Connect with us

Sport

ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች………

Juliana

Published

on

1-የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በመጨረሻ ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ቲማዩ ባካዮኮን ጉዳይ ቋጭቷል፡፡ በዛሬው እለትም ቼልሲ ዝውውሩን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትዶች ባካዮኮን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን በመጨረሻ ግን ቼልሲ ተጫዋቹን በ38.8 ሚሊየን ፓውንድ የግሉ ማድረጉ ታውቋል፡፡ አጠቀላይ ሂደቱንም ለመጨረስ ባካዮኮ ወደ ለንደን ማምራቱ ታውቋል፡፡ 2-ሊቨርፑሎች ናቢ ኬታን ከሌፕዚግ ለመግዛት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቢቀጥልም የጀርመኑ ክለብ ግን ተጫዋቹ እንደማይሸጥ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ የርገን ክሎፕ ለብዙ ቀናት ተጫዋቹን ለማግኘት የተለያዩ የድርድር ሂደቶችን ቢጠቀሙም እስካሁን ቀና ምላሽ ሊመለስላቸው አልቻለም፡፡በዝውውር መስኮቱ ቀዮቹ ከሌሎች ታላላቅ ክለቦች ባነሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ይህም የክለቡን ደጋፊዎች ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ታውቋል፡፡ 3-ኤዲን ሀዛርድ በዘንድሮ የውድድር ዘመን በሪያል ማድሪድ ከሚፈለጉ ቀንደኛ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ማድሪዶችም አንዳንድ የዝውውር ሂደቶችን ቢጀምሩም ተጫዋቹ ግን በድርጊታቸው ደስተኛ የሆነ አይመስልም፡፡በቼልሲ ለተጨማሪ አመት መቆየት እንደሚፈልግ በማሳሰብ ማድሪዶች ከዕቅዳቸው እንዲያወጡት መግለፁ ታውቋል፡፡ ይህን አቋሙንም ለማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን በስልክ በሚገባ አስረድቶታል አአ፡፡ 4-አንደሪያ ቤሎቲ በቶሪኖ በ38 ጨዋታዎች 28 ጎሎችን ካስቀጠረ በኋላ በተለያዩ ክለቦች በተለይ በማነቸስተር ዩናይትድ ተፈላጊ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል፡፡ጆሴ ሞሪንሆም ቤሎቲን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ነገር ግን ከቶሪኖ ጋር በዋጋ መስማማት ባለመቻላቸው የዝውውር ሂደቱ በክለቦቹ መሀከል ሊቋረጥ ችሏል፡፡አሁን ደግሞ ቼልሲ ለአንደሪያ ቤሎቲ 89 ሚሊየን ፓውንድ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ ኢንዲፔንደንት እንዳስነበበው ቼልሲዎች ከቶሪኖ ጋር ድርድር የሚጀምሩ ከሆነ ያቀረቡት ሂሳብ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 5-የአልቫሮ ሞራታ ጉዳይ እስካሁን የለየለት አይመስልም፡፡ ጆሴ ሞሪንሆ የተጫዋቹ አድናቂ በመሆናቸው እስካሁን በሞራታ ላይ ያላቸው ፍላጎት አልተቀዛቀዘም፡፡ ቼልሲም የስፔናዊው ቀንደኛ ፈላጊ ክለብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹ ክህሎት እና ብቃት እያሳሳቸው በመሆኑ ለዝውውሩ እንቅፋት እየሆኑ እንደሆነ የስፔን ጋዜጦች በስፋት ምክንያትበማቅረብ እያስነበቡ ይገኛሉ፡፡አሁን ደግሞ ዩናይትድ ለአልቫሮ ሞራታ በዓመት 10 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ በማቅረብ ዝውውሩን ለማሳካት እንዳሰቡ ታውቋል፡፡

1-የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በመጨረሻ ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ቲማዩ ባካዮኮን ጉዳይ ቋጭቷል፡፡በዛሬው እለትም ቼልሲ ዝውውሩን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትዶች ባካዮኮን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን በመጨረሻ ግን ቼልሲ ተጫዋቹን በ38.8 ሚሊየን ፓውንድ የግሉ ማድረጉ ታውቋል፡፡ አጠቀላይ ሂደቱንም ለመጨረስ ባካዮኮ ወደ ለንደን ማምራቱ ታውቋል፡፡

2-ሊቨርፑሎች ናቢ ኬታን ከሌፕዚግ ለመግዛት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቢቀጥልም የጀርመኑ ክለብ ግን ተጫዋቹ እንደማይሸጥ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ የርገን ክሎፕ ለብዙ ቀናት ተጫዋቹን ለማግኘት የተለያዩ የድርድር ሂደቶችን ቢጠቀሙም እስካሁን ቀና ምላሽ ሊመለስላቸው አልቻለም፡፡በዝውውር መስኮቱ ቀዮቹ ከሌሎች ታላላቅ ክለቦች ባነሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ይህም የክለቡን ደጋፊዎች ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ታውቋል፡፡

3-ኤዲን ሀዛርድ በዘንድሮ የውድድር ዘመን በሪያል ማድሪድ ከሚፈለጉ ቀንደኛ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ማድሪዶችም አንዳንድ የዝውውር ሂደቶችን ቢጀምሩም ተጫዋቹ ግን በድርጊታቸው ደስተኛ የሆነ አይመስልም፡፡በቼልሲ ለተጨማሪ አመት መቆየት እንደሚፈልግ በማሳሰብ ማድሪዶች ከዕቅዳቸው እንዲያወጡት መግለፁ ታውቋል፡፡ ይህን አቋሙንም ለማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን በስልክ በሚገባ አስረድቶታል አአ፡፡

4-አንደሪያ ቤሎቲ በቶሪኖ በ38 ጨዋታዎች 28 ጎሎችን ካስቀጠረ በኋላ በተለያዩ ክለቦች በተለይ በማነቸስተር ዩናይትድ ተፈላጊ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል፡፡ጆሴ ሞሪንሆም ቤሎቲን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ነገር ግን ከቶሪኖ ጋር በዋጋ መስማማት ባለመቻላቸው የዝውውር ሂደቱ በክለቦቹ መሀከል ሊቋረጥ ችሏል፡፡አሁን ደግሞ ቼልሲ ለአንደሪያ ቤሎቲ 89 ሚሊየን ፓውንድ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ ኢንዲፔንደንት እንዳስነበበው ቼልሲዎች ከቶሪኖ ጋር ድርድር የሚጀምሩ ከሆነ ያቀረቡት ሂሳብ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

5-የአልቫሮ ሞራታ ጉዳይ እስካሁን የለየለት አይመስልም፡፡ ጆሴ ሞሪንሆ የተጫዋቹ አድናቂ በመሆናቸው እስካሁን በሞራታ ላይ ያላቸው ፍላጎት አልተቀዛቀዘም፡፡ ቼልሲም የስፔናዊው ቀንደኛ ፈላጊ ክለብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹ ክህሎት እና ብቃት እያሳሳቸው በመሆኑ ለዝውውሩ እንቅፋት እየሆኑ እንደሆነ የስፔን ጋዜጦች በስፋት ምክንያትበማቅረብ እያስነበቡ ይገኛሉ፡፡አሁን ደግሞ ዩናይትድ ለአልቫሮ ሞራታ በዓመት 10 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ በማቅረብ ዝውውሩን ለማሳካት እንዳሰቡ ታውቋል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close