Connect with us

Ethiopia

በኢትዮጵያ ቡድን ውስጥ ወርቅነሽ ኪዳኔን ፍለጋ

Published

on

በኢትዮጵያ ቡድን ውስጥ ወርቅነሽ ኪዳኔን ፍለጋ

በኢትዮጵያ ቡድን ውስጥ ወርቅነሽ ኪዳኔን ፍለጋ | ታደለ አሰፋ ከለንደን

ወርቅነሽ ኪዳኔ ለእኔ የቡድን ስራ ተምሳሌት ነች ከራሷ በላይ የቡድን ውጤት የሚያስደስታት ታሪካዊ አትሌት፣ አሁን ግን ያዘመን በብዙ መልኩ አልፋል እርሷ በጉዳት እና ወሊድ ምክንያት እንደፈለገችው ብዙ ሳትጓዝ ቀርታለች፣ በሜዳ ላይ ለቡድን ስራ ሲሉ እራሳቸውን መስዋእት የሚያደርጉ አትሌቶች አይደለም አብረው ውሃ የሚጠጡና የሚበሉ በፈገግታ እንደ አንድ ቡድን የሚተያዩ አትሌቶችን አጥተን ቆይተናል፡፡

በአንድ ጀምበር አንድነታችንን እንዳለጣነው ሁሉ በአንድ ጀምበርም አንድነታችንን አንመልሰውም ከቡድን ስራ በፊት እንደ አንድ ቡድን መነጋገር ይቀድማልና፣ ባለሙያዎቹ አትሌቲክስ የግል ክህሎት ላይ የተመሰረተ ስፖርት እንደ ሆነ ይናገራሉ እውነታውም እርሱ ነው፣ በሀይሌ ፍጥነት የልምምድ ሁኔታ ቀነኒሳን ሩጥ ማለት በቀነኒሳ ፍጥነት እና ልምምድ ታምራት ቶላን ስራ ማለት ስፖርቱን ያለመረዳት ችግር የሚፈጥው ነው፡፡

አትሌቶች የቡድን ስራ ውስጥ ለመሳተፍ በቅድሚያ እርስ በእርስ ማን ምን አይነት ብቃት አለው የሚለውን ሊተዋወቁ ይገባል ማን ምን አይነት ልምምድ እንደ ሰራ በማይታወቅበት ማን አንዱን ዙር በስንት ሲሄድ እንደ ነበር በማይታወቅበት የቡድን ስራ ከሚዲያ ወሬ ባለፈ ለመተግበር አስቸጋሪ ነው፡፡

ከዛ ውጭ ሁሉም አትሌቶች በተመሳሳይ የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ነው፣ ከሁሉም በላይ እራሳቸውን መስዋእት አድርገው ሌላው እንዲሸንፍ ለማድረግ ወርቅነሽ ኪዳኔ አሊያም አሰፋ መዝገቡ መሆን ሲቻል ፡፡

አሁን ግን ዘመኑ ተቀይሮአል ሁሉም አሸናፊ ስለ መሆን ነው የሚያልመው አንተ ዙሩን አክርለት እርሱ ፍጥነት ስላለው የመጨረሻውን ዙር አፈትልኮ ይውጣ ያለፈበት የስልጠና ዘዴ ሆኖአል፣ እንደ አልማዝ አያና የመጨረሻውን ዙር አፈትልከው መውጣት የማይችሉ አትሌቶች ከመጀመሪው ዙር ጀምሮ አፍጥኖ በመሄድ ተወዳዳሪን ከቻሉ ደርቦ ማስወጣት የቡድን ስራን በትራክ ላይ ጊዜ አልፎብካል ብሎታል፡፡

ለዛም ነው አሰልጣኝ ቶሎሳ ቆቱ በ10 ሺህ ሴቶች “ሁላችሁም የየራሳችሁን የምትችሉትን ሩጡ ስትጨርሱ ግን ማንም ያሸንፍ ማን ባንዲራ ይዛችሁ ተቃቀፉ” የምትል እውነታ ላይ የተመሰረተች ምክር ጣል ሲያደርጉ የተሰሙት፡፡

ሮም በአንድ ቀን አልተገነባችምና አንድነትም በአንድ ለሊት እና በአንድ መግለጫ አይመጣም ግን ከሜዳ ላይ የቡድን ስራ በፊት የቡድን አንድነት ስሜት ይቀድማል፣ ይህን ጅምር ደግሞ በጋራ ከመመገብ እስከ በጋራ ውድድር ከማየት ይጀመራል ዘንድሮ የተሻለ ነገር አይቻለሁ በተለይ የቡድን አባላቱ የወንዶች ማራቶን በጋራ ተሰብስበው ውድድሩን በቴሌቪዝን ሲመለከቱ( ፎቶግራፍ ከስር አለ) ለካ እኛ ኢትዮጵያውያን የሚስተባብረን ካገኘን አንድነትን እንመርጣለን አስብሎኛል፡፡

