Connect with us

Art and Culture

መላከፍ ያመጣብኝ ቅሌት…

Published

on

መላከፍ ያመጣብኝ ቅሌት…

መላከፍ ያመጣብኝ ቅሌት…| አሳዬ ደርቤ በድሬ ትዩብ

‹‹ስጋ›› እወዳለሁ፡፡ ገንዘብ ካልቸገረኝና ጾም ካልሆነብኝ በስተቀር ያለምንም ማሳለስ አመቱን ሙሉ በጥሬውም ሆነ ተቀቅሎ ብበላው አይሰለቸኝም፡፡ የስጋ አፍቃሪ ከመሆኔ የተነሳ የምገዛበት ገንዘብ ባይኖረኝ እንኳን ጮማ የሰቀለ ሉካንዳ-ቤት አይቼ ዝም ብሎ ማለፍ አይሆንልኝም፡፡ ቢያንስ ዋጋውን ጠይቄና ‹‹አይቀንስም?›› እያልኩ መጨቃጨቄ አይቀሬ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሰው ቤት ውስጥ ገብቼ ልክ ቂጤ ወንበር እንደያዘ… ዐይኔ ሳሎናቸው ውስጥ የተሰቀለውን ፎቶና ጌጣጌጥ ችላ ብሎ ወደ ጓዳ በማምራት የተሰቀለ ቋንጣ ሲፈልግ አገኘዋለሁ፡፡

ይሄን አመሌን ለማስተካከል ብዙ ጥረት ያደረኩ ቢሆንም ቀበዝባዛ ዐይኔን የሞንዳላ ሴቶችን የኋላ ኪስና የሰው ቤት ቋንጣ እንዳይመለከት ማድረግ አልተሳካልኝም፡፡
.
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወር በፊት ምን አጋጠመኝ መሰላችሁ!
ምሳዬን ለመብላት በማሰብ ከቢሮ ወጥቼ የስጋ አምሮቴን የምወጣበት ምግብ ቤት እያፈላለኩ እንዳለ መንገድ ላይ ከአንዲት ቆንጆ ጋር ተገጣጠምኩኝ፡፡

የኮረዳዋ ውበት ለረዥም ሰዓት ስክሪን ላይ በማተኮሬ ምክንያት ከመደፍረስም አልፎ የሚያቃጥለኝን የዐይኔን ህመም ለተወሰነ ቅጽበት እንዳስረሳኝ አስታውሳለሁ፡፡

እናም ይችን ኮረዳ መራመድ እስኪያቅታት ድረስ መመልከቴ አልበቃኝ ብሎ፣ አልፋኝ ልትሄድ ስትል ጥበብ ጠራችኝና……‹‹ምን ዓይነት መልክ ነው- አስደማሚ ውበት›› በማለት የጀመርኩትን ግጥም ‹‹ዝም ብለህ አትሄድም- ቅሌታም አሮጊት!›› በሚል ስንኝ… ቤት ደፍታልኝና አንገቴን አስደፍታኝ ገላምጣኝ ሄደች፡፡
.
የሰደበችኝ ስድብ በቅጽበት ውስጥ የስጋ አምሮቴን ብቻ ሳይሆን ወጣትነቴንም ያጠፋ ነበር፡፡
ልጂቱ ከዐይኔ ስትሰወር በአጠገቤ ቁሞ ወዳየሁት መኪና በማምራት ከስፖኪዮው ላይ ተለግቼ ላፍታ ያህል ትኩር ብዬ አሮጊት ያስባለኝን ፊቴን እያየሁ እንዳለ… ከሹፌሩ ቦታ ላይ መቀመጡን ልብ ያላልኩት ጥላ-ቢስ ሰውዬ ‹‹ዝም በላት አያ! ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ!›› እያለ ይስቅብኝ ጀመር፡፡

READ  ገድሉ በተፈጸመበት ምሽት በታላቅ እርካታ የተጻፈ

በወረደብኝ የስድብ ዶፍ በመበሳጨቴ የተነሳ ምሳዬን ሳልበላ ወደ ቢሮ በመመለስ ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ የኖርኳቸውን ዓመታት ስቆጥራቸው ያገኘሁት ቁጥር ‹‹34›› የሚል ሆነ፡፡ ማቱሳላ በእዚህ እድሜ ላይ እያለ ጡት ከመጥባት ተላቆ ጡት ለማሸት አልደረሰም ነበር፡፡ ታዲያ ይሄ እድሜዬ እንዴት አሮጊት ሊያስብለለኝ ቻለ?

