የታገደው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሊጀመር ነው

0
የታገደው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሊጀመር ነው
የቀድሞ አዋጅ ከመታገዱ በፊት በሀገሪቱ ከ400 ያላነሱ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የነበሩ ሲሆን ነባሮቹን ጨምሮ አዲስ ወደዘርፉ የሚገቡ ባለሃብቶች በአዲሱ አዋጅ መሠረት አዲሱን መስፈርት አሟልተው ፈቃድ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያዊያን የውጭ አገር ሥራ ስምሪትን የሚመለከተው አዲሱ አዋጅ በቅርቡ ወደተግባር እንደሚገባ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በተሌ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያዊያንን መብት አላስጠበቀም በሚል ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረው አዋጅ ቁጥር 632/2001 በመንግሥት ውሳኔ እንዲታገድ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ የታገደው አዋጅ ክፍተቶቹ በጥናት ተለይተው ከታወቁና በሚመለከታቸው አካላት አስተያየት ከዳበረ በሃላ ረቅቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ባለፈው ዓመት ፓርላማው አጽድቆታል፡፡

አሁን በሥራ ላይ ያለው አዲሱ አዋጅ ቀደም ሲል የታዩትን ክፍተቶች መድፈን ያስቻለ ነው ተብሎለታል፡፡ በአዋጁ መሠረት የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተገቢውን ዕውቀትና ልምድ እንዲኖራቸው፣ ከቀድሞው ሻል ያለ የገንዘብ ዋስትና እንዲያሲዙ ያስገድዳል፡፡

አሠሪዎች በኤጀንሲ በኩል ካልሆነ በስተቀር ቀጥታ ቅጥር ማድረግ አይችሉም፡፡ ሠራተኞች ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቅ እንዲሁም የጤና ምርመራ ማድረግ፣ ከመሄዳቸው በፊት መሠረታዊ ሥልጠና መውሰድ አለባቸው፡፡ በመንግሥት በኩል ሠራተኞች የሚሄዱባቸው አገራት ጋር ሀገሪቱ የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት ማድረግ አስገዳጅ ሆኖ ተቀምጦአል፡፡

የቀድሞ አዋጅ ከመታገዱ በፊት በሀገሪቱ ከ400 ያላነሱ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የነበሩ ሲሆን ነባሮቹን ጨምሮ አዲስ ወደዘርፉ የሚገቡ ባለሃብቶች በአዲሱ አዋጅ መሠረት አዲሱን መስፈርት አሟልተው ፈቃድ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡ DIRETUBE

READ  በጎንደር ከተማ በሁለት ቢሊየን ብር የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ሊገነባ ነው

NO COMMENTS