Connect with us

Environment

በአርባምንጭ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

Published

on

በአርባምንጭ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአርባምንጭ ከተማ ባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ተመስገን አንጁሎ ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው ትናንት ጠዋት ላይ የደረሰው በከተማው ዓባያ ክፍለ ከተማ ኩልፎ ቀበሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው መንደር ነው፡፡

በመንደሩ ንብረትነቱ የአቶ ወልደ ሰንበት ጋጋ የሆነ ባለሁለት ፎቅ መኝታ ቤት ተደርምሶም በመኝታ ቤቱ አልጋ ይዘው የነበሩ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በአርባምንጭ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡

በህንፃው ፍርስራሽ ውስጥ ቀሪ ሰዎችን ለማግኘት ቁፋሮና የነፍስ አድን ስራው እንደቀጠለ አስታውቀዋል፡፡

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኤዞ ኤማቆ በበኩላቸው ግለሰቡ ህንፃውን የግንባታ ፈቃድ ሳያገኝ እየገነባ መሆኑ በመረጃ ተደርሶበት በህግ መጠየቁን ገልጸዋል፡

ደረጃውን ሳይጠብቅ በድብቅ ማታ ማታ ግንባታውን በማካሄድ በህገ ወጥ መንገድ የመኝታ ቤት ኪራይ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ተግባሩ ቀደም ሲል ክስ ተመስርቶበት በህግ ሂደት ላይ እያለ አደጋው መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉንም አመልክተዋል፡፡ ENA

READ  የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
Continue Reading

Art and Culture

መስቀልን መናፈቅ ከዳሞታ ተራራ ሥር፤ ከጊፋታ ናፍቆት ጋራ

Published

on

መስቀልን መናፈቅ ከዳሞታ ተራራ ሥር፤ ከጊፋታ ናፍቆት ጋራ

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም መስቀልን መናፈቅ በሚል ከዛሬ ጀምሮ ተከታታይ የመስቀል በዓል ዘገባዎቹን ይዞልን ይቀርባል፡፡ ከወላይታ እስከ ጎፋ፣ ከኦይዳ እስከ ጋሞ፣ ከጉራጌ እስከ ዓጋመ የመስቀልን ድባብ ይተርክልናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ይህ ተራራ ዳሞታ ይባላል፡፡ ከእግሩ ጫፍ አናቱ ድረስ አረንጓዴነቱ በሚደምቅበት በዚህ ወቅት የወላይታን ፍሰሐ የጊፋታን ድምቀት ሲታደም የኖረ ተፈጥሮ ነው፡፡

የዳሞታ ጫፍ ዘመን የሚሻገር ታሪክ ደብቆ ኖሯል፡፡ የዳሞታ ግርጌዎች ደግሞ ለዘመናት የጊፋታን ድግስ ያደመቁ መቼቶች ናቸው፡፡ መስቀልን በመናፈቅ ስሜት ውስጥ ነኝ፡፡

ከመስቀል በኋላ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ እምነቴ ተስፋ ከማድረግ የመጣ እንጂ ከትንቢት የተነሳ አይደለም፡፡ የደመራውን ጢስ ተከትሎ መከራችን ወደ ሰማይ የሚበን ስለሚመስለኝ መስቀልን እናፍቀዋለሁ፡፡

የመስቀል ድባብ ከጎንደር ከተማ አናት ከጎሃ ላይ ቁልቁል ይታየኛል፡፡ መስቀላይ የዐጋመዎች መንደር ይወስደኛል፡፡ የጉጌ ጫፍ አዘቅዝቆ የሚመለከተው የመስቀልን በዓል ውበት ነው፡፡ ከአልባ ዙማ እስከ የም መንደሮች መስከረም የደስታ ወር ነው፡፡

ወላይታዎች ደስ ብለውኛል፡፡ ባህላቸውን ሃይማኖትን ምክንያት ከሚያደርግ ጥፋት እየታደጉት ነው፡፡ መስቀልን እንደ ባዕድ አምልኮ የሚቆጥሩ የማንነታችን ጥፋቶችን የሚያሸንፍ መንፈስ ከቦደቲ እስከ አረካ፣ ከቦሎሶ ሶሬ እስከ ዳሞት ጋሌ ሰፍኖ አየሁ እናም ዮዮ ጊፋታ የሚለው ድምጽ ሲያስተጋባ ይሰማኛል፡፡