አሁንም ግን ከቡድኑ ጋር የማይቀላቀሉ የራሳቸውን ውድድር ለማድረግ ብቻ የመጡ ስለ ሌሎች ውጤት የማይሰሙና ከቡድን አባላቶቻቸው ጋር ሰውነት እያሟሟቁ እንኳን ሰላምታ የማይለዋወጡ እንዳሉ ታዝባለሁ፣ ታዲያ ከቡድን ስራ በፊት የቡድኑ አንድነት ላይ መስራት አይቀድም ትላላች፡፡

ማራቶን በለንደን…. 35ተኛ ኪሎ ሜትርን የማለፍ ችግር ከወትሮው በተለየ መልኩ መዞሪያ የበዛበት የዘንድሮው ውድድር በአንድ ስፍራ ላይ አራት ጊዜ መመላለስን ጠይቆዋል፣ በተለይ የመዞሪያው ስፍራ ጠባብ መሆን ውድድሩን ፈታኝ አድርጎታል፣ በወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ የቀኝ የውስጥ እግሩ ደም በመቋጠሩ ሩጫውን ለማቋረጥ ተገዳል፣ ፀጋዬ መኮንን አስራ ዘጠነኛ ወጥቶአል፣ በጥሩ አቋም ላይ የነበረው ታምራት ቶላ የእግር ህመም እና የታክቲክ ስህተት ወርቅ አሳጥተውታል፡፡

በ10ሺህ ለመሮጥ ፍላጎቱ የነበረው ታምራት ፌዴሬሽኑም ያቀረበለትን ጥያቄ ቢቀበልም የእግር ህመሙ ግን የትራክ መሮጫ ጫማ ስፓይክ (ከስሩ እሾክ የመሰሉ ጥርሶች ያሉት ጫማ ነው) ሲያደረግ ስለሚነሳበት በሀኪም ትእዛዝ የማራቶን ጫማው ተጨማሪ እግር መደገፊ እንዲገባለት ተደርጎ ሮጦአል፡፡

ታምራት ወደ 30ኛው ኪሎሜትር ድረስ ኬንዊውን ጄፌሪ ኪሪዊ ጋር እየተፈራረቁ መምራት ቢችሉም ኬንውያኑ ፍጥነቱን ቀንሶ የተቆረጡ የቡድን ጓደኞቹን ሊቀላቅልብኝ ነው ብሎ በማሰብ ፍጥነቱን ጨምሮ ሲወጣ የግራ እግሩ ጉዳት በመቀስቀሱ ቀሪውን ዙር ከነጉዳቱ ለመሮጥ ተገዳል፡፡

አሰልጣኞቹ ግን የታምራትን ፈጥኖ መውጣት ለወርቅ ሜዳሊያ ማጣት እንደ ምክንያት ቀጥረውታል፣ ታምራት እስከ መጨረሻው ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮ ቢሄድ ኖሮ የ10 ሺህ ሩዋጭ ስለሆነ ኬንያዊው አትሌት እርሱን የሚያቆም ጉልበት አይኖረውም ሲሉ አስቴየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ማራቶን ቡድናችን የጋራ ዝግጅት አላደረገም፣ ከአራት የተለያዩ የስልጠና ማእከላት ነው የመጣው፡፡ በተለይ በሴቶች ቡድን ሁሉም በየስልጠና ማእከላቸው በፍጥነት ላይ የተመሰረተ ልምምድ ላደረጉ አትሌቶች ውድድሩ ፍጥነት ሲቀንስ የእግር መዛላ ያመጣል ፍጥነትን ጨምሮ ለመጓዝ ግን ከአራት ስልጠና ማእከል ለመጡ አትሌቶች መነጋገር ቢችሉ የውድድሩ ፍጥነት በጋራ በዚህ ኪሎሜትር ይህን ያህል ፍጥነት ላይ አድርገን ይዘነው ብንሄድ በዚህ ያህል ቢፈጥኑብን እኛ ደግሞ በዚህ ያህል ብንቀንሰው ከሰራነው እና ካለን የግል ብቃት አንጻር ተብሎ የአራቱም የስልጠና ማእከላት አሰልጣኞች እንኳን ቢያወሩ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በተቻለ ነበር፡፡

ሹሬ ደምሴ አምስተኛ ማሬ ዲባባ ስምንተኛ ብርሀን ዲባባ አስረኛ አሰለፈች መርጊያ አስራ ሁለተኛ ወጥተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የስልጠና ዘዴያችን እንዴት ከ35 ኪሎ ሜትር በሁዋላ ማለፍ ያስችለናል የሚለው ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው፡፡ DIRETUBE

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close