ችሎቱ የ22 የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ተመለከተ

0
ችሎቱ የ22 የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ተመለከተ
ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ባለሃብቶችና ደላሎች መካከል ጉዳያቸውን ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የ22 የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ጉዳይን ተመለከተ።

ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ባለሃብቶችና ደላሎች መካከል ጉዳያቸውን ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ትናንት ማለትም ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዝርዝር ጉዳይ እንዲታይ ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው 42 ተጠርጣሪዎች በልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

ነገር ግን ከቀረቡት መካከል ጉዳያቸው በሶስት መዝገቦች ስር የተጠቃለሉ 22 ተጠርጣሪዎችን ብቻ ተመልክቷል።

ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀው ፖሊስ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ ዝርዝር የምርመራ ውጤት እንዲያቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም፤ፖሊስ ጉዳዩ ከአዲስ አበባ ውጭና ውጭ አገር ድረስ ስለተዘረጋ አሁንም ያላጠናቀቀው ምርመራ እንዳለው ገልጿል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ግለሰብ ላይ የተጣራ መረጃ አለማቅረቡን ተቃውመዋል።

ደንበኞቻቸውም የዋስትና መብት ተሰጥቷቸው ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ችሎቱን ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ ችሎቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም ከሁለት ቀናት በፊት አንድ ቀን ብቻ መገናኘት እንደቻሉ ገልጸዋል።

ፖሊስ በበኩሉ ማረሚያ ቤቱ ጠበቆችና ቤተሰብ ለመጠየቅ የራሱ ህገ ደንብ እንዳለው ገልጾ፤ በዚህም መሰረት ጠበቆች በተፈቀደላቸው ሰዓት አለመከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ መልስ ሰጥቷል።

ፖሊስ ያጣራቸው መረጃዎችንና ተጨማሪ ምስክሮችን ማግኘቱን ጠቁሞ ተጠርጣሪዎቹ የሰነድ ማስረጃዎች ይሰውራሉ በሚል ዝርዝር የምርመራ ውጤቱን ከመግለጽ ተቆጥቧል።

ቀሪ የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን ለማጠናቀቅም ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ችሎቱን ጠይቋል።

ችሎቱም የቀሪ ተጠረጣሪዎችን ጉዳይ ከተመለከተ በኋላ በዛሬ ዕለት የተጨማሪ የምርምራ ጊዜ ፈቃድም ሆነና የዋስትና ጥያቄው ውሳኔውን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

READ  President Appeals to Public’s Help in Construction of Dialysis Centre

በአንደኛ መዝገብ ስር ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች መካከል አቶ ሙሳ መሃመድ፣መስፍን ወርቅነህ፣ዋሲሁን አባተ የቀረቡ ሲሆን በመዝገብ ሁለት የቀረቡት ደግሞ መስፍን መልካሙ፣ብርጋዴር ጀኔራል ኤፍሬምና ሚ/ር ጁ ዩኪን ናቸው።

ጉዳያቸው በሶስተኛ መዝገብ ከተካተቱት መካከል አቶ እንዳልካቸው ግርማ፣ ወይዘሮ ሰናይት ወርቁና አቶ በለጠ ዘለለው ይገኙበታል። ena

NO COMMENTS