መስከረምን የምናፍቀው ክረምት ጠላት ሆኖብኝ፣ ዝናብን እንደ አበሳ አይቼው አይደለም፡፡ መስከረም ጭፍግግ የሚለውን ስሜት በደመራው ብርሃን አፍክቶ ለአዲስ ዘመን ስለሚያሻግር ነው፡፡

መስከረምን ለማወደስ መነሻም መድረሻም የመስቀሉ ድባብ ነው፡፡ ይህ የመስቀል ድባብ በደስታ የሚጋልብ፣ ከግቤና ከኦሞ ወንዞች ይበልጥ የሚገማሸር ሀሴት የተሞላ ነው፡፡ እናም መስከረም ይናፍቃል፡፡

READ  ኢሕአዴግ በሕገ መንግሥቱ በድንበር ጉዳይና በፖለቲካ እስረኞች ዙሪያ እንደማይደራደር ግልጽ አደረገ

በዳውሮዎች ቶኪቢያ አንድ ብሎ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ሰማይ ደስታውን እስከ የም ሄቦ ይዞን ይጓዛል፡፡ ለእርድ የቆሙት ሰንጋዎች ከሰንሰለታማዎቹ ተራሮች በላይ ገዝፈው ይታዩኛል፡፡ ስጋ ብቻ አይደሉም፡፡ አብሮ የመኖር መገለጫዎች ናቸው፡፡

ደስታ ብቻ አይደሉም፡፡ አመትን የሚያርቁ የናፍቆት ትዝታዎች ናቸው፡፡

የመስቀልን ናፍቆት ዘመኑን ይፈውሳል በሚል ተስፋ እናፍቀዋለሁ፡፡ በዚህ ናፍቆት ውስጥ ከደምባ ጎፋ እስከ ገዜ እንጓዛለን፡፡ ያንን የጋልማ ድባብ፣ ያንን የካዎ አማዶ ቀዬ ድግስ እስከ ጊያ ካንሶ እንተርከዋለን፡፡ የዚህ ዘገባ ምስሎች የተገኙት የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝም በፌስቡኩ ከለጠፈው የጊፋታ ናፍቆት ነው፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Environment

ሶስት ልጆቹን በአንዴ ያጣው አርሶአደር ልብ የሚነካ ገጠመኝ

Published

on

ሶስት ልጆቹን በአንዴ ያጣው አርሶአደር ልብ የሚነካ ገጠመኝ

አቶ ኃይሉ ታዬ ሦስት ወንድ ልጆቻቸውን በአንዲት ቅፅበት አጡ

እለቱ ነሐሴ 17/2009 ዓ.ም ነበር:: መርሐ ቤቴ ወረዳ ሐሮ ገንዳ ቀበሌ:: አቶ ኃይሉ ታዬ የደረሠ ሰብላቸውን ከአረም ለመከላከል ሌሎች አምስት ሰዎችን ጨምረው ከሦስት ወንድ ልጆቻቸው ጋር ለአረም ተሠልፈዋል:: በመሀል ስለቀጣይ ህይወታቸው ጉዞ ተወያይተው የኑሯቸውን አቅጣጫ በውይይት አስተካክለው አስቀምጠዋል::

ስድስት ሠዓት አካባቢ እንደሆነ ነበር መጠነኛ ዝናብ መጣል ጀምሮ አራሚዎች ማሳቸውን ትተው ወደ መጠለያ ጐጆ ያመሩት:: የጐጆዋ ማነስ አቶ ታዬን ከልጆቻቸው ጋር እንዲጠለሉ አልፈቀደችም:: እናም ትንሽ ራቅ ብለው የወቅቱን ዝናብ አመለጡ:: አቶ ኃይሉ ወደ ማሳቸው ተመልሰው ሥራቸውን ጀመሩ:: ግን ማንም ሊመጣ አልቻለም:: ልጆቻቸውን መጥራት ጀመሩ:: መልስ የለም:: በተደጋጋሚ ሞከሩ:: መልሱ ፀጥታ ሲሆንባቸው ወደ ጐጆዋ ዘልቀው ገቡ:: የሚያዩትን ማመን ተሳናቸው::