መልሱ ቀላል ነው፡፡ የያዝኩት ግንባር 34 አመት ብቻ ጸሐይና የሰው-ፊት የመታው አይመስልም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ያለ ጊዜው የረገፈ ጸጉሬ………፡፡
.
ልክ ከቢሮ እንደወጣሁ በቀጥታ ወደ ኮስሞቲክስ ሱቅ በማምራት እንደነ ሰይፉ በእርጅና ሳይሆን በእንክብካቤ ጉድለት ያለ ጊዜው የተመለጠ ጸጉሬን እንደ አዲስ እንዲያበቅል የሚያደርግ ‹‹ዶክተር-ምንትስ›› የሚባል ውድ ክሬም ገዛሁ፡፡ በፌስቡክ እንዳየኋቸው‹‹Before & After›› የሚሉ ማስታወቂያዎች ከሆነ… ይሄን ቅባት ለሶስት ወር በመጠቀማቸው የተነሳ ከመላጣነት ወደ ፍሪዚነት የተቀየሩ ሰዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ስለዚህ ጸጉሬን ድጋሜ የማፈረፍርበትን እድል ላገኝ እንጂ… እንኳን ሶስት ወር ቀርቶ ሶስት አመትም ብቀባው ሰለቸኝ አልልም›› እያልኩ በስጋ ፈንታ ቆስጣና ቃሪያ በፌስታል ቋጥሬ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ (ስጋ-በል መሆኔማ እርጅናን አመጣብኝ አይዴል?)

ከዚያ በኋላ ባሉ ቀናቶች… ቀን ቀን ከዚያች ልጅ ስድብ በላይ የሚያቃጥል ቃሪያና ሰላጣ እየቆረጠምኩ… ማታ ማታ ቅባቴን እየተቀባሁ የቀድሞው ጸጉሬ ወደ በፊት ይዞታው ተመልሶ የማፈረፍርበትን ቀን ስጠብቅ ከረምኩኝ፡፡

ባለፈው ታዲያ ከጸጉሬ ማደግ ጋር ተያይዞ ወሩን ሙሉ የተቀባሁት ቅባት ያመጣውን ለውጥ ለማየት ተሸሽጌው ከከረምኩት መስታወት ፊት ብቀርብ… እንኳን አዲስ ጸጉር ሊበቅል ቀርቶ በፊት የነበረውም ሸበቶ ቀላቅሎ አገኘሁት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አመጋገቤን ከስጋ ወደ አትክልት በማዛወሬ የተነሳ አገጬና አንገቴ መሃከል የሟሸሸ ቆዳ ተንጠልጥሏል፡፡

READ  ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

እናም ከመስታወቱ ፊት ለፊት የማየውን ምስሌን ትኩር ብዬ ስመለከተው ከቆዬሁ በኋላ ‹‹እፈረፍረዋለሁ›› ያልኩትን ጸጉሬን ከጺሜ ጋር አዳብዬ ሙልጭ አድርጌ በመላጨት ባንዱ ስብሰባ የተሰጠኝን ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነትን እንዋጋ!›› የሚል ኮፊያ ደፋሁበት፡፡ (በቀንድ ይሆን የምንዋጋው?)

በመጨረሻ ‹‹እንደ አሞራ›› ስጋ ፍለጋ ከቤቴ ከመውጣቴ በፊት መለስ ብዬ ገጽታዬን በመስታወቱ ስገመግመው ያች ቁሌታም ሳዱላ ‹‹ቅሌታም አሮጊት›› ያለችውን ሽማግሌ ለመሆን ከዘራ ብቻ ጎድሎኝ ነበረ፡፡(እምጵጽ) DIRETUBE

Art and Culture

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ

Published

on

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ዳንጉር ተራራ ይዞን ሊወጣ መተከል ዞን ገብቷል፡፡ በማንቡክ የነበረውን ቆይታ የጉብላክ ከተማን ድባብ እየተረከ ዳገቱን ይዞን ይወጣል፡፡ ስውሩ የተፈጥሮ መስህብ እስከ ዛሬስ የት ነበር? ብሎ ይጠይቃል፡፡ ቋንቋ አብሮ ለመኖር እንቅፋት የማይሆንበትን አኗኗርን እንዲህ ያስጎበኘናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ማንቦጓ የሚለው ቃል የመጣው ከጉምዝኛ ነው፡፡ መዋቢያ ማለት ነው ትርጉሙ፡፡ ማንቦጓ የሚለው ቃል ደግሞ ማንቡክን ወለደ፡፡ እኔ ማንቡክ ነኝ፡፡

በአሶሳ በኩል ነው የመጣሁት 379 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዤ እዚህ ደርሻለሁ፡፡ ያለሁባት ከተማ ስያሜዋን ያገኘችው ከማንቡክ ወንዝ ነው፡፡

