ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጠቃት | በቁሙ ለሞት እንጂ በስራው ሕያው ለሆነ አይለቀስም

0
ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጠቃት፡፡
የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት እና የአስራ ሦስት ወር ጸጋ መለዮ ስያሜ ፈጣሪ የሆኑት ሀብተ ስላሴ ታፈሰ ሞተዋል፡፡ ተጓዡ ጋዜጠኛና የቱሪዝም ዘጋቢው ሄኖክ ስዩም ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጠቃት ይለናል፡፡

ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጠቃት፡፡ በቁሙ ለሞት እንጂ በስራው ሕያው ለሆነ አይለቀስም፡፡

የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት እና የአስራ ሦስት ወር ጸጋ መለዮ ስያሜ ፈጣሪ የሆኑት ሀብተ ስላሴ ታፈሰ ሞተዋል፡፡ ተጓዡ ጋዜጠኛና የቱሪዝም ዘጋቢው ሄኖክ ስዩም ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጠቃት ይለናል፡፡) ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዮብ

ማልቀስስ ለራሳችን ሚሊዮን ሆነን የአንድ ሰውን ያኽል ላልመዘነው፤ በአርግጥ ኢትዮጵያ የቱሪዝም አባቷን ሞት ነጥቋታል፡፡
እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ለራሳችሁ አልቅሱ እንዳለው ማልቀስ ያለብን ግን ለእኛ ነው፡፡ እንዴት በቁሙ የሞተ እያለ በስራው ሕያው ለሆነ ይለቀሳል፡፡

ዛሬ አሰብሁ፤ ያ የቢኒ አመር ሳቂታ ፎቶ ህላዌ ቢኖረው ፊቱ በጨፈገገ፤ ፊታችንን የምንነጨው ለራሳችን ነው፡፡ እንደውም የተገላገልነው ከሚያሸማቅቀን ሰው ነው፡፡

አንድ ሆኖ አንድ ሀገርን ከዓለም ጋር ለማስተዋወቅ ወጣትነቱን የሰጠ፤ እርጅናንም ትዝታን በመተረክ ከመኖር ስለ ኢትዮጵያ እና ራስን ስለማሸነፍ ድል ያደረገ ሰው ብዙ ሆነን ያቃተን እኛ መሀል መኖሩ በእርግጥም ያሸማቅቃል፡፡

ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው አለ ዘፋኙ፡፡ ደጋጉ ቢኖር ለእኛ ነበር፡፡ ጎበዝ እድሜ በቃህ አይባልም፡፡ ሊያውም ሳይወለድ በሚሞት ተስፋ ቢስ ትውልድ መካከል፡፡ በርትተናል፡፡

የቀደሙት አንድ ሆነው የሰሩትን እኛ በኮሚቴ መስራት አቅቶን ይኽው በኮሚቴ መቅበር ጀምረናል፡፡ አይ ዘመን፡፡ ሀብተ ስላሴ ታፈሰ የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት ናቸው፡፡ አባት የሚለው ቃል ከቀለለ፡፡

በልዑል ራስ መንገሻ ባለ ራዕይነት በሀብተ ስላሴ ታፈሰ ወላጅነት ኢትዮጵያና ቱሪዝም ተዋወቁ፡፡ አንድ ሰው ወጣትነቱን ሰጠ፡፡ አንድ ሰው ጉልምስናውን ቸረ፡፡ አንድ ሰው እርጅናውን ለገሠ፡፡ እንዲህ ያለ ታሪክ ያለው ሰው ሞተ አይባልም፡፡

READ  በኦሮሚያ የሚገኙ ግዙፍ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርቶቻቸውን የክልሉ ወጣቶች እንዲያከፋፍሉ ተስማሙ ተባለ

መቅበርስ የራስን ዳተኝነት፤ መቅበርስ በየነገሩ የተሸነፍንበትን ምክንያት፤ እንጂማ እንዴት ህያው ታሪክ ላለው ታላቅ ሰው ለቀብር እንጠራራለን፡፡ ሦስት ቀን ከርሰ መቃብር ለማያድር መልካም ስም፤ መቃብር ፈንቅሎ ለሚወጣ ታላቅ ስራ፤ ጉድጓድ ምሶ ሀብተ ስላሴን ቀበርሁ ማለት አይቻልም፡፡

ግድግዳዎቻችን ላይ ያሉት ውብ ምስሎች፣ መስከረም ሲጠባ የአስራ ሦስት ወር ጸጋ ብሎ በትዝታ ጅራፍ የሚዠልጠን የጥላሁን ገሰሰ ዜማ፤ ኢትዮጵያ እና ቱሪዝም ከምንለው ስም ጋር ተገደን አብረን የምናስበው ሰው ሞተ አልልም፡፡ ህያው ስራ ቆሞ ከሚንገላወድ የሰነፍ ህላዌ ይልቅ አብራ ትኖራለችና፡፡ DIRETUBE

NO COMMENTS