የአቶ ሀብተሥላሴ ግብዐተ መሬት እሁድ ይፈጸማል

0
የአቶ ሀብተሥላሴ ግብዐተ መሬት እሁድ ይፈጸማል
በስማቸው ፓርክ ቢሰየምላቸው ሙዝየምም ቢገነባላቸው ለክብሩ ይመጥናሉ። የሀገራችንን ቱሪዝም ከምንም ጀንረውና ትልቅ ድርጅት አቋቁመው ለዓለም ያሳወቁ ጀግና እንደማንም "ዐረፉ" ተብሎ ብቻ ሊሸኙ ነው።

tየኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት አቶሀብተሥላሴ ታፈሰ የቀብር ሥነሥርዓት የፉታችን እሁድ እንደሚከናወን ኢ.ፌ.ዲ.ሪ የባህልና ቱሪዝምሚኒስቴር አስታወቀ። አቶ ሀብተሥላሴ ታመው የህክምናክትትል ሲያርጉ ቆይተው በ96 ዓመታቸው ትላንት ረቡዕ ነሀሴ 03/2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል፡፡

የእኚህን ታላቅ የአገር ባለውለታ የቀብር ሥነ-ሥርዓት እሁድ ነሀሴ 07/2009 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የሚከናወን መሆኑን ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጻል።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት ጋሽ ሀብተሥላሴ ታፈሰ ዐረፉ።

ኢትዮጵያ ያላትን ቱባ ባህልና አስደናቂ የቱሪዝም ሀብት ለዓለም ዓይንና ጆሮ ለማድረስ ጃንሆይን አሳምነውና አስፈቅደው “የኢትዮጵያ የቱሪዝም ኮሚሽንን” በማቋቋምና ሀገራችን ከዓለም ልዩ የምትሆንበትን “የ13 ወር ፀጋ – 13 Months of Sunshine” ምስል በመቅረጽ ምትክ “የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት” የሚል መጠሪያን ያገኙት ታላቁ ሰው ጋሽ ሀብተሥላሴ በ90 ዓመታቸው ዐረፉ። በሠሩላት ልክ ሀገራቸው ውለታቸውን ሳትከፍላቸው… እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በልዩ ሀብቶቿ ሊያስተዋውቋት እንደደከሙላት ተሰናበቷት።

እስከማውቀው ድረስ ለእኝህ ታላቅ ሰው “ከምስክር ወረቀት ያለፈ” ክብር አልተሰጣቸውም። እንደወጉ ቢሆን በቱሪዝን ዘርፉ ላበረከቱት አልባ ሚና ሀውልት ይገባቸዋል።

በስማቸው ፓርክ ቢሰየምላቸው ሙዝየምም ቢገነባላቸው ለክብሩ ይመጥናሉ። የሀገራችንን ቱሪዝም ከምንም ጀንረውና ትልቅ ድርጅት አቋቁመው ለዓለም ያሳወቁ ጀግና እንደማንም “ዐረፉ” ተብሎ ብቻ ሊሸኙ ነው።

.
…ነፍስ ይማር…

DIRETUBE

READ  በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የቀረበው ክስ እንዲሻሻል ብይን ተሰጠ

NO COMMENTS