Connect with us

Art and Culture

ከጾለቶች ሁሉ ምላሽ የማያገኝ፤ ‹‹እባክህ ጌታ ሆይ አክባሪ ሴት ስጠኝ!››

Published

on

ከጾለቶች ሁሉ ምላሽ የማያገኝ፤ ‹‹እባክህ ጌታ ሆይ አክባሪ ሴት ስጠኝ!››

ከጾለቶች ሁሉ ምላሽ የማያገኝ፤
‹‹እባክህ ጌታ ሆይ አክባሪ ሴት ስጠኝ!››
(አሳዬ ደርቤ በድሬቲዩብ )


በዚህ መሬት ላይ እንደሚስቴ የምፈራው ፍጡር የለም፡፡ በቁመት ከቻርሊ ቻፕሊን የምታንስ ቢሆንም ስትቆጣ ግን ከሜትር አርቲስት አፈ-ወርቅ ተክሌ› ትረዝማለች፡፡ ሚስቴ በአንድ ወገኗ ከአቦ-ሸማኔ ጋር የሚያዛምዳትን ጥፍሯን የምታሳድገው እኔን ለመሟጨር እንጂ ለጣቶቿ ማማር ስለምታስብ ነው ብዬ አልወስደውም፡፡ እኔን ካገባቸ ጊዜ ጀምሮ እንደ ጥፍር ቀለም የምትጠቀመው የኔን ደም ሁኗል፡፡ በዚህም የተነሳ ደም ልለግስ ወደ ቀይ መስቀል ሄጄ ተለግሼ መመለሴ የቅርብ ጊዜ ትዝታዬ ነው፡፡
.
ሹራብ ስገዛ ከውበቱ በላይ ባለ ኮፊያ ስለመሆኑ እጠነቀቃለሁ፡፡ ኮፊያው ከጸሐይ ጨረር ብቻ ሳይሆን ቢያንስ በሳምንት ሁለት ቀን በሚስቴ ሹል ጥፍር አንገቴ ላይ የሚፈጠርን ንቅሳት ለመደበቅ ይረዳኛል፡፡

ሃይለኝነቷ ሲደክማት የዋለ ቀን ይብሳል፡፡ የድካሟ ምንጭ ተጫምታው ከምትውለው ባለ ተረከዝ ጫማዋ ጋር የተያያዘ መሆኑን በተደጋጋሚ ብነግራትም ‹‹አጭር›› ከመባል ይልቅ ሲደክሙ መዋልን ምርጫዋ አድርጋዋለች፡፡ እናም በቀጫጫ እግሯ ‹‹አይፈል ታወርን›› ስትገትት ትውልና አመሻሽ ላይ በድካም ዝላ ወደ ቤቷ ስትመጣ ሁሉም ነገር ለጠብ የሚያነሳሳት ሆኖ ያርፋል፡፡
.
የሚስቴ የሃይለኝነት ባህሪ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን ሞባይሌም ላይ ተፅዕኖውን አሳርፏል፡፡ ልክ ባለቤቴ ስትደውል መጥሪያውን ከሳይለት ሞድ ወደ ቫይብሬሽን በራሱ ጊዜ ይቀይርና መንቀጥቀጥ ይጀምራል፡፡

ምን ያድርግ? እኔ ባመጣሁበት ጣጣ እሱም ብዙ ጊዜ የመፈርከስ አደጋ ደርሶበታል፡፡
ይሄንን ለጉዳት የተፈጠረ ስልክ እንደገዛሁት አካባቢ አብዛኛው ባለትዳር ወንድ እንደሚያደርገው ሁሉ በፓስወርድ ተብትቤው ነበር፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ ማድረጌ ከእሷ የሚደበቅ ሚስጥር ስላለኝ ሳይሆን ‹‹ጊዜው ሲደርስ የፍች ማመልከቻዬን እሰጣታለሁ›› በማለት ነው፡፡

