ቴዲ አፍሮ የነገሰበት ኮንሰርት፤ ብዙ የታዘብንበት መድረክ

ቴዲ አፍሮ የነገሰበት ኮንሰርት፤ ብዙ የታዘብንበት መድረክ
ጎንደር ጎንደር የሚለው ዜማ ከመድረኩ በዲጄ ከአራት ጊዜ በላይ ተዘፈነበት፡፡ ሌላው ሙዚቃው እንዲሁ፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው ለመዝፈን ተራ የሚጠብቅ ድምጻዊ ቁጭ ብሎ ነው፡፡

ቴዲ አፍሮ የነገሰበት ኮንሰርት፤ ብዙ የታዘብንበት መድረክ | ከስናፍቅሽ አዲስ@DireTube

እንግዲህ ኖረን ኖረን ዘመነ ኮንሰርት ላይ ደርሰናል፡፡ ድምጻውያን ከካሴቱ ባላይ ተስፋ የሚያደርጉት የገቢ ምንጭ እንዲህ ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተጋጥመው በመድረክ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት የሙዚቃ ኮንሰርት ነው፡፡

አዲስ ኮንሰርት ተናፍቆ ተናፍቆ እንዳይቀር የመጣ ዝግጅት ነው፡፡ የናፍቆታችን ምክንያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ዐሊ ቢራን ከማሕሙድ ጋር አንድ መድረክ ማየት ከመናፈቅ በላይ ወደ ሆነ ስሜት ይወስደናል፡፡

ለዓመታት ከኤፍሬም ታምሩ ጋር ትገናኛለህ የተባለ አድናቂ ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ያው ታደምን፡፡ እኛ ቴዲ አፍሮ ብለን አልነበረም የታደምነው፡፡ ለካንስ ድፍን የሚሌኒየም አዳራሽ ሰው አንድ ትኬት ቆርጦ አንድ ሰው በድብቅ በመያዝ ሁለት ሆኖ ገብቷል፡፡ ያ ሰውማ ቴዲ አፍሮ ነው፡፡

የታደለ ኤፍሬምን ፍለጋ ገብተን ቴዲ አፍሮን አደመጥን፡፡ ዲጄ ሼሪ እንዲህ ተፈትኖ የሚያውቅ አልመሰለኝም፡፡ እንዲያም ሆኖ ጥሩ አድርጎ መድረኩን አዝናንቶታል፡፡

ቴዲ እያለ የሚጮኽው ህዝብ ቴዎድሮስ ካሳሁን የነገሰበት የነ ኤፍሬም ታምሩ መድረክ አድርጎት አረፈ፡፡
ጎንደር ጎንደር የሚለው ዜማ ከመድረኩ በዲጄ ከአራት ጊዜ በላይ ተዘፈነበት፡፡ ሌላው ሙዚቃው እንዲሁ፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው ለመዝፈን ተራ የሚጠብቅ ድምጻዊ ቁጭ ብሎ ነው፡፡

ዐሊ ቢራ ኢትዮጵያዊው የምስራቅ አፍሪካ የሙዚቃ ንጉሥ ብቃቱን አሳይቶበታል፡፡ ሰውን ከፍ ወደ አለ ስሜት የወሰደበት ስራዎችን አቀርቧል፡፡

አቢ ላቀው የመድረኩ ፈርጥ ነበረች፡፡ ብዙ ሰው ኤፍሬምን ለማየት ጓጉቶ ቢመጣም ሰው እንደ ጠበቀው ብዙ ዘፈን በመድረኩ አልተጫወተም፡፡ ይልቁንስ ብዙም ሩቅ ያልሆኑ ድምጻውያን ብዙ ስራ በመጫወት ታዳሚው እንዲሰለቸው አድርገዋል፡፡

READ  Bedilu Ayele with a big heart but Poor

የጋሽ ሙሐሙድ ነገር እንደምታውቁት ነው፡፡ ባይሆን ባይሆን ደረጃው ከፍ ያለ የሙዚቃ ኮንሰርትን ከፍ ያለ ብር ከፍሎ መግባት የለመደው ህዝባችን እንደ ከፈለው ብር ደረጃውን የጠበቀ የሳውንድ ሲስተም አልታደልንም፡፡ የድምጽ ችግር አሁንም ችግራችን መሆኑ ታይቷል፡፡

መድረኩን ዝቅ ካደረጉ አጋጣሚዎች አንዱ የድምጹ ችግር ነው፡፡ የዐሊ ቢራን ሙዚቃ ለማጣጣም እንኳን እንከን ሆኖ ነበር፡፡
ከታናፈቀው የሙዚቃ ኮንሰርት የወጣ ሰው ምን ትዝታ አተረፍክ ቢሉት ቴዲ በሌለበት ሲነግስ አየሁኝ ማለቱ አይቀርም፡፡ አዲስ ኮንሰርት ቴዲ አፍሮ የነገሰበት የብዙ ድምጻውያን የጋራ መድረክ ነበር፡፡

DIRETUBE[/signinlocker-bulk-1]

NO COMMENTS