Connect with us

Sport

ከስፖርት ማዕድ- ትኩስ የዝውውር ወሬዎች

Juliana

Published

on

ከስፖርት ማዕድ

1- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለኦክስሌድ ቻምበርሊን ዝውውር 35 ሚሊየን ፓውንድ መመደቡ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ይህም ተጫዋቹ ያወጣል ተብሎ ከተገመተው  ዋጋ በላይ ነው፡፡ የ23 ዓመቱ ቻምበርሊን 63 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ክፍያ የሚያገኝ ሲሆን ወደ 120 ሺ እንዲያድግለትም ይፈልጋል፡፡ቀሪ የ1 ዓመት ኮንትራት ከሚቀረው እንግሊዛዊ ተጫዋች ጋር ድርድር የጀመረው አርሰናል ከቼልሲ የቀረበውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ግን ችላ ይለዋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

2- የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የዝውውሩ መስኮት ሳይዘጋ አንድ ተጫማሪ ተጫዋች ማስፈረም እንደደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ የቶትንሀሙ ግራ ተመላላሽ ተጫዋች ዳኒ ሮስ ወይንም የኢንተር ሚላኑ ክንፈኛ ኢቫን ፐርሲች ወደ ኦልድትራፎርድ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡ ዳኒ ሮስ በበኩሉ ስፐርስን የመልቀቅ ፍላጎት ባይኖረውም ከታላላቅ ክለቦች የሚሰነዘሩ የዝውውር ጥያቄዎችን እንደሚያጤናቸው ገልጧል፡፡

3- ፒኤስጂ የሞናኮውን የ18 ዓመት ወጣት ተጫዋች ኬይላን ምባፔ ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱን የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡የአወዛጋቢውን የኔይማር ዝውውር በ200 ሚሊየን ፓውንድ የጠቀለለው የፈረንሳዩ ክለብ የምባፔን ዝውውር በ180 ሚሊየን ዩሮ ለማገባደድ ምንም የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለለ የከዚህ በፊት እንቅስቃሴያቸው ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ሪያል ማድሪድና ማንቸስተር ሲቲ የ18 ዓመቱ ድንቅ ፈረንሳዊ ተጫዋች ፈላጊ ክለቦች መሆናቸው ይታወቃል፡፡የኳታር ባለሀብቶቹ የፒኤስጂ ባለቤቶች በዝውውር መስኮቱ እያፈሰሱት ያለው የገንዘብ መጠን መነጋገሪያ አድርገጓቸዋል፡፡

4- የአርሰናሉ ቺሊያዊ አጥቂ አሌክሲ ሳንቼዝ የመጀመሪያዎቹ የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት አርሰን ቬንገር አስታውቀዋል፡፡ ሆኖም ግን ሁኔታው ከዝውውር ጉዳይ ጋር የተያያዘ አንዳች ጉዳይ እንደሌለው የገለፁት ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ሳንቼዝ በመድፈኞቹ ቤት እንደሚቆይ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ እንደ ዴይሊሜይል ዘገባ አልክሲ ተጨማሪ ኮንትራት በሚቀጥለው ዓመት በገንዘብ ለመዘዋወር ይረዳው ዘንድ ለመፈረም መዘጋጀቱን አስነብቧል፡፡

5- ባርሴሎናዎች ለ25 ዓመቱ ፊሊፕ ኩቲንሆ ዝውውር ለሶስተኛ ጊዜ የገንዘብ መጠን በመጨመር ያቀረቡት ጥያቄ በመርሲሳይዱ ክለብ ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡ የካታሎኑ ክለብ ለተጫዋቹ ዝውውር 72 እና 80 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ አቅርቦ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ 90 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳቡን አሳድጎ ለድርድር በር ቢያንኳኳም  ቀና ምላሽ ግን ከሊቨርፑሎች ሊያገኝ አልቻለም፡፡ሊቨርፑሎች ኩቲንሆን ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ሲሆን የባርሴሎና ተደጋጋሚ ጥያቄ ግን ስጋት ደቅኖባቸዋል፡፡ ኩቲንሆ የቅዳሜው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በጀርባ ጉዳት ምክንያት እንደሚያመልጠው ታውቋል፡፡

6- ማንቸስተር ዩናይትዶች ከሲውዲናዊው የ 35 ዓመት አጥቂ ዝላታን ኢብርሀሞቪች ጋር ኮንትራቱን በማራዘሙ ዙሪያ ንግግር ጀምሯል፡፡ኢብራ እስከ ግማሽ የውድድሩ ዓመት ድረስ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ የሚታወቅ ሲሆን 9 ቁጥር ማሊያንም አዲሱ ፈራሚ ሮሜሎ ሉካኩ እንዲለብሰው ፍቃድ ሰጥቶታል፡፡ጆሴ ሞሪንሆም ዝላታን አዲስ ኮንትራት ባይፈርምም አሁንም የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

7- ባርሴሎናዎች ብራዚላዊው ኔይማርን ካጡት በኋላ የሱን ተተኪ ተጫዋች በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ፡፡ለዚህም የቦርሲያ ዶርትሞንዱን ኦስማን ደምበሌን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የጀርመኑ ክለብ ግን ባርሳዎች 135 ሚሊየን ፓውንድ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ በካታሎኑ ክለብ ደምበሌን ለማዘዋወር የቀረበው 90 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ ውድቅ የተደረገ ሲሆን ድርድሩ ግን አሁንም በጀርመን እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡የ20 ዓመቱን ደምበሌን ቦርስያ ዶርትሞንድ ባለፈው ዓመት ከ15 ሚሊየን ፓውንድ ባነሰ ሂሳብ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close