የዝውውር መስኮቱ ዋና አጀንዳ አልቫሮ ሞራታ አሁን ደግሞ በአርሰናሎች እይታ ውስጥ ገብቷል

አልቫሮ ሞራታ
የዝውውር መስኮቱ ዋና አጀንዳ አልቫሮ ሞራታ አሁን ደግሞ በአርሰናሎች እይታ ውስጥ ገብቷል

እንደ ስፔኑ ዶን ባሎን የዜና  ምንጭ ዘገባ አርሰናሎች የአሌክሲ ሳንቼዝ ተተኪ አጥቂ ይሆናቸው ዘንድ ብዙዎችን ባስደነቀ መልኩ ዓይናቸውን ወደ አልቫሮ ሞራታ አዙረዋል፡፡እንደዘገባው ከሆነ አርሰን ቬንገር በ52 ሚሊየን ፓውንድ ከሊዮን ላስፈረሙት አሌክሳንደር ላካዛቴ ትክክለኛ አጣማሪ አልቫሮ ሞራታ እንደሆነ አምነዋል፡፡

ሞራታ በሌላኛው የሎንደን ክለብ ቼልሲ የሚፈለግ በመሆኑ መድፈኞቹ ፉክክሩን ለማሸነፍ ከሰማያዊዎቹ ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል፡፡  ሳንቼዝ በቻምፒንስ ሊጉ መጫወት እንደሚፈልግና የሰሜን ለንደኑን ክለብ መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልፅ ተናግሯል፡፡

አለቫሮ ሞራታ ወደ ኦልድትራፎርድ  ይጓዛል ቢባልም  በዩናይትድና በማድሪድ መካከል ስምምነት ባለመደረሱ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ቼልሲ ደግሞ ዘግየት ብሎ በከፍተኛ ሂሳብ ተጫዋቹን ለማግኘት ድርድር የጀመረ ሲሆን አሁን ደግሞ አርሰናሎች የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነዋል፡፡ የዝውውር መስኮቱ አብይ መነጋገሪያ ርዕስ አልቫሮ ሞራታ የመጨረሻ ማረፊያ ክለብ የትኛው ይሆናል የሚለውን ጥያቄ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት ምላሽ እየጠበቁለት ይገኛሉ፡፡

READ  ኮፓ ኮካ-ኮላ የ2017 የኮፓ ኮካ-ኮላን ብሄራዊ ውድድር ያከብራል

NO COMMENTS