Connect with us

Sport

ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች………

Juliana

Published

on

ከስፖርት መዓድ

1-የሞናኮው ተጫዋች ቶማስ ሌማር በአርሰናል በጥብቅ የሚፈለግ ተጫዋች እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመድፈኞቹ እና በፈረንሳዩ ክለብ መካከልም በተጫዋቹ ዙሪያ ድርድሩ ወደ መቋጨቱ መቃረቡን የሚገልፁ ዘገባዎች በሰፊው ሲወጡ ነበር፡፡ አሁን ላይ ሞናኮ ሌማርን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አለመሆኑ ተሰምቷል፡፡ ይህም የተጫዋቹን ወደ ኤምሬትስ የመጓዝ ጉግት ውሀ ቸልሶበታል ነው የተባለው፡፡ በእርግጥ ሞናኮዎች ወሳኝ ተጫዋቾቻቸው በተለያዩ ክለቦች እየተወሰዱባቸው ይገኛሉ፡፡በርናንዶ ሲልቫ በቀዳሚነት ወደ ኢትሀድ ያመራ ቀዳሚው ተጫዋቻቸው ሲሆን ቲማዩ ባካዮኮም የቼልሲ ንብረት እነደሆነ በትላንትናወ ዕለት ተረጋግጧል፡፡ብንጃሚን ሜንዲም ወደ ሲቲ ለመግባት የተቃረበ ሲሆን የምባፔም ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው ያለው፡፡ እናም ቁልፍ ተጫዋቾቻቸውን በሌሎች ታላላቅ ክለቦች እየተነጠቁ ያሉት ሞናኮዎች የቶማስ ሌማርን የአርሰናል ዝውውር በስተመጨረሻ ለማገት እንደወሰኑ ዘገባዎች አትተዋል፡፡

2-ጆሴ ሞሪንሆ የአልቫሮ ሞራታን ዝውውር ለምን እነደተደናቀፈባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኞች ይፋ አድርገዋል፡፡ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ እንደገለፁት ከሆነ ለሞራታ ዝውውር አለመሳካት አንድና አንድ ተጠያቂው ሪያልማደሪድ እንደሆነ ተናገረዋል’’በመጀመሪያ ማድሪዶች የተጫዋቹን የመግዣ ዋጋ በግልፅ አስቀምጠው ነበር፡፡እኛም ያን ዋጋቸውን ተመርኩዘን ድረድር ጀመርን፡፡ ሆኖም ግን እነሱ የመጀመሪያ ቃላቸውን አጥፈው በከፍተኛ ደረጃ የማይቀመስ ሂሳብ እንደሚፈልጉ አስረግጠው ነገሩን፡፡ዛሬ የተናገርከውን ነገር ነገ መድገም መቻል አለብህ፡፡ ማድሪዶች ግን ወላውለዋል፡፡ይህም ያሳፍራል’’ ሲሉ የስፔኑን ክለብ ወቅሰዋል፡፡አክለውም ክርስቲያኖ ሮናለዶ ወደ ኦልድ ትራፎረድ የመምጣቱ ነገር ያበቃለት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

3-ኤቨርተኖች የአርሰናሉ የክንፍ ተጫዋች ቲዮ ዋለኮትን በ30 ሚሊየን ፓውንድ ለማስፈረም ማቀዳቸው ተሰምቷል፡፡ ክርስቲያን ቤንቴኬን ከክሪስታል ፓላስ የማግኘት ዕድላቸው የተደናቀፈባቸው ኤቨርተኖች ዥሩድና ዋልኮትን ከመድፈኞቹ ለማስመጣት አስበዋል፡፡ ነገር ግን አርሰናሎች ዥሩድን የዶርተሞንዱን ጋቦናዊ ተጫዋች ኦቦሚያንግን ወደ ኤምሬትስ ለማስመጣት የዝውውሩ አካል ሊያደርጉት እንደወሰኑ ነው የተነገረው፡፡ እንዲያም ሆኖ አሰልጣኝ ሮናልድ ኪዩመን ባለፈው የውድድር ዘመን መድፈኞቹን ሊለቅ ከጫፍ ደርሶ የነበረውን ዋልኮት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ለማስመጣት ከፍተኛ ተስፋ እንደሰነቁ ታውቋል፡፡

4- የዝውውር መስኮቱ አነጋጋሪ አጥቂ አልክሲ ሳንቼዝ አርሰናልን መልቀቅ እንደሚፈልግ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ቺሊያዊው በቻመፒዮንስ ሊጉ ለሚሳተፍ ክለብ መጫወት እንደሚፈልግና የአርሰናልን ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡አርሰናሎች በፕሪሚየር ሊጉ አምስተኛ ሆነው በመጨረሳቸው ከአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውጪ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የአርሰናልና የሳንቼዝ ጉዳይ በየጊዜው ያልተጨበጡ ወሬዎች እየተነዙበት እስካሁን መቋጫን ሳያገኝ አለ፡፡

5-ሪያል ማድሪዶች የሞናኮውን የ18 አመት ኮከብ ምባፔን ለማስፈረም ከማንቸስተር ሲቲ እና ከፒኤስጂ ከባድ የሆነ ፉክክር እንደገጠማቸው ይታወቃል፡፡ 120 ሚሊየን ፓውንድ አይቀመስ ዋጋ የተጫነበት ወጣቱ ምባፔን ለማግኘት ታዲያ ጋሬዝ ቤልን የዝውውሩ አካል ለማድረግ ማሰባቸው ታውቋል፡፡ሆኖም ግን ማድሪዶች አልቫሮ ሞራታን የማጣት አደጋ የተጋረጠባቸው ሲሆን ዩናይትድን 80 ሚሊየን ፓውንድ ተጫዋቹ ላይ በመጫን ያራቁት ቢሆንም ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ቼልሲ ለሞራታ 70 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቧል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close