READ  ዶ/ር መረራ የኦሮሚያን ብጥብጥ በማባባስ ክስ ተመሠረተባቸው

አንድ ቀን ታዲያ ይሄን ትብታቦዬን ስፈታ ሚስቴ ከአጠገቤ መቀመጧን ዘንግቸው ነበር፡፡
‹‹ፍቅርዬ እንዲህ ያለ ውስብስብ ፓስወርድ ስልክህ ላይ የምታደርገው ለምንድን ነው?›› አለችኝ ከእሷ በማይጠበቅ ለስላሳ ድምጽ፡፡
ዝም ብዬ ስራ ስፈታ ያደረኩት መሆኑን ነገርኳት፡፡
‹‹እስኪ ፍታው አለችኝ፡፡››
‹‹ትዳራችንን ነው?›› ልላት ብዬ ሙጭሪያዋን ስለፈራሁ መስመሮችን በማገጣጠም የሰራሁትን ላሊበላንና አክሱምን አጣምሮ የያዘ ፓስወርድ ፈትቼ ሰጠኋት፡፡
‹‹አሁን ደግሞ የፌስቡክህን ፓስወርድ አስገባው›› አለችኝ ብሮውሰሩን ከፍታ እየሰጠችኝ፡፡

አዕምሮዬን በፍጥነት በማሰራት በትክክለኛው ሰዓት ‹‹ሊዮ›› ኮከቤ ያደለኝን የትወና ብቃት ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ በመነሳት እተገብረው ጀመር፡፡

‹‹ለምንድን ነው ግን የሞቀ ትዳራችንን ባልተገባ ጥርጣሬ ውሃ የምትከልሽበት? ለምንድን ነው የዋህና አፍቃሪ ልቤን እንደ አንገቴ በየቀኑ የምትተለትይው?›› ወዘተረፈ እያልኩ ያለ ምንም እረፍት ለሩብ ሰዓት ያህል ዘበዘብኩኝ፡፡ (ጌትነት እንየውም እንዲህ አይተውን!)

‹‹በቃ ተወው እሽ የኔ ጌታ አትናደድብኝ›› ስትለኝ መንጎራደዴን አቁሜ እያለከለኩኝ ከአጠገቧ አረፍ አልኩኝ፡፡ (በጊዜው ከድካሜ ተነስቼ ማረጋገጥ የቻልኩት ነገር የቲያትር ተዋናዮች የድካማቸውን ያህል ክፍያ እንደማያገኙ ነው፡፡)

እናም በጣቷ አንገቴን እየደባበሰች ‹‹የማላምንህ እኮ ማርዮ….›› ስትለኝ ከአፏ ቀበል አድርጌ ‹‹የማታምኒኝ እኮ!›› አልኳት መለሳለሷ ያልታሰበ ጥቃት ለመሰንዘር መሆኑን ሳልረዳ፡፡

‹‹የማላምንህማ ሲያምኑህ የማትታመን ሰላቢ ተዋናይ መሆንህን ስለማውቅ ነው›› ብላ ስታሻሸው የነበረውን አንገቴን በብርሐን ፍጥነት በጥፍሯ ተለተለችው፡፡ ይሄም አልበቃ ብሏት አምስት ሺህ ጉብላሊት ጓደኞቼን እንደያዘ ሳምሰንግ ሞባይሌን ወለሉ ላይ አረገፈችው፡፡

ለአፍታ ይህል በልሳን ካወራሁ በኋላ ወደ መስታወቱ ሄጄ አንገቴን ስመለከተው ሞባይሌ ላይ የተበተብኩት ፓስወርድና አንገቴ ላይ ያሰመረችልኝ ንቅሳት በቅርጹ ተመሳሳይ የሚባል ነበረ፡፡
.
ይሄም ሆኖ ልፈታት እንጂ ልመታት አልፈልግም፡፡ ካልቾዬን ባሳርፍባት ከእሷ መጎዳት ባለፈም አገራችንን ‹ረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳዔል ተኮሰች› ብለው ሃያላን አገሮች ማዕቀብ ሊጥሉባት ይቻላሉ፡፡

