Ethiopia
የኦሮሚያ ጠቅላይ ኦዲት መስሪያ ቤት ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ጉድለት ማግኘቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ጠቅላይ ኦዲት መስሪያ ቤት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በክልሉ መንግስት 320 ተቋማት ላይ ባካሄደው የሂሳብ አሰራር ኦዲት ክንውን ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ጉድለት ማግኘቱን ገለጸ።
የመስሪያ ቤቱ ዋና ኦዲተር አቶ ኤሌማ ቃምጴ በአዳማ አባገዳ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ላለው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ የ2009 ዓ.ም የኦዲት ክንውን ሪፖርት አቅርበዋል።
ዋና ኦዲተሩ በዚሁ ሪፖርታቸው እንደገለፁት ተቋሙ በ428 የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ የገቢና ወጪ ሂሳብ አጠቃቀምን ጨምሮ በፋይናንስ አሰራር፣ የንብረት አያያዝና አስተዳደር ላይ የሂሳብና የአይነት ኦዲት አድርጓል።
በዚህም አብዛኛው ተቋማት ህጋዊ የፋይናንስ አሰራር የተከተሉ ቢሆንም 54 የሚሆኑት በገቢና ወጪ ሂሳብ፣ በፋይናንስ አጠቃቀም፣ በንብረት አያያዝና አስተዳደር ላይ የጎላ ችግር እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ከክልል ጀምሮ በዞን፣ ከተሞችና ወረዳዎች ድረስ ባሉ 320 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ በተካሄደው የፋይናንስ ኦዲት ክንውን ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ የሂሳብ ጉድለትና የሂሳብ አጠቃቀም ችግር ማግኘቱን አመልክተዋል።
በዚህም ወደ መንግስት ካዝና መግባት ሲገባው ያልገባ 414 ሚሊየን ብር በአዳማ፣ ሰበታ፣ ለገ ጣፎ ለገዳዲ ከተሞችና የሰበታ ሀዋስ ወረዳ የገቢዎች ባለስልጣን ላይ የታየ ጉድለት መሆኑን ገልፀዋል።
በአንዳንድ ተቋማት ላይ በሚታየው የወጪ ሂሳብ አስተዳደር አሰራር ግልፅነት የጎደለውና ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ኤሌማ፥ በዚህም ከ628 ሚሊየን ብር በላይ የሂሳብ ጉድለት በኦዲት መገኘቱን ጠቅሰዋል።
ይህ የሂሳብ ጉድለት ከታየባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል ደግሞ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የኦሮሚያ ህንፃዎች አስተዳደር፣ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ገንዝብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር፣ የበቆጂ ከተማ አስተዳደር፣ የምስራቅ ሐራርጌ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽሕፈት ቤት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።
አሳማኝ መስረጃ ሊቀርብበት ያልቻለ፣ ያለአግባብ ወጪ የሆነና ያልተወራረደ 551 ሚሊየን ብር ውዝፍ ሂሳብ ደግሞ በኢሉአባቦራ፣ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፣ በኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትና በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ማግኘቱን ገልፀዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስትን የወጪ አሰራር ሳይከተል ክፍያ የተፈፀመ 595 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር አስፈላጊው ሰነድ ካልቀረበበት ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ ሃሳብ መሰጠቱንና ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት መደረጉን አመልክተዋል።
የኦዲት መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ በየደረጃው በሚገኙ የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ በተደረገው የንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ የግዥ አሰራር ላይ ችግር መኖሩን ለጨፌው በቀረበው ሪፖርት አመልክተዋል።
በዚህም የአዳማ ከተማ ጤና መምሪያ፣ የቡራዩ ከተማ ውሃና ፍሳሽና ገቢዎች ባለስልጣን፣ አዳሚ ቱሉ ግብርና ምርምር ማእከል፣ የሰበታ ከተማ ውሃና ፍሳሽ፣ የመንግስት ግዥ ኤጄንሲ፣ የክልሉ ጤና ቢሮና የመንገዶች ባለስልጣን እንደሚገኙበት ገልፀዋል፡፡
በኦሮሚያ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ግንባታን ለማፋጠን በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግዥ የተፈፀመባቸው ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ማሽነሪዎች ለወረዳዎች ስለመድረሳቸው የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዳልተገኘም የኦዲት ሪፖርቱ አመልክቷል።
በኦዲት ግኝቱ ላይ የተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ አፈፃፀም እስካሁን 25 በመቶ ብቻ መሆኑንም ዋና ኦዲተሩ አቶ ኤሌማ በሪፖርታቸው ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሂሳብ አያያዝና አሰራር፣ የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም፣ የግዥ ሂደቱ ግልፅነት የተላበሰ ለማድረግና ለልማት የተመደበ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል አዳዲስ አሰራሮች መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።
ቅዳሜ የተጀመረው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚውል ኢዜአ ዘግቧል። FanaBC
-
Ethiopia2 days ago
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አዳዲስ ተሿሚዎች ታውቀዋል
-
Entertainment4 days ago
አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ተሞሸረች
-
Ethiopia22 hours ago
ለሜቴክ እና ለኢንሳ አዲስ ዋና ዳይሬክተሮች ተሾሙ
-
Ethiopia4 days ago
ከህገ-መንግስቱ የተኳረፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ!
-
Art and Culture2 days ago
በወርቅ የተሞላው ነገር ግን በሴጣን የተከበበው ተራራ
-
Ethiopia1 day ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶስት ቁልፍ ቦታዎችን ለኦህዴድ መስጠታቸው ጠቃሚ እርምጃ ነው ተባለ
-
Ethiopia24 hours ago
‘የምሞት እየመሰለኝ በጣም ተጨንቄያለው’ ከመሞቱ ሶስት ቀናት በፊት የተናገረው
-
Entertainment22 hours ago
የአርቲስት ታምራት ደስታ የቀብር ሥነሥርዓት ተከናወነ