ከደቂቃዎች በፊት ስለቀጣይ የህይወት ዑደታቸው ተጨንቀው ያወያዩዋቸው ሦስት ልጆቻቸው ከቀሪዎቹ አምስት ሰዎች ጋር በመብረቅ ተመትተው ህይወታቸው አልፏል:: ጉርምስናቸውን ተመልክተው የሳሱላቸው ልጆቻቸውን አስከሬን ከማንም ቀድመው ራሳቸው አዩ:: የሚገርመው የነበሩበት ርቀት 100 ሜትር የማይሞላ ቢሆንም የመብረቁ አደጋ ሲደርስ አልሰሙም::

ወ/ሮ ወርቅአፈራሁ እንግዳሰው የመርሐ ቤቴ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው:: ይህ አደጋ በመጠን የገዘፈ ቢሆንም ሌሎች የመብረቅ አደጋዎችም በወረዳው መከሠታቸውን ገልፀዋል::

በአጠቃላይ በዚህ ክረምት በወረዳው የአስራ አንድ ሰዎች ህይወት በመብረቅ አደጋ ጠፍቷል::… በቆቦ ከተማ ለአንድ ሳምንትና ከዚያ በላይ መብራት ተቋርጧል:: ይህ በከተማዋ የመብራት ታሪክ በጣም አስከፊ የሚባል ነው:: ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የመብራት ተሸካሚ ምሰሶዎች በመብረቅ ተመትተው ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ለመቀየር ጊዜ በመውሰዱ ነው።

በሰው ላይ የተከሰተ ጉዳት ባይኖርም በከተማዋ ከሚገኙ መስጊዶች በአንደኛው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል:: በዚህ ክረምት ከፍተኛ የመብረቅ አደጋ የተከሰተበት ሌላው ስፍራ የአፋር ክልል ነው:: ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባለሙያ ከአቶ ከድር አሊ ጋር በስልክ ባደረግሁት ቆይታ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከ70 በላይ ሰዎች በመብረቅ አደጋ መሞታቸውን ገልፀውልኛል::

READ  “ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም እየመጣ ነው ተባለ

ፓሊስ ሙሉ መረጃውን እያጠናቀረ ሲሆን ምናልባትም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል:: የጉዳቱ መጠን ይለያይ እንጅ በዘንድሮው ክረምት ሌሎች አካባቢዎችም ከፍተኛ የመብረቅ አደጋ ተከስቶባቸዋል ። ይህን ተከትሎ አደጋው በዚህ ደረጃ እንዲጨምር ያደረገውን ምክንያት ለማወቅ የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ የቅድመ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ጫሌ ደበሌን አነጋግሬያለሁ:: በእርሳቸው ገለፃ መሠረት ምድር ላይ የሚከሠት ከፍተኛ የሙቀት መጠን ትልቁን ድርሻ ይወስዳል::

መብረቅ የሚከሰተው ከፍታ ላይ በተቀመጠ ከፍተኛ የደመና ቁልልና ከታች በሚገኙ ስስ የደመና ክምችቶች መካከል በሚደረግ መላተም ነው:: በዚህ ሂደት ከመሬት በከፍተኛ ሙቀት ትነት የሚሠራው ይህ ደመና ዕርስ በርሱ እየተጋጨ በረዶና ብዛት ያለው የብርሃን ብልጭታን ይፈጥራል:: ይህ የሚሆነው እንግዲህ የደመና ክምሩ እየፈረሠ በሚጋጨበት ወቅት በሚፈጠሩት አሉታዊና አወንታዊ የኤሌክትሪክ ምንጮች መሳሳብ ምክኒያት ነው፤ ይህ በሁለት መልኩ ሊከሠት ይችላል::