READ  የተመስገን ደሣለኝ ቤተሰቦች እሥር ቤት እንዳጡት ይናገራሉ

በነገራችን ላይ አብዛኛው ባለትዳር ወንድ ታቅፎት የሚዞረውን ግርማ ሞገስና ክብር ወደ ቤቱ ሲገባ ይዞት አይገባም፡፡ እንደ እኔ በሚስቱ ጥፍር ባይተለተል እንኳን በነገር ሲቀቀል የሚያድር ነው፡፡

ሌላውን ተውትና አጼ ቴወድሮስን ዉሰዱ፡፡ በጀግንነታቸው ምድር የምትርድላቸው ንጉስ ቢሆንም ይሄ ጀግንነታቸው ግን በሚስታቸው በጥሩ-ወርቄ ፊት ላይ ግርማ አልነበረውም፡፡

ባንድ ወቅት እንደውም ላንድ ንጉስ በማይመጥን መልኩ በግልምጫ ስታፈርጣቸው ገብርዬ ተመልክቶ ‹‹እንዴት ብትጠግብ ነው ጌታዬን ለመዳፈር የበቃችው›› ብሎ ሲቆላጭ አጼው የመለሱለት ‹‹አይ ገብርዬ አንተ የምታውቀኝ ታጥቄ፣ እሷ የምታውቀኝ አውልቄ›› በማለት ነበር፡፡

ያም ሆኖ በእኛ በኩል ግን ከልብሳቸውን ጋር ጸጉራቸውንም ጭምር አውልቀው ሚስቶቻችንን ስናያቸው ምስኪን ከመሆናችን የተነሳ የማነቅ እንጂ የመናቅ ስሜት ገጽታችን ላይ አይስተዋልም፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

የኢትዮጵያ ባንዲራ ጉዳይ የባንዲራ ቀን አጀንዳ?

Published

on

የኢትዮጵያ ባንዲራ ጉዳይ የባንዲራ ቀን አጀንዳ?

የኢትዮጵያ ባንዲራ የሙስሊሙም የክርስቲያኑም የአይሁዱም ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከእነዚህ እምነቶች መምጣት በፊት ያገኘችው የህገ ልቦና ዘመን ቃል ኪዳን ነውና?  | ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

አልታደልንም፡፡ ይህው በባንዲራችን እንኳን መች እንግባባለን፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ እንደኛ ብዙ ባንዲራ ይዞ አንድ መሆን ያቃተው ቀደምት ህዝብ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡

ኮኮቡን የሚጠሉ ወገኖችም ሆኑ አንበሳውን የሚናፍቁ፣ አሊያም ኮኮቡ ጌጣችን ነው ያሉ፤ ዓላማቸው በባንዲራ ልዩነት አንድ የነበረችውን ሀገር አስር የማድረስ እስኪመስል ግራ አጋብተውናል፡፡

የኢትዮጵያን ባንዲራ ቀለማት የእኔ ብላ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፋና ወጊ ናት፡፡ ይሄ የሚያስመሰግን ነው፡፡

ጥቂት መስመር የሳቱ እምነታችን ኦርቶዶክሳውያን ነው የሚሉ ወገኖች ደግሞ ባንዲራውን ሙሉ የእምነታችን ነው በማለት ለሀገራዊ አንድነቱ እንቅፋት የሆኑ ይመስለኛል፡፡

ከዚህ ቀደም አንድ ጽሑፍ ላይ ያነበብኩት ሀሳብ ይሄንን ይበልጥ ያብራራልኛል ብዬ አስባለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ባንዲራ የአይሁዱም፣ የክርስቲያኑም የሙስሊሙም ኢትዮጵያ ነው፡፡ የባንዲራው ታሪክ መነሻ ኖህ ነው፡፡ ኖህ የህገ ልቦና ዘመን ነቢይ ነው፡፡ ኖህ የአይሁድ አባት ነው፡፡ ኖህ የክርስቲያኖች ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ ኖህ በእስልምና ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ነቢይ ነው፡፡ እንግዲህ ሦስት ሳንሆን በፊት አንድ አድርጎ ያግባባን የነበረው የኖህ ቃል ኪዳን ነበር ማለት ነው፡፡ አሁን በባንዲራችን ሳቢያ ብዙ ሆነናል፡፡

