የሙስና ተጠርጣሪዎች የፍ/ቤት ውሎና ቀጠሮዎች

0
የሙስና ተጠርጣሪዎች የፍ/ቤት ውሎና ቀጠሮዎች
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ባለሀብቶች ጉዳያቸው በስምንት መዝገቦች በፍ/ቤት መታየት መጀመሩን ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ ጠቆመ።

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ባለሀብቶች ጉዳያቸው በስምንት መዝገቦች በፍ/ቤት መታየት መጀመሩን ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ ጠቆመ።

ከሐምሌ 22/2ዐዐ9 ዓ.ም. ጀምሮ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት በተለያየ የመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ቁጥር 54 መድረሱ ይታወቃል፡፡

ከአሁን በፊት ተጠርጣሪዎቹ በፌ.ከ.ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው እንዲታይ /እንዲመረመር/ በተደረገው መሠረት የፌዴራል ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ለፍርድ ቤት በጠየቀው መሠረት ፍ/ቤትም የጉዳዮን ከባድነትና ውስብስብነት በመረዳት የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ ለነሐሴ ዐ3/2ዐዐ9 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ከትላንትና በስቲያ ነሐሴ 3 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. 45 ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት ቀርበው የ22 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በርካታ የችሎት ታዳሚዎች በተገኙበት ከታየ /ከተሰማ/ በኋላ ጉዳዩ በዕለቱ ባለመጠናቀቁ የቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች በማግስቱ ዐ4 ነሐሴ 2ዐዐ9 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የተጠርጣሪ ቤተሰቦችና ሌሎች በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ፖሊስ የተጠረጠሩበትን ፍሬ ነገር ለተከበረው ፍ/ቤት አሠምቷል፡፡ ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ምን ምን እንደተሰራም ዝርዝር ሪፖርቱን ለክቡር ፍ/ቤቱ አሰምቷል፡፡

በዚሁ መሠረት የተጠርጣሪዎቹ መዝገብ እንደ የተጠረጠሩበት ሁኔታ በ8 የተለያዩ መዝገቦች የተያዘ ሲሆን ፡-
1. በእነ አቶ ሙሳ ሙሃመድ 13 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 15/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
2. በእነ አቶ አብዱ መሃመድ መዝገብ 8 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 15/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
3. በእነ አቶ አበበ ተስፋዬ መዝገብ 6 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 17/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
4. በእነ አቶ ኤፍሬም ደሳለኝ መዝገብ ዐ2 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 17/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
5. በእነ ኢንጅነር ፈቃደ ኃይሌ መዝገብ ዐ3 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 17/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
6. በእነ ወ/ሮ ፀዳለ ኃይሌ ማሞ መዝገብ ዐ2 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 8/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
7. በእነ አቶ መስፍን መልካሙ መዝገብ ዐ6 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ለነሐሴ 17/2ዐዐ9 ዓ.ም. እንዲታይ የፍ/ቤት ቀጠሮ መያዙ፣
8. በእነ አቶ ዘነበ ይማም ለነሀሴ 17/2009 ዓ.ም እንዲታይ ፍ/ቤቱ ቀጠሮ የያዘ ሲሆን በአቶ አስናቀ ምህረት መዝገብ ጉዳይ በቀጣይ ቀጠሮ የሚታይ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ጠቁሟል፡፡

READ  972 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

በወቅቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች
– ተከላካይ ጠበቆች የጊዜ ቀጠሮ አያስፈልግም ሲሉ ለክቡር ለፍ/ቤት ማሰማታቸው
– ተከላካይ ጠበቆች ለደንበኞቻቸው የዋስትና መብት እንዲፈቀድ ለክቡር ፍ/ቤቱ መጠየቃቸው
– ፍርድ ቤቱ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ጉዳዮ ከባድና ውስብስብ በመሆኑና የህዝብና የመንግስት ጥቅም ያለበት ጉዳይ

በመሆኑ የዋስትና መብት አለመፍቀዱ እና ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ
– በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎች “በቁጥጥር ስር ከዋልንበት ጊዜ አንሰቶ እስካሁን ከጠበቆች እና ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዳንገናኝ ተከልክለናል” በማለት ለፍ/ቤት አቤቱታ ቢያቀርቡም ፖሊስ “ሀሰት መሆኑን እና ከጠበቃም ከቤተሰብም ጋር እየተገናኙ መሆኑን ገልጿል፡፡

– ፍ/ቤቱም አለመከልከላቸው እውነት መሆኑን በቀጣይ ቀጠሮ ፖሊስ ማስረጃ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑ፣
– ሚዲያዎች ከፍረጃና ከስሜት የፀዳ ዘገባ እንዲዘግቡ ክቡር ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ
– የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ ቤተሰቦቻቸውና በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የተሰማ /የታየ/ መሆኑ ይታወቃል። DIRETUBE

NO COMMENTS