የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባኤው የአህጉሪቱ ጉዳዮች ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን፤ ከጸጥታ እና ደህንነት አንጻር የሶማሊያና የሊቢያ ወቅታዊ ሁኔታ አጀንዳ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ነገ እና ከነገ በስቲያ የህብረቱ አባል ሀገራት ቋሚ ተወካዮች ስብሰባ የሚያደርጉ ይሆናል።

በቀጣይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የአስፈጻሚዎች ስብሰባ ተደርጎ በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ስብሰባ የሚካሄድ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀድመው በሰጡት መግለጫ ለጉባኤው የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ጊዜ የከተማዋ ነዋሪዎች በተለመደ እንግዳ ተቀባይነት እንግዶቹን ተቀብለው እንዲያሰተናግዱም ጥሪ ቀርቧል- ኤፍ.ቢ.ሲ

READ  የአልሸባብ ቡድን በአንድ የኬንያን ወታደራዊ ምድብ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰማ

NO COMMENTS