Connect with us

Sport

ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች………

Juliana

Published

on

ከስፖርት መዓድ

1-ቼልሲዎች ለአርጀንቲናዊ አጥቂ ጎንዛሎ ሄጉዌን 87.5 ሚሊየን ፓውንድ ያቀረቡት ሂሳብ በጁቬንቱሶች ውድቅ መደረጉ ታውቋል፡፡ ጁቬንቱሶች ሂጉዌንን ከናፖሊ በ75.3 ሚሊየን ፓውንድ ባለፈው የክረምቱ ዝውውር ማስፈረማቸው ይታወቃል፡፡ ሰመያዊዎቹ ሮሜሎ ሉካኩን በማንቸስተር ዩናይትድ ከተነጠቁ በኋላ ሌላ ሁነኛ አጥቂ እያፈላለጉ ሲሆን የተለያዩ ሙከራዎችንም እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን አንትኒዮ ኮንቴ ትክክለኛ 10 ቁጥር ለባሽ ለማግኛታቸው ጥርጣሬ ስለገባቸው ይመስላል ዲያጎ ኮስታን ከመልቀቃቸው በፊት ነገሮችን በጥለቀት እየመረመሩ ናቸው፡፡

2-ብራዚላዊው የተከላካይ አማካኝ ሉካስ ሌቫ ከላዚዮ ጋር መነጋገር ይችል ዘንድ ፍቃድ ከሊቨርፑሎች ማግኘቱ ታውቋል፡፡ ትላንተና ሊቭርፑሎች ከዊጋኖች ጋር ካደረጉት ጨዋታ ላይ ከተካተቱት የቡድን ስብስብ ውጪ የሆነ ሲሆን ይህም የጣሊያኑ ክለብ ላዚዮ 5ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ለተጫዋቹ በማቅረቡ ቀዮቹም የሮሙ ክለብ ባሳየው ፍላጎት ሙሉ ፍቃደኛ ቢሆኑም የድርድሩ ጉዳይ ለሉካስ ትተውለታል፡፡ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በብራዚላዊው ዙሪያ ’’ 100 ፐርሰንት እርግጠኛ መሆን አልችልም፡፡አውነታው ግን ሉካስ በክለቡ ሊቆይ ይቻላል አሊያም ደግሞ በተቃራኒው’’ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውታል፡፡ አሁን ላይ በወጡ ዘገባዎች ሉካስ ከላዚዮ ጋር ከስምምነት መደረሱንና ሰኞ አለትም በሰባት ሰዓት ሜዲካል ምርመራ ለማድረግ ቀጠሮ እንደተያዘለት አስነብበዋል፡፡

3-የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ሮሜሎ ሉካኩና ቪክተር ሊንዶልፍን ቢያስፈርሙም ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በዝውውር መሰኮቱ ማግኘት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ልዩው ሰው እንደገለፁት ’’በዝውውር መስኮቱ 50 ፐርሰንት ስራችንን አከናውነናል ማለት ይቻላል ነገር ግን ባለን የቡድን ስብስብ ላይ ሁለት ታላላቅ ዝውውሮችን ማድረግ እንደሚጠበቅብን ይገባኛል፡፡ ቀላል ባይሆንም ያሰብነውን ማሳካት ስለሚኖርብን የምንፈልጋቸውን ተጫዋቾች ባናገኝ እንኳን አማራጮችን እንወስዳለን’’ ሲሉ ካሁን በኋላ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ከፍተኛ ወጪ አባል እንደሚያደርጉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡አሰልጣኙ በዩናይትድ ከተመደበላቸው የተጫዋቾች ማዘዋወሪያ በጀት100 ሚሊየን ፓውንድ ቀሪ ተጫዋቾች ማስፈረሚያ  ሂሳብ ይቀራቸዋል፡፡

4-የዶርትሞንዱ ጋቦናዊ ተጫዋች ኦቦሚያንግ በብዙ ክለቦች እይታ ውስጥ የወደቀ ተጫዋች ነው፡፡ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግን ተጫዋቹን ለማግኘት ከሌሎች ታላላቅ ክለቦች በተሸለ ተጫዋቹን የማግኘት ዕድል እንዳለው ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ አንቶኒዮ ኮንቴ ኦቦሚያንግን ለማስፈረም 65ሚሊየን ፓውንድ አቅርበው ከዶርትሞንድ ጋር ድርድር መጀመራቸው የታወቀ ሲሆን የጀርመኑ ክለብ ጥያቄያቸውን ውድቅ ቢያደርግባቸው እንኳን የሂሳብ መጠኑን ከመጨመር ወደ አይሉም ነው የተባለው፡፡ ቼልሲዎች የገጠማቸውመሰረታዊ የአጥቂ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ያሳሰባቸው በመሆኑ አንፈልግህም ያሉትን አመለኛውን ኮስታ በድጋሚ ለማባበል እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡

5-የሜክሲኮው ግብ አዳኝ ሀቪየር ሄርናንዴዝ(ቺቻሪቶ) በዘንድሮ የዝውውር መስኮት ባየርን ሊቨርኩሰንን እንደሚለቅ እርግጥ  ነው ፡፡ የጀርመኑ ክለብም ማንኛውም 13.5ሚሊየን ፓውንድ የሚያቀርብ ክለብ ቺቻሪቶን መውሰድ እንደሚችል ይፋማድረጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የተጫዋቹ ፍላጎት እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ሁለቱ የለንደን ክለቦች ማለትም ዌስትሃም እና ቼልሲ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ ለሚፈልገው ሜክኳዊ አጥቂ ፈላጊ ክለብ ሆነው ቀርበዋል፡፡ እናም የቺቻሪቶ ቀጣይ ማረፊያ የሎንደኖቹ ማለትም የሰሌቨን ብሊቹ መዶሻዎች አሊያም ደግሞ የአንቶኒዮ ኮንቴ ሰማያዊዎቹ ይሆናሉ በሚል በሰፊው ታምኗል፡፡ ቺቻሪቶ በተለይ በባከነ ደቂቃዎች በሚያስቆጥራቸው አንጀት አርስ ጎሎች በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን 90 ደቂቃ እና የሄርናዴዝ ጎሎች በዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ሁሌም የሚታወሱ ናቸው፡፡

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close