ጳጳስና ፓትረያሪክ ፊት የነሳው የአባባ ተስፋዬ ቀብር

0
ጳጳስና ፓትረያሪክ ፊት የነሳው የአባባ ተስፋዬ ቀብር
ቀብር፡፡ እዚህ ሀገር አንድ ነጠላ ዜማ ካልሰራህ አልያም ተከታታይ የቴሌቨዥን ቧልት ላይ ካልቦለትክ እንኳን ሀገር ቤተክህነትም አታከብርህም፡፡

ጳጳስና ፓትረያሪክ ፊት የነሳው የአባባ ተስፋዬ ቀብር | እዚህ ሀገር አንድ ነጠላ ዜማ ካልሰራህ አልያም ተከታታይ የቴሌቨዥን ቧልት ላይ ካልቦለትክ እንኳን ሀገር ቤተክህነትም አታከብርህም፡፡ | ከስናፍቅሽ አዲስ

ከሰው ኑሮ ይልቅ የሰው ሞት ብዙ የሚያስተምርበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ አባባ ተስፋዬ ዝቅ ብለው ኖረው ከፍ ብለው እንዲቀበሩ የተደረገውን ጥረት አይተናል፡፡ ለአንድ ቀን አዳራሹን የማይፈቅድ ተቋም እንደ አስለቃሽ ሬሳ ስር መርመስመስ ባህሉ በሆነባት ሀገር መሞት ሁለት ሞት ነው፡፡

የአባባ ተስፋዬ ቀብር ላይ የጠበቅነው ቀርቶ ያልጠበቅነው ሆኗል፡፡ የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር ሹማምንት ከሕይወት ዘመኑ ከያኒ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም መሰል አፈር ለማልበስ ጊዜ አጥተዋል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን  በአባባ ተስፋዬ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

መንግስት በሁለተኛው ሰው የተወከለበት የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ቤተ ክህነት ሲሆን ፓትረያሪኳን አሊያም ጳጳሳቷን ወክላ ትገኛለች ብሎ የማይጠረጥር ዜጋ አለ ብዬ አላምንም፡፡

ቤተ ክህነት ከኢየሱስ ቼጉቬራ ይበልጥብኛል ብሎ የሚያምነውንና እምነቱን በአደባባይ ለወጣቶች ሲሰብክ የኖረውን ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር በፓትረያሪኩ መሪነት በብጹአን ጳጳሳት አጃቢነት በክብር ቀብረዋለች፡፡

በርካታ ድምጻውያን በጳጳሳት አጀብ ቀብረናል፡፡ በቴሌቨዥን ድራማዎች ላይ ከማሳቅ ያለፈ ሚና ለትውልዱ ትተው ያላለፉ ሰዎች በቤተክህነት ክብር አግኝተው ከፍ ባለ መንፈሳዊ ማዕረግ ሲቀበሩ አይተናል፡፡

በእርግጥ አሁን የገባኝ ነገር ቤተ ክህነት በክብር እንድትቀብርህ ኢትዮጵያን ወክለህ ኮርያ መዝመት የለብህም፤ ሕይወት ዘመንህን ህጻናትን ለማረቅ መድከምህም አይበጅህም፡፡

ይልቁንም አንድ ዘፈን ዝፈን፤ አሊያም ራሷን ጨምረህ እየሸረደድክ ተፈላሰፍ፣ ወይም ዝናህ ከገንዘብህ ጋር ከፍ ብሎ ግነን ያኔ፤ አቤት የጳጳሳቱ ብዛት፤ ያኔ አቤት የሰንበት ተማሪው ዝማሬ፤ ያኔ አቤት የቀሳውስቱ ጥንድ ድርብ፤ አባባ ተስፋዬ ምናልባትም የመጨረሻውን ምዕራፍ ሲንከራተቱ የተመለከቱ የቤተ ክህነት ሹማምንት መንግሥት የማይፈልጋቸው ይሆኑ ይሆን በሚል ችላ ያሉት የቀብር ስነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኙ፡፡

READ  ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎቻቸው ኪሳራ ተሰልቶ ካሳ እንዲከፈላቸው ጠየቁ

ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ያለፉት የኢትዮጵያ ታላቅ ሰው የሃይማኖት አባቶችን ትኩረት ባልሳበ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተሸኙ፡፡ ጳጳስና ፓትረያሪክ ፊት የነሳው የአባባ ተስፋዬ ቀብር ተረሳና ሕይወት ሌላ ምዕራፍ ጀመረች፡፡ DIRETUBE

NO COMMENTS