አንደኛው አየር ላይ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ እነዚህ የኤሌክትሪክ ምንጮች መሬት ላይ ወደሚገኝ ተቃራኒ (አሉታዊ ወይም አወንታዊ) የኤሌክትሪክ ምንጭ በመሳሳብ ፍንዳታ ያስከትላሉ:: ከሰማይ የሚወርደው የኤሌክትሪክ ምንጭ ከሶስት መቶ ሺህ እስከ አምስት መቶ ሺህ ዲግሪ ፋራናይት የሙቀት መጠን የያዘ በመሆኑ የመሬት ከባቢ አየር ላይ ከሚገኘው ቅዝቃዜ ጋር ሲጋጭ ፍንዳታው ከፍተኛና አውዳሚ ይሆናል:: በዚህም ምክንያት ነው አብዛኛዎቹ ዓለም ላይ የሚከሠቱት ሠደድ እሳቶች መነሻቸው የመብረቅ አደጋ የሚሆነው።

በክላይሜት ሴንትራል ድረ ገፅ መረጃ መሠረት መሬት በእያንዳንዷ ሠከንድ 100 ጊዜ በመብረቅ ትደበደባለች:: በዚህም መሠረት ዓለማችን በአንድ ሙሉ ቀን ከስምንት ሚሊዮን በላይ የመብረቅ አደጋን ታስተናግዳለች እንደማለት ነው:: በየዕለቱ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ የሚከሠት ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የመብረቅ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያስረዳሉ:: መብረቅ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሠት ከመሆኑ ባሻገር ከሚያደርሰው ሰብዓዊና ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ በተጨማሪ ሠደድ እሳትን በመፍጠር ጫካዎችን አውድሞ ለበረሃነት መፈጠር አስተዋፅኦ ያደርጋል::

READ  ቢቢሲ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞና ትግርኛን ጨምሮ በ11 ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው

የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ ዴቪድ ሮምፕስ በጥናታቸው እንዳረጋገጡት በዓለም ላይ የምትጨምረው እያንዳንዷ አማካይ አንድ መቶኛ የሙቀት መጠን የመብረቅ አደጋን 12 በመቶ እንዲጨምር ታደርጋለች:: በጥናቱ መሠረት ዓለም በ2100 አሁን ካለው ጋር ሲነፃፀር በአማካይ አራት በመቶ የሙቀት መጠን ጭማሪ ይኖራታል::

ጭማሪውን ተከትሎ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በሠከንድ 100 ጊዜ ምድራችንን እየነረተ የሚገኘው መብረቅ መሬት ላይ የሚያደርሠውን ጥፋት በ50 በመቶ ያሳድጋል:: መጥፎው ነገር ደግሞ የሙቀቱ መጠን በየትኛውም የዓለም ክፍል ይጨምር እንጂ የመብረቅ አደጋው ግን በሁሉም ቦታ ሊከሠት መቻሉ ነው:: እንዲያውም ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ባለባቸው አካባቢዎች ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ወይም በተቃራኒው:: ለዚህም ነው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የአንድ የተወሰነ አካል ኃላፊነት ብቻ ተደርጐ የማይወሠደውና የሁሉንም ሀገራት ጥምረት የሚጠይቀው::

በመብረቅ አደጋ በዓለም ላይ ከፍተኛ መሠረተ ልማትና ሠብዓዊ ኪሣራ ይደርሳል:: በአሜሪካ የተደረገውን ጥናት ብቻ ብንመለከት በ2013 በደረሠ የመብረቅ አደጋ 100 ሺህ አሜሪካውያን በመኖሪያ ቤትና ሌሎች ውድመቶች ጋር በተያያዘ የመድን ጥያቄ አቅርበው ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ 869 ዶላር በአማካይ ክፍያ ተፈፅሟል:: ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት በመብረቅ ምክንያት የፈራረሡ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በየዓመቱ 451 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል:: ይህ እንግዲህ መብረቅን ለመከላከል ከሚደረጉ ጥረቶችና ሠደድ እሳትን ለማጥፋት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭ ሳይጨምር ማለት ነው::

