Connect with us

Ethiopia

“በባቢሌና ሐረር አካባቢዎች ግጭት አልተቀሰቀሰም ፤ መንገድም አልተዘጋም”- ዶክተር ነገሪ ሌንጮ

Published

on

"በባቢሌና ሐረር አካባቢዎች ግጭት አልተቀሰቀሰም ፤ መንገድም አልተዘጋም"

The U.S. Embassy in Ethiopia said it is aware of reports that the main road from Addis Ababa to Jijiga has been blocked by security forces between the cities of Babile and Harar due to intense fighting including gunfire.

It added Ethiopian Defense Force troops are arriving in the area, and the road is not passable.

=

የአሜሪካ ኤምባሲ “ከአዲስ አበባ ጅግጅጋ መስመር በባቢሌ እና ሐረር አካባቢዎች ግጭት ተከስቶ መንገድ ተዘግቷል ፤ መንቀሳቀስ አይቻልም” ብሎ ያወጣው መረጃ ሐሰት መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት እንደገለጹት፤ በተጠቀሱት አካባቢዎች የተቀሰቀሰ ግጭት የለም።

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በአንድ ወቅት በአካባቢው ተከስቶ የነበረውን ችግር ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች አስተዳደሮች መፈራረማቸውን አውስተው፤ በተወሰነ ወራት ውስጥም የወሰን ማካለሉን ሥራ ለማከናወን መስማማታቸውን አስታውሰዋል።

“ይህንን መሠረት በማድረግ የወሰን ማካለሉ ሥራ እየተከናወነ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ከፌዴራል እና ከሁለቱ ክልሎች የተወጣጡ ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ይሄንኑ ሥራ የሚሠሩ ባለሙያዎች ሥራ ላይ እያሉ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝ አትሰሩም በሚል ከለከሏቸዋል፤ እነርሱም ትተው ሄዱ እንጂ ምንም ዓይነት ተኩስ እና ግጭት አልተቀሰቀሰም” ብለዋል።

አሁን ባለው መረጃም አካባቢው ሠለማዊ እንደሆነና ምንም ዓይነት የተቀሰቀሰ ግጭትም ተኩስም እንደሌለ፤ መንገድም እንዳልተዘጋ ዶክተር ነገሪ አብራርተዋል።

በመሆኑም የአሜሪካ ኤምባሲ በድረገጹ የለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ተናግረዋል። ena

=

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ በባቢሌ እና ሀረር ከተሞች መካከል ያለው መንገድ እንደተዘጋ እና በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ ለዜጎቹ ገልፆ ከቦታው እንዲርቁ ዛሬ አሳስቧል።

READ  ካናቢስ ዕፅ ይዞ የተገኘ አንድ ግለሰብ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተቀጣ

Continue Reading

Ethiopia

ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

Published

on

ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

ሰማያዊ ፓርቲ ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ።

ፓርቲው ስብሰባውን የሚያካሂደው ጥቅምት 19 ቀን 2010 በአዲስአበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የመብራት ሀይል አዳራሽ ነው። ፓርቲው በእለቱ ከቀትር በሀላ በጠራው ስብሰባ ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊገኝ እንደሚችል ጥሪ አስተላልፎአል።

ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ በመስቀል አደባባይ ሊጠራ አቅዶ የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ቦታው ባለመፈቀዱ መስተጎአጎሉ ይታወሳል።

DIRETUBE

READ  ካናቢስ ዕፅ ይዞ የተገኘ አንድ ግለሰብ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተቀጣ
Continue Reading

Africa

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን ተገለጸ

Published

on

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት በቴክኒክ ደረጃ በሶስትዮሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ውይይት ወቅት ያልተቋጩ ጉዳዮች ዙሪያ በሶስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመግባባት መንፈስ ላይ የተመሰረተ ገንቢ ውይይት ተደርጎ በስኬት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም በተመለከተ ካላት በጋራ ተጠቃሚነት፣ ፍትሐዊነት፣ምክንያታዊነት እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች በመነሳት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ አገራት ጋር ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

