በዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገው ኢቫን ፐርሲች የኢንተርን የልምምድ አካዳሚ ጥሎ ወጣ

ivan persic
በዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገው ኢቫን ፐርሲች የኢንተርን የልምምድ አካዳሚ ጥሎ ወጣ

በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገው ክሮሽያዊው ተጫዋች ኢቫን ፐርሲች የኢንተር ሚላንን የልምምድ አካዳሚ ጥሎ መውጣቱ ታውቋል፡፡በተጫዋቹ ዙሪያ ዩናይትዶችና ኢንተሮች አስካሁን ከስምምነት ሊደርሱ አልቻሉም፡፡

የሳንሴሮው ክለብ ለፐርሲች ዝውውር 49 ሚሊየን ፓውንድ የሚፈልግ ሲሆን በአንጻሩ ዩናይትዶች ያቀረቡት ዋጋ ከተቀመጠው ሂሳብ በጣም በተራራቀ መልኩ 26ሚሊየን ፓውንድ ነው፡፡ ፐርሲች ግን ኢንተር ሚላን በሱ ላይ በጫነው ዋጋ ደስተኛ ባለመሆኑ ነው የኢንተር ሚላንን የልምምድ አካዳሚ ጥሎ ወደ ክሮሽያ ያመራው እየተባለ ይገኛል፡፡ምንም እንኳን ክለቡ የተጫዋቹን ድርጊት በዛ መልኩ እንዳልሆነ በመግለፅ ሙሉ ለሙሉ ቢያስተባብልም፡፡

የ28 አመቱ ፐርሲች ወደ ኦልድተራፎርድ ማመራት በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈልግ ሲሆን ዝውውሩ እንዲፋጠንለትም ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የጣሊያኑ ክለብ አቋም ግን እስካሁን ድረስ ፈቅ ሊል አልቻለም፡፡ ዘግየት ብሎ በወጣ ዜናዎች ደግሞ ኢንተር ሚላኖች ዩናይትዶች ለኢቫን ፐርሲች ካቀረቡት 26 ሚሊየን ፓውንድ በተጨማሪ በኦልድትራፎርድ አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን አንቶኒ ማርሻል የዝውውሩ አካል እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ ሲሉ አትተዋል፡፡

READ  1 ሜትር ከ20 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ድመት በቁመቱ ክብረወሰን ሊይዝ ይችላል ተብሏል

NO COMMENTS