የጉምዝ ሴቶች ወደ ወንዙ እየወረዱ ከሚዋቡበት፤ እናም ወንዙን ማንቦጓ ሲሉ መዋቢያ አሉት፡፡ ማንቡክ ከዚህ ቃል ተገኘ፡፡

ዳንጉር ነኝ፡፡ መተከል ገብቻለሁ፡፡ እዚህ ብዙ ተሸሽጎ የኖረ መስህብ አለ፡፡ እዚህ ምንም ያልተነገረለት ተአምር ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ የጠንካራ ገበሬዎች ከተማ በጠዋት ትነቃለች፡፡ ሲያቅላላ የታረደው በሬ ጸሐይ ስትወጣ ትዝታውም አይተርፍ፡፡ እንዲህ ናቸው ስጋ ቤቶቿ፤ ብዙው ሱቅ ከግብርና የተቆራኘ ነው፡፡ ብዙ ሰው የሚያወጋችሁ ምድር ምን ያህል ፍሬ እንደሰጠችው ነው፡፡ ብዙ ቋንቋ የሚሰማባት ከተማ ናት፡፡

የሰው ልጆች ከተማ፤ 838700 ሄክታር ቆዳ ስፋት ካለው ዳንጉር ወረዳ ብዙው ቆላማ ነው፡፡ ሦስት እጁ ቆላማ በሆነበት ምድር ደግሞ ሃያ በመቶ የሚሆን አስደናቂ ደጋ ምድር አለ፡፡ ማንቡክ ግን ሞቃታማ ናት፡፡

በ1962 ዓ.ም. ነበር ከተማ ሆና የተቆረቆረችው፡፡ ከከተማዋ ታሪክ ጋር ባለውለታ ሆነው ፊታውራሪ ኢያሱ ዘለቀ እና አቶ ተፈራ ሆሬ ስማቸው ጎልቶ ይነሳል፡፡ ማንቡክን በጠዋት ለቅቄ መንገድ ጀመርኩ፡፡ ቀጥዬ የምንደረደርባት ከተማ ጉብላክ ነች፡፡

READ  ከልማቱ ጋር ያደገው የህይወት ዘመናችን ልኬት

ጉብላክ ከማንቡክ በበለጠ ለግብርና ሕይወት ትቀርባለች፡፡ ሁለ ተገሯ ከምድር ፍሬ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ሰሊጥ በቆሎ ማሽላ ነው ጨዋታው፡፡ ትራክተሮች ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ የማሳ ላይ ውሎ አላደርስ ብሏቸው የነተበ ልብሳቸውን አላወልቅ ያሉ ብርቱዎች ወዛም ያደረጓት ከተማ ናት፡፡

ጉብላክ ሰባ በመቶ ምድሩ ሜዳማ ለሆነው ዳንጉር አንድ ማሳያ ናት፡፡ ሩቅ ድረስ በተዘረጉ የእርሻ ማሳዎች ተከባለች፡፡ ከጉብላክ እስከ ድባጉያ እጓዛለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በእግር ነው፡፡

ለብዙ ሰዓታት በእግር መጓዝ፤ ወደ ዳንጉር ተራራ አናት መውጣት፤ ከዳንጉር አናት ሆኖ ትይዩውን በላያን ማየት፤ እድሜ ጠገቡን ገዳም መጎብኘት፤ የደገኛውን ምድር እስክጠግበው መቆየት፡፡ ወደዚያው ለመሄድ መንገድ ላይ ነኝ፡፡ DireTube

Continue Reading

Art and Culture

“ህዳር ሲታጣን” በዚህ ዘመን….

Published

on

“ህዳር ሲታጣን” በዚህ ዘመን….

ከ100 ዓመታት በፊት በአገራችን በህዳር ወር ተከስቶ የበረው የኢንፍሉዌንዛ በሽታ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰው ህይወት እንዳጠፋ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

በዘመኑ የነበሩት ነግስታት የበሽታውን ስያሜ “የህዳር በሽታ” ብለው በሽታው በቀላሉ ሊስፋፋ የሚችለው ደግሞ ከጽዳት ጉድለት መሆኑን ለህዝብ በማስገንዘብ ነዋሪዎች የመንደራቸውን ቆሻሻ እያሰባሰቡ በማቃጠል በሽታውን ለመከላከል እንዲዘምት በአዋጅ አዘዙ።

ይህ የቆሻሻ ማቃጠልና በጭስ የማጠኑ ልምድ በጊዜው የነበረውን በሽታ በማጥፋት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ቢሆንም አሁን የምናቃጥላቸው ፌስታልና የተለያዩ ኬሚካል ያላቸው ቁሶች የከባቢ ሙቀት መጨመርን የሚያባብስ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

