት ገጽታ አንዴ ከሮም ፣አንዴ ከፍራንስ ፣ አንዴ ከዩኤስ ሆነው የተነሱት ፎቶ ፖስት በማድረግ በሚገልጹ ጊዜ ያኔ ታዲያ ብዙም ያልበሰለው አይምሮዬ ዋናው ነገር ከጤንነት እና ከማይናወጽ ሰላም ጋር የትም ቦታ ላይ መኖር እንደሆነ ሳይረዳ ጓደኞቼ ሁሉ ጥለውኝ እንደከነፉ በግድ ሊያሳምነኝ ይሞግተኝ ነበር፡፡ ለካ ደረስንበት ብለን በፌስ ቡክ ፖስት በምናደርገው ፎቶ በአንድ ወቅት አብረውን ተመሳሳይ ቦታ ላይ የነበሩና አሁን ግን ኑሮው የተጫናቸውን ወዳጆቻችንን ሳያስቡት የስነ ልቦና ጫና ሊያድርባቸው ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡ከዛ በኋላ ያን ያህል ወዳጆቼን ሊያስጎመጅ በሚችል የተጋነነ የኑሮ ደረጃ ላይ ባልኖርም እንኳን ፎቶ ፖስት ማድረግን ተውኩ፡፡

READ  በላሊበላ በአስጎብኚነት ይሰራ የነበረው ኢትዮጵያዊ ከብሪታኒያ የቀድሞ የማራቶን ሯጭ ጋር በመጣመር በእንግሊዝ የቱሪስት ስራ ድርጅት አቋቋመ ሲል ትራቭል ሞል ዘገበ

ሎዛ አንቺ ያለሽበት ሰሜን አሜሪካ ኑሮው ግላዊ ስለሆነና ማንም የማንንም ነገር ስለማይተያይ ደረስንበት ብለን በፌስ ቡክ ፖስት የምናደርገው ፎቶ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ነግር ግን እንደ ኢትዩጵያ ኑሮው ማህበረሰባዊ በሆነበት እና ጎረቤት ለጎረቤት ያላቸውን ለውጥ በጥሞና በሚተያይበት ሀገር ግን ስልቦናዊ ጫናው ይበዛል፡፡ ስለዚህ በፌስ ቡክ ላይ የደረስንበትን የሀብት ደረጃ ፣የረገጥነውን የመዝናኛ ስፍራ ፣ ያገባናትን ቆንጆ ሚስት ፖስት ለማድረግ ከምንጠቀምበት ይልቅ የደረስንበትን የሃሳብ ደረጃ የትኛውንም ሰው ሊጠቅም በሚችል መልኩ ካለንበት ሆነን ፖስት ብናደርግ መልካም ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

የልጅነት ትውስታሽ ጨርሶ ከመጥፋቱ በፊት ግን አሁን ላይ ምን እንደምመስል ፎቶዬን inbox አደርግልሻለው፡፡
ሰላም!! DIRETUBE

NO COMMENTS