መድረክ ዶ/ር ሚልዮንን በሊቀመንበርነት፣ ፕሮፌሰር በየነን በውጭ ግንኙነት ኃላፊነት መረጠ

መድረክ ዶ/ር ሚልዮንን በሊቀመንበርነት፣ ፕሮፌሰር በየነን በውጭ ግንኙነት ኃላፊነት መረጠ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 13ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስን በመተካት ድርጅቱን ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚመሩለትን ዶ/ር ሚልዮን ቱማቶ በሊቀመንበርነት መረጠ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 13ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስን በመተካት ድርጅቱን ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚመሩለትን ዶ/ር ሚልዮን ቱማቶ በሊቀመንበርነት መረጠ፡፡

አዲሱ ተመራጭ ዶ/ር ሚልዮን ቱማቶ የመድረክ አባል ድርጅት የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ሊቀመንበር ናቸው፡፡ የቀድሞ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለሁለት ጊዜያት ያህል በሊቀመንበርነት በመምራታቸው በቅዳሜው ጉባዔ እንደገና ለሊቀመንበርነት ውድድር ዕጩ ሆነው አለመቅረባቸው ታውቋል፡፡

መድረክ በተጨማሪም አቶ ጎይተኦም ጸጋዬ ከአረና፤ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ሙላቱ ገመቹ ከኦፌኮ፤ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ ወ/ሮ ራሔል ባፌ ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ፤የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ኃላፊ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ፤ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ካሕሳይ ዘገየ ከአረና፤ የመድረክ ዋና ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የሕብረብሔራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ በአባልነት ያቀፋቸው ፓርቲዎች፤ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (ትላንት ባካሄደው ጉባዔ ስሙ የተቀየረ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ፣ የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዐላዊነት (አረና)፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) መሆናቸው ይታወቃል፡፡ DIRETUBE

READ  ኢትዮጵያና ግብፅ ግንኙነታቸውን የሚጎዱ ሁኔታዎችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

NO COMMENTS