Connect with us

Sport

ከስፖርት ማዕድ- ትኩስ የዝውውር ወሬዎች

Juliana

Published

on

ከስፖርት ማዕድ

1- የፊሊፕ ኩቲንሆ ጉዳይ አሁንም መሰራታዊና ተጨባጭ የሆነ መግባባት ላይ እስካሁን ሊደርስ አልቻለም፡፡ ባርሴሎናዎች አሁንም የኔይማርን ተተኪ በአማራጭ ተጫዋቾች ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የ25 ዓመቱ ኩቲንሆ ደግሞ ቀዳሚ በካታሎኑ ክለብ ራዳር ውስጥ የገባ ተጫዋች ነው፡፡ ኩቲንሆም ወደ ባርሳ ለመጓዝ ፍላጎት ቢኖረውም ቀዮቹ ግን በፍጹም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በድጋሚ ብራዚላዊው የአጥቂ አማካኝ ድንቅ ተጫዋች ፊሊፕ ኩቲንሆ ለማንኛውም ክለብ በየትኛውም ዋጋ እንደማይሸጥ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም የዝውውር መስኮቱ እንደ ኔይማር ሁላ በኩቲንሆ ጉዳይ አዲስ ወሬ ሊያሰማን ይችላል፡፡

2- የቀድሞው የአርሰናል ድንቅ አጥቂ አለን ራይት የአርሰን ቬንገር ቡድን ትልቁ ችግሩ መሪ የሆነ ተጫዋች ማጣቱ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትዶች ኒማኒያ ማቲችን 40 ሚሊየን ፓውንድ አውጥተው ማስፈረማቸው ለመድፈኞቹ ትልቅ ትምህርት ሊሆናቸው ይገባል ብሏል፡፡ የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች አስተያየቱን በመቀጠልም አርሰን ቬንገር ከተኙበት በመንቃት ቡድኑን ሊመራ የሚችል ተጫዋች ሊያስፈርሙ እንደሚገባ በመጠቀስ ለዚህ ደግሞ እንደ ቫንዳይክ ዓይነት ተጫዋች ትክክለኛ ምርጫ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡አለን ራይት በ ፋይቭ ላይቭ ስፖርት አስተያየቱን በሚሰጥበት ወቅት እልህና ቁጭት በተቀላቀለበት ስሜት እነደነበር ለማስተዋል ተችሏል፡፡

3- ቴሪ ሄነሪ ጋሬዝ ቤል ሪያል ማድሪድን የሚለቅ ከሆነ ለሱ ትክክለኛ ማረፊያው ሊሆን የሚገባው ማንቸስተር ዩናይትድ እንደሆነ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ጆሴ ሞሪንሆም ዌልሳዊውን ወደ ኦልድ ትራፎርድ የሚያስመጡት ከሆነ ከከፍተኛ ሞገድ እንደታደጉት ይቆጠራል ብሏል፡፡ ሄነሪ ቤልን የገለፀበት መንገድ ’’ ጋሬዝ ቤል እንደ እኔ በየትኛውም ሊግ መጫወት የሚችልና በቡድን ውስጥ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ተጫዋች ነው፡፡ በበርናባው የጎደለው ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡ሆኖም ግን ይህ የተጫዋቹ ጉድለት (ቤልን ማለቱ ነው) ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቢቀላቀል ያለምንም ጥርጥር ይቀረፋል፡፡ እርግጠኛ ነኝ ሞሪንሆም የቤል ፈላጊ አሰልጣኝ ናቸው፡፡’’

4- ሆላንዳዊው ተከላካይ ቫንዳይክ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ መጫወት ስለሚፈልግ  ሳውዝአምፕተኖች እንዲለቁት ሲወተውት ቆይቷል፡፡ በአሁን ሰዓት ደግሞ በዓይምሮ በኩል ዝግጁ አይደለሁም በሚል ከክለቡ ጋር ልምምድ ማድረግ ያቋረጠ ሲሆን ይህም በሴይንት ሜሪው ክለብ መማረሩን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ የሊቨርፑል ታማኝ ደጋፊዎች የተጫዋቹን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሲሆን ወደ አንፊልደ ሮድ እንዲመጣም ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት አሳድረዋል፡፡ይህን ሁኔጣ በመረዳት ይመስላል ሊቨርፑልም የቫንዳይክን የዝውውር ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት 60 ሚሊየን ፓውንድ መድቧል፡፡60 ሚሊየን ፓውንድ + የቫንዳይክ ወደ ቀዮቹ የመሄድ ፍላጎት = የሳውዝአምፕተኖች የእሺታ መልስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

5- የፒኤስጂ ተጫዋች ሰርጌ ኦሪየር የፈረንሳዩን ክለብ እንደሚለቅ በይፋ ከታወቀ በኋላ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን በዝውውሩ ላይ ቼልሲዎች የተጫዋቹ ፈላጊ ክለብ ሆነው ብቅ ብለዋል፡፡ 27 ሚሊየን ፓውንድ የተለጠፈበት ኮትዲቯራዊ ተጫዋች አሁን ባለው ሁኔታ ወደ እንግሊዝ መግባት በፍርድ ቤት ዕግድ ምክንያት የማይችል በመሆኑ ኦሪየርን አስፈራሚ የሚሆን የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ በይግባኝ ውሳኔውን ማስቀልበስ ይኖርበታል፡፡ ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦችም ማለትም ቼልሲ እና ዩናይትድ ይህን ሀላፊነት በመውሰድ ተጫዋቹን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሁንም በሮሜሉ ሉካኩ ጉዳይ ዩናይትዶችን ለመበቀል ቀዳዳ እያፈላለጉ ይመስላሉ፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close