ሳዑዲ ያወጣችው የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቢቀሩትም የተመላሾች ቁጥር ግን አናሳ ነው 

0
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የስራና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ከሀገሪቱ እንዲወጡ
ዜጎች እንግልት ሳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ በሚሰሩ ስራዎች፥ የተመላሾች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ቢመጣም ከሚገመተው መጠን አኳያ አነስተኛ ነው።

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የስራና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ከሀገሪቱ እንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 8 ቀናት ብቻ ቀርተውታል

ኤፍቢሲ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያነጋገራቸው ከሳዑዲ ተመላሾች የምህረት አዋጁ ሳይጠናቀቅ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፥ ቀነ ገደቡ እስከሚያልቅ ቢቆዩ ግን ሊደርስ የሚችለው አስከፊ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ዜጎች እንግልት ሳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ በሚሰሩ ስራዎች፥ የተመላሾች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ቢመጣም ከሚገመተው መጠን አኳያ አነስተኛ ነው።

የምህረት አዋጁ ሳይጠናቀቅ አዲስ አበባ የገቡ ተመላሾች እንደሚናገሩት፥ አዋጁ ይራዘማል የሚል ዋጋ የሚያስከፍል አስተሳሰብ፣ የደላሎች ጉትጎታ፣ የተወሰኑ የሳዑዲ ዜጎች ያልተጨበጠ ማባበያ፥ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ከሚገፋፉ ምክንያቶች ወስጥ ዋናዎቹ ናቸው።

አሁን በሀገራቸው የተገኙት ኢትዮጵያውያን ያለቻቸውን ጥቂት ገንዘብ እና ሙያ ተጠቅመው፥ መንግስት በሚያመቻቸው የስራ እድል ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ተስፋ መሰነቃቸውን ይናገራሉ።

የኦሮሚያና አማራ ክልል የስራ ሃላፊዎችም ከየክልሎቻቸው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በህገ ወጥ መንገድ የተጓዙት ዜጎች፥ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንዲመለሱ ለማድረግ ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ የተቀናጀ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ክልሎቹ በአሁኑ ወቅት እየሰሩት ያለው ስራ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ብቻ ሳይሆን፥ ተመልሰውም የሚቋቋሙበትን መንገድ ላይ ያተኮረ ጭምር ነው።

የኦሮሚያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ ጅሎ፥ እስካሁን የተመለሱት ዜጎች ቁጥር ከሚታሰበው አኳያ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረው፥ ለተመላሾች በክልሉ ካሉ ወጣቶች ጋር የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው፥ የሳዑዲ ተመላሾችን በክልሉ ካለው የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ጋር አስተሳስሮ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።

READ  የድሬደዋ ወጣቶች በአፋጣኝ ወደ ስራ መግባት እንደሚፈልጉ ገለፁ

እርሳቸው እንደሚሉት የክልሉ ቴክኒክ ሙያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ፥ ይህን ስራ የማስተባበር እና የማቀናጀት ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

ሚኒስቴሩ ሳዑዲ ያወጣችው የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ 8 ቀናት የቀሩት ሲሆን፥ በእነዚህ ቀናት ዜጎችን የማስመለሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። fanabc

NO COMMENTS