የታላቁ ኢትዮጵያዊ የሀጂ ዘይኑ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ ተመረቀ

የታላቁ ኢትዮጵያዊ የሀጂ ዘይኑ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ ተመረቀ፡፡
በኳስ ሜዳ የሚገኘው የሀጂ ዘይኑ መስጂድና ማዕከል በርካታ ቅርሶች የሚገኙበት የሀገራችን መገለጫ የሆነው የመቻቻልና አብሮ የመኖር እሴትን የታደለ ኢስላማዊ ፍልስፍናዎች መዐከል በመሆን ይታወቃል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያዊ የሀጂ ዘይኑ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ ተመረቀ

ከታላላቅ ኢትዮጵያዊ ኡላማዎች አንዱ የሆኑት ታዋቂው አባት ሀጂ ዘይኑ ወይም የሙቅና ሼኽ በመባል የሚታወቁት ዑላ ግለ ታሪክ በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ በመታተም ትናንት ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር በሺ የሚቆጠሩ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል፡፡

በሀጂ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ አማካይነት በአቶ አብዱልፈታህ አብደላህ የተዘጋጀው ይህ ግለ ታሪክ ከ1916-2005 ዓ.ም. በሕይወት የኖሩትን ሀጂ ዘይኑን የሕይወት ዘመን ከዘመኑ በፊትና በኋላ ካለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጋር በማስተሳሰር በርካታ መረጃዎችን በመያዝ የተዘጋጀ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢስላማዊ ትምህርትና የዳዕዋ እንቅስቃሴ የጎላ ስም ያላቸውን ታላቅ ዑላማ ስራዎች እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚዳስስ ነው፡፡

በኳስ ሜዳ የሚገኘው የሀጂ ዘይኑ መስጂድና ማዕከል በርካታ ቅርሶች የሚገኙበት የሀገራችን መገለጫ የሆነው የመቻቻልና አብሮ የመኖር እሴትን የታደለ ኢስላማዊ ፍልስፍናዎች መዐከል በመሆን ይታወቃል፡፡ DIRETUBE

 

READ  ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

NO COMMENTS