እንደ አቶ መለስ ገለጻ የሶስቱ አገራት የውሃ ሚ/ሮች ቀጣይ ውይይታቸውን በቅርቡ በሚገለጽ ጊዜና ቦታ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን ትናንት (ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም.) የተደረገው ውይይት በበለጠ መግባባትና በግልጽ ወንድማማችነት መንፈስ የተካሄደ ነበር።

የሶስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ጋባዥነት ያደረጉት ጉብኝት ታሪካዊ እንደሆነም አቶ መለስ ተናግረዋል።

ለዚህም ማሳያዎቹ በአገሮቹ መካከል ግልጽነትና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር እድል መፍጠሩ፣ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ መሬት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማየት ማስቻሉ፣ ከጉብኝቱ በኋላ ከግድቡ የቴክኒክ ጉዳዮች አንጻር ሚኒስትሮቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በፕሬጀክቱ ጽ/ቤት በኩል የተሰጠውን አርኪ ማብራሪያ መጥቀስ ይቻላል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ ይህንን ጉብኝት በማዘጋጀቷ አመስግነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶቹ በኩል በ 2009 በጀት ዓመት አራት ነጥብ ዘጠኝ ስምንት (4.98) ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቦንድ ሸጧል፡፡ ከፍተኛው ተሳትፎ የተገኘውከመካከለኛ ምስራቅ ነው። በ2010 ዓ.ም የበጀት ዓመት አምስት ነጥብ አንድ (5.1)ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ታቅዷል፡፡

የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተሟሟቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አትዮጵያውያን በግድብ ግንባታ በገንዘብ የማይተመን የአርበኝነት መንፈስ እየተረባረቡ ናቸው።

READ  አንጋፋው የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ማዕከል የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አልሙኒ ዛሬ ይመሰረታል

ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብጽና ሱዳን ጋር በወንድማማችነት መንፈስ ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች፣ ይህም ትብብር ብቸኛው አማራጭ ነው ብላ ስለምታምን ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 09 ቀን 2010 ዓ.ም.

 

Continue Reading

Ethiopia

የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅና ባለቤት ጋዜጣውን ለመዝጋት እንደወሰነ ተናገረ

Elias Tesfaye

Published

on

አውራምባ ታይምስ

የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅና ባለቤት የሆነው ዳዊት ከበደ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጋዜጣውን ለመዝጋት እንደወሰነ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ተናግሯል።

አውራምባ ታይምስ ድረገጽ በቅርቡ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶች (ምሁራን፣ የትግራይ ብሄርተኝነት አራማጆች፣ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች) ናቸው ያላቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲያወታይ መቆየቱ ይታወሳል። የድረገፁ መዘጋት እየተደረገ ካለው ውይይት ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው የታወቀ ነገር የለም።

የአቶ ዳዊት ከበደ መግለጫ ይህን ይመስላል።

እ.ኤ.አ ከሜይ 2012 ጀምሮ ላለፉት አምስት አመታት በአገራችን ፖሊቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በቻለው አቅም መረጃ ሲያቀርብላችሁ የነበረውን ድረገጻችን (www.awrambatimes.com) በተለያዩ (እዚህ በማንገልጻቸው) ፈታኝ ነገሮች ምክንያት ከፊታችን እሁድ ኦክቶበር 22, 2017 ጀምሮ ለመዝጋት የምንገደድ መሆኑን እየገለጽን፣ እስካሁን ስንሰጥ በነበረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከጎናችን በመሆን ጠቃሚ ሀሳቦችን በማዋጣት የሞራል ስንቅ ለሆናችሁን በአገር ውስጥና በውጭ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለወደፊትም አቅማችን በፈቀደ መጠን (ከግል ህይወታችን በሚተርፈን ጊዜ) ቴክኖሎጂው በፈጠረልን ነጻ የማህበራዊ ሚዲያ “ፕላትፎርም” (Facebook፣ Youtube እና Twitter) አማካኝነት ለአገራችን ሰላም እድገትና ብልጽግና ይጠቅማል የምንለውን ሀሳብ ማራመዳችንን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን።

ከሰላምታ ጋር
ዳዊት ከበደ
አዘጋጅ

 

READ  አንጋፋው የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ማዕከል የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አልሙኒ ዛሬ ይመሰረታል
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close