የዘንድሮው ደመራ ላይ የቀድሞውን ባንዲራ ይዘው የታዩ ወገኖች አሁንም የባንዲራ ጉዳይ እንዳልተፈታ አሳይተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሚደረጉ የቄሮ ሰልፎች የኢትዮጵያ ባንዲራ የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችን ያህል እንኳን ውልብ አትልም፡፡

በኦሮሚያ የኦነግ ባንዲራ አሁን ክልላዊ የሆነ እስኪመስል የሰልፎች ማድመቂያ ሆኗል፡፡

ያለ አግባብ በባንዲራ ጉዳይ እረፍት ወስዶ የተነሳው ኢህአዴግ ዳግም ኢትዮጵያን በአንድ ባንዲራ ለማግባባት እያደረኩ ነው የሚለው ጥረት በተቃራኒው ባንዲራ የማያግባባት ሀገር ትፈጠር ዘንድ አንድ ባለድርሻ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

READ  ወራጅ አለ!

በአማራ ክልል ለዘመናት የኖረው የቀድሞ ባንዲራን ይዞ ለቀብር ሥርዓት መውጣት ማስወንጀል ከጀመረ ወዲህ ባንዲራዋ የበለጠ ክብር አግኝታለች፡፡

በተቃራኒው ባለ ኮከቡን ባንዲራ የመንግስት አድርጎ ማየቱም ተለምዷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የባንዲራ ቀንን ከመደገስ ግን አልቦዘንም፡፡ የእኔ ምኞት የሚያግባባንን ባንዲራ ማየት ነው፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

Published

on

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

በትላንትናው ዕለት የተካሄደው 7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች….

የአመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም – ዘመን
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ – አለምሰገድ ተስፋዬ (ያበደች የአራዳ ልጅ 3)
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት – ዘሪቱ ከበደ (ታዛ)
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ – ኢትዮጵያ (ቴዎድሮስ ካሳሁን)
የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ/ድምፃዊት – ዳዊት አለማየሁ
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ – ብስራት ሱራፌል (ወጣ ፍቅር)
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም – ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)/ኢትዮጵያ/
የአመቱ ምርጥ ፊልም -ታዛ
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ – ግርማ በየነ

SHEGER FM 102.1 RADIO

READ  ወራጅ አለ!
Continue Reading

Art and Culture

በጣና ሃይቅ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች ወደስፍራው እያመሩ ነው

Published

on

በጣና ሃይቅ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች ወደስፍራው እያመሩ ነው

በጣና ሃይቅ የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻን ለማገዝ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ 200 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ወደ ባህርዳር እያመሩ መሆኑን የሁለቱም ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጎዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት ጣናን ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች “ጣና የእኛ ነው” በሚል ወደ አማራ ክልል ማምራታቸውን ገልፀዋል።

ጣናን እንታደግ በሚለው ዘመቻ በክልል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒትስር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት ባለስልጣናት የእምቦጭ አረምን መስፋፋት በጣና ተገኝተው የስጋቱን ደረጃ ተመልክተዋል።

እምቦጭ አረምን የማስወገድ የ2010 ዘመቻ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሩ ይታወቃል።

ጣና የአንድ ክልል ሃብት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ገደብ የለሽ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንንም ተከትሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በማምራት ለአንድ ሳምንት የቆየ ለ“ጣናን እንታደግ” ዘመቻ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታዎችን ከባህርዳር ከተማ፣ ከፋሲል ከነማ እና ከአውስኮድ ጋር ሲያደርግ ሰንብቷል።

ደጋፊዎቹም በጣና ሀይቅ የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም በማስወገድ ዘመቻም ተሳትፈው ነበር።

የጎንደር እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች አረሙን ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ የሚያግዙ የተለያዩ ማሽኖችን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ኤፍ ቢ ሲ

READ  የኳታር ረድኤት ድርጅት ለስድስት ሺህ በድርቅ ለተጠቁ ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ማድረጉ ተዘገበ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close