በታዳጊ ሃገራት መሠረተ ልማትና ደንን ያወደመ በመብረቅ ምክንያት ሠደድ እሳት ባይፈጠርም፣ የሰውን ልጅ ህይወት ግን እያጠፋ ይገኛል:: ኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ በዚህ ክረምት ብቻ ቁጥራቸው 100 የሚደርስ ሰዎች በመብረቅ ህይወታቸውን አጥተዋል::

READ  ባንኮች ማኅበር ለሦስት የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ዕውቅና ሰጠ

ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሠራችው ስራ ዝቅተኛ በመሆኑ የመጣ ነው ማለት አይደለም:: እንዲያውም በዚህ ዘርፍ ምሳሌ ከሚደረጉት እንደ ጋቦንና ናይጀሪያ ከመሳሰሉት ሃገራት ጋር ተጠቃሽ ነች::

በዚህ ረገድ በየዓመቱ የሚሠራው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራም ሁነኛ ምሳሌ ነው:: ነገር ግን ኢትዮጵያ የራሷን ኃላፊነት በመወጣቷ ብቻ ከአየር ንብረት ለውጥ ጥቃት ታመልጣለች ማለት አይደለም:: በአየር ንብረት ለውጥ የቀመር ስሌት ህንድ ሃገር ውስጥ የተከሠተ ችግር የኢትዮጵያ ትልቅ ጠንቅ ነው::

ደቡብ አሜሪካ ብራዚል ጫፍ ላይ የሚለቀቅ መርዛማ አየር ሚቴንና ካርቦን ለአፋር አርብቶ አደሮች ትልቅ ፈተና ነው:: ለዚህም ነው ከሁለት ዓመት በፊት ዓለም በኢልኒኖ ስትናወጥ ኢትዮጵያም የችግሩ ተቋዳሽ የሆነችው:: አሁን ደግሞ መብረቅ የዜጐችን ህይወት እየቀጠፈ ነው::

እንደ ዴቪድ ሮምፕስ ጥናት ደግሞ የመብረቅ አደጋ እየጨመረ የሚሄድና በየትኛውም ቦታ የሚከሠት ነው:: እናም ለጊዜው ከዚህ አደጋ ለማምለጥ እና ህልውናን ለማረጋገጥ ማንኛዋም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያይዘች ጥቃቅን ተግባር በትኩረትና በጥንቃቄ ልትሠራ ይገባል:: ፋሲካው መንበሩ በኩር ጋዜጣ (የአማራ ክልል ልሳን) መስከረም 1/2010 ዕትም DIRETUBE

Continue Reading

Business

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የዓለም አቀፍ ሽልማት ተረከበች

Published

on

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የዓለም አቀፍ ሽልማት ተረከበች

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽልማት ተረከበች።

ሽልማቱ በረሃማነትን እና የመሬት መሸርሸርን በተሳካ ሁኔታ የሚከላከሉ ህጎችን እና አሰራሮችን አውጥቶ ተግባር ላይ በማዋል ውጤታማ ለሆኑ ሀገራት የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ዓላማውም በረሃማነትን ለመከላከል እና ውጤታማ ዘዴዎችን ለማጠናከር ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በረሃማነትን መዋጋት አካባቢን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

በዚህ ተግባር የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የትግራይ ክልልም ሽልማቱን ተረክቧል።

ክልሉም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና የወጣት ተሳትፎ ጥምረት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ መጠን መሬት መልሶ የማልማት ስራ በመስራት ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

በውጤቱም የአፈር መሸርሸር በእጅጉ በመቀነሱ፣ የከርሰ ምድር ውኃ በመጨመር፣ ዘላቂ የግብርና ልምዶችን በማጠናከር፣ በምግብ እህል ራስን በመቻል እና የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል።

ሽልማቱ የተሰጠው መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም የምርጥ ፖሊሲ ሽልማት በዓል አስመልክቶ በቻይና በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የልማት ኮንፈረንስ 13ኛ ስብሰባ ላይ መሆኑ ተነግሯል። ኤፍ.ቢ.ሲ

READ  የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!