በአንድ ተከታታይ የቴሌቨዥን ድራማ፣ ለአንድ ገጸ-ባሕሪ፤ አራት ተዋነያን

በአንድ ተከታታይ የቴሌቨዥን ድራማ፣ ለአንድ ገጸ-ባሕሪ፤ አራት ተዋነያን
የልጆቻቸውን ሞት ሰምተው ቲያትር ተውነው ጨርሰው የሚወርዱ ጥበበኞች ነበሩን፡፡ ቤተሰብ ቀብረው ከሰዓት መድረክ ላይ የሚቆሙ ድንቅ ተዋነያን ያለፉበት ኢንዱስትሪ ነው፡፡

በአንድ ተከታታይ የቴሌቨዥን ድራማ፣ ለአንድ ገጸ-ባሕሪ፤ አራት ተዋነያን | ከስናፍቅሽ አዲስ፤

ወደ ኋላ እየሄድን ነው? መቼም ወደ ፊት ከጀርባችን የለም፡፡ የቴሌቨዥን ድራማ ተመልካች አይደለሁም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ስመለከት እከርምና አንድ ቀን አቋርጬ በሌላ ቀን ሌላኛውን ክፍል ስቀጥል የማይገባኝ ነገር ይፈጠራል፡፡ እኔ የማውቃት ተዋናይ ተቀይራ አዲስ ተዋናይ ያቺን ሆና መተወን ትጀምራለች፡፡ እኛ ሀገር መተካካቱ የሰራው በእነኚህ ድራማ ጀምረው መጨረስ ባቃታቸው ተዋነያን ብቻ ይመስለኛል፡፡

ነገሩን ስቀን እንለፍበት ካለን ቀላል ይመስለናል ግን አይደለም፤ የትወና ኢንዱስትሪያችን ሥነ-ምግባር አልባነት ማሳያ ነው፡፡ የልጆቻቸውን ሞት ሰምተው ቲያትር ተውነው ጨርሰው የሚወርዱ ጥበበኞች ነበሩን፡፡ ቤተሰብ ቀብረው ከሰዓት መድረክ ላይ የሚቆሙ ድንቅ ተዋነያን ያለፉበት ኢንዱስትሪ ነው፡፡

ዛሬ ግን…… የችግሩ መንስኤ የተዋነያኖቹ አመጣጥ ይመስለኛል፡፡ ገንዘብ ያለው ፕሮዲዩሰር ሲሆን መልክ ያለው መተወን ጀመረ፡፡ የቴሌቨዥን ድራማዎቻችን ጥሩ ባል የማምጫ መንገዶች ተደርገው ተወሰዱ እና አምስት ክፍል ሳትተውን ባህር ማዶ ያያት አዲስ ባል ወደድሁኝ ሲል ስድስተኛው ክፍል በሌላ እሷን መሰል ተዋናይ ተተክቶ ይቀጥላል፡፡

ለተመላካቹ ክብር መጨነቅ ሌላ ቅንጦት ነው፡፡ ማዘን የለም፤ በቀጭኗ ተዋናይ ምትክ የሷን አምስት የምታህል ወፍራም ተክቶ፣ አልያም በተቃራኒው ይቀጥላል፡፡

ቴሌቨዥኖቻችን የብዛታቸውን ያክል ለቁጥር የሚታክቱ ተከታታይ ድራማዎችን በየራሳቸው ያቀርቡልናል፡፡ አንዳቸውም ግን በቀጣዩ ሳምንት ስለማሳየታቸው እርግጠኞች አይደሉም፡፡ አቋርጦ የሚሄደው አልያም አኩርፎ ቤቴ እቀመጣለሁ የሚለው ተዋናይ እጅ ነው ተስፋቸው፡፡ ፕሮዲዩሰሮችም ቢሆኑ የጀመሩትን ድራማ ስለመጨረሳቸው እርግጠኞች አይደሉም፡፡

የምናየው ይሄንኑ ነውና፤ የቴሌቨዥን ድራማዎች አስቀድሞ ጥንቅቅ ብለው ያለመቀረጽ የራሱ ችግር እየፈጠረ መጥቷል፡፡ አንዳንድ ድራማዎች ላይ ነውጠኛ ሆነው ያስቸገሩ ተዋነያን የሚወክሉትን ገጸ ባህሪ ገድሎ መገላገል አዲስ የኢትዮጵያ ጥበብ ስልት ሆኗል፡፡

READ  ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዳያስፖራው የባንክና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ እየቀረቡ ነው ተባለ

ከታዘነ ደግሞ ገጸ ባህሪዋን ወደ ውጪ ሀገር መላክ፡፡ እናም በዚህ ሳቢያ ድራማዎቻችንን ስከታተል ፈተና ሆኖብኝ ስቸገር ብተወውስ አልኩ፡፡ አንቺ ተውሺው አልተውሺው አትበሉኝ እንጂ ችግሩ አሳሳቢ የሙያው የሥነ-ምግባር ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል፡፡DIRETUBE

 

NO COMMENTS