ሰይፉ ፋንታሁን መመስገን አለበት!

0

ሰይፉ ፋንታሁን መመስገን አለበት!
(ሚካኤል አስጨናቂ ፥ በድሬ ቲዩብ )

ሰላም ተወዳጆች እንደምን ሰንብታችኋል? መቼም የዘንድሮ ሰው ወዳጁ ሲጠፋ ወዴት ገብቶ ይሆን ብሎ እንኳ አይፈልግም?! ምፅ!
የሆነውም ሆኖ መተናል !

በሰሞኑ አንድ አባታችን በሞት ከዚህ ዓለም መለየታቸውን ተከትሎ በእጅጉ አዝነን የነበረ ቢሆንም ፥ ታሪክ ሰርተውና ትውልድ አንፀው ያለፉ አባታችን በአካል ቢለዩንም ባቆዩልን መልካም ስራዎች ግን ሁሌም ከጎናችን እንዳሉ ስለሚሰማን ተፅናንተናል!

አዎን አባባ ተስፋዬ ማለት ፥ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ ብቅ ብለው ሲመክሩን ሲገስፁን ተረትም ሲተርኩልን ሁሌም አጠገባችን ያሉ ያህል ጥልቅ የሆነ የደስታ ስሜት እንደሚሰማን ለማስታወስ ሁላችንም ቢሆን ወደልጅነት ህይወታችን ለአንድ አፍታ ያህል በትዝታ መመለስ ብቻ ጥሩ ምስካሬ ሊሆነን ይችላል።

ይህም ብቻ አይደለም ፥ እኒህ ከያኒ አባታችን ፣ እኒህ መካሪ አባታችን ከቴሌቪዥን መስኮት ተለይተው በነበሩበትም ወቅት ላይ ሁላችንም አንዳች ነገር የጎደለን ያህል ስሜትም የተሰሙን ጊዜያትም ነበሩ።

በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ደግሞ ከአብዛኛዎቻችን የዚህ ትውልድ ልማድ ውጭ በሆነ ሁኔታ ጋዜጠኛው ሰይፉ ፋንታሁን እኒህን አባት በተደጋጋሚ በመጎብኘትና ከጎናቸውም ባለመለየት ከተነፋፈቁት ህዝብ ጋርም መልሰው እንዲገናኙ ያደረገበት ሁኔታ ነበር።
እኛም እንግዲህ ብዕራችንን በማንሳት ፥ ሰውም በህይወት እያለ ለሰራው መልካም ስራ መመስገን አለበት በማለት ጋዜጠኛውን ሰይፉ ፋንታሁን ሆይ ስላደረከው መልካም ስራ ሁሉ ልናመሰግንህ እንወዳለን በማለት ላቅ ያለ አክብሮትና ከበሬታችንን ይኸው አድርሰናል።
መልካም ምሽት ! DIRETUBE

READ  ሳውዲ አረቢያ ለመጀመርያ ግዜ ለኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ሰጠች

NO COMMENTS