በዘንድሮው ህዳር 12 ማለዳም አዲስ አበባ በግራጫማ ጭስ ታፍና ተስተውላለች፡፡

በጉዳዩ ላይ ያለዎት ሀሳብ አስተያየት ያካፍሉን!!  ebc

READ  የአፍሪካ ዋንጫና ፍትሐዊ ምርጫ
Continue Reading

Art and Culture

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት

Published

on

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት፤ የኦቦ ለማ መገርሳ ካቢኔ ሩቅ አሳቢነት እና የኦሮሞ ባህል ጥላቻን የመጥላት እሴት | ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኦዳ ትራንስፖርት የብስራት ጉባኤ ላይ ከፊት ታይተዋል፡፡ ጎናቸው ያሉት ያሳደጓቸው የፖለቲካ ልጆች ናቸው፡፡ በርሃ ሳሉ አይተዋወቁም፡፡ የበርሃ ጓዱን ለእግዜሃር ሰላምታ ዓይኑን አያሳየኝ በሚል የፖለቲካ ሜዳ ሌላ ዓይነት ጨዋታ ማየታችን አጃኢብ አስብሎን ከርሟል፡፡

እውነቱ ግን ኦሮሚያን የሚመሯት የኦሮሞ ልጆች መሆናቸው ነው፡፡ አንድ መሪ የሚመራው ሕዝብ አብራክ ክፋይ ሲሆን ባህሉን ያከብራል፡፡ እንደ ባህሉ ይኖራል፡፡ ከሀገር ወግ አያፈነግጥም፡፡

እኔ በኦዳ ትራንስፖርት ጉባኤ ላይ ነጋሶን ከነ ለማ ጋር አብሬ ሳያቸው የገባኝ የገዳ ሥርዓት እሴት ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ነው፡፡ በሀሳብ ልትለያይ ትችላለህ ግን ጠላት አይደለህም፡፡

ኦሮሚያን በመምራት በኩል የኦሮሞን ባህል አውቆ እንደ ኦሮሞ በመምራት ረገድ የተሳካላቸው መሪ አባዱላ ነበሩ፡፡ ግን እሳቸው በዚያን ወቅት ብቻቸውን ናቸው፡፡ ዛሬ ድፍን ካቢኔው ሊባል በሚችል መልኩ የአባቶቹን ወግ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የአባቶቹ ወግ ደግሞ ጥላቻን ይጠላል፡፡

እናም እንደ ገዳ ባህል ወንድም ወንድሙን አይጠላም፡፡ ሀሳቡን ስለ ጠላ ወንድሙን አያሳድም፡፡ የዶክተር ነጋሶ ከፊት መምጣት ምስጢሩ ይሄ ይመስለኛል፡፡ ያም ሆኖ በጥላቻ ፖለቲካ መጠጥ የሰከርን ስለሆነ በሆነው ነገር ደንግጠናል፡፡ ተገርመን አላበቃንም፤ አሰላስለን አልጨረስንም፡፡

ዶክተሩ በምን አግባብ ዳግም በኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ እንደ አንድ ኦሮሞ በጉባኤ እንግዳ ሆነው ይታደማሉ ብለን እናስብ ነበር፡፡ አዲስ ትውልድ መጣና አደረገው፡፡ በዶክተሩ ቋንቋ ስንጠቀም፤ መንግስቱ ሃይለማርያምን የማይመስል አዲስ ትውልድ፡፡ ይሄ ሌሎቹም ጋር ቢለመድ መልካም ነበር፡፡ ግን ውሃ መውቀጥ ስለሆነ አልናፍቀውም፡፡ ኦሮሚያ ይቀጥል ዘንድ ግን እመኛለሁ፡፡

READ  የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት 7 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳየ

ኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ብዙ ዓመታት ቀድማ የጀመረች ሀገር ናት ብለን ስንሟገት ማስረጃችን ገዳ ነው፡፡ ሀሳብ እንጂ ሰው እንደማይገፋ ማሳያ የሆነው ይህ ባህል የገዳ ስርዓት እሴት የፈጠረው ነው፡፡ እናም ደስ ያሰኛል፡፡

ኦህዴድ ቀጥሎ ስለ ዶክተሩ ህልውና ያስብበት፡፡ ተገፍተዋል፡፡ እንደ አንድ ተራ ሀገር ዘራፊ ካድሬ እንኳን የሚታዩ አይደሉም፡፡ ርዕሰ ብሔሩ በብዙ ችግሮች ውስጥ ናቸው፡፡

ትናንትናቸውን ማሰብ ባይቻል እንኳን ጀርመንን ከመሰለች ሀገር ከሞቀ ህይወት የሰው ሀገር ሰው ጭምር ይዘው ሀገር አለኝ ብለው የመጡት የኦሮሞን ህዝብ ለማገልገል እንጂ የጀመሩት ትምህርት አላልቅ ብሏቸው አሊያም፤ ከዚች ሀገር ስራ ፍለጋ አይደለምና፤ አርቀን በማሰብ ትውልድ የሚኮራበት ስራ እንስራ፡፡ DireTube

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!