Connect with us

Entertainment

‹‹አስምና ጊኒ-ዋርም››

Published

on

አስምና ጊኒ-ዋርም

‹‹አስምና ጊኒ-ዋርም›› | አሳዬ ደርቤ @ድሬ-ትዩብ

ገና ክረምቱ ሳይገባ የአዲስ አበባ አየር ከመንግስት ጋር ህብረት ፈጥሮ ያፍነኝ ይዟል፡፡

አፈናው የሚጀምረኝ ቀኑ መሽቶ እራት ተበልቶ ሲጠናቀቅ ነው፡፡

እናም ሰው ሁሉ ወደ መኝታ ቤቱ በሚገባበት ሰዓት እኔ ‹‹ሲርርርር›› የሚል ትንፋሼን እያሰማሁና ጋቢዬን እያጣፋሁ ወደ ደጅ በማምራት ኮሪደር ላይ ተቀምጨ ‹‹በመንግስት ከመታፈንና በአስም ከመታፈን የትኛው ይሻላል?›› እያልኩ ሳሰላስል ሌሊቱ ይነጋል፡፡

ደጅ ላይ ማደሬን የተመለከተው የኮንዶሚንዬማችን የጥበቃ ሰራተኛ በብሎኩ ፈንታ ነቅቶ የሚጠብቀው የእኔን መታፈን ሁኗል፡፡ ልክ ጋቢዬን ለብሼ ወደ ደጅ ስወጣ ከተቀመጠበት በደስታ እየዘለለ ወደ እኔ ይመጣና ‹‹እንደው እስከመቼ ይሆን እንዲህ ታፍነህ ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ የምትገፋው?›› ከሚል ጥያቄ ጋር የኮንዶሚንዬሙን የጥበቃ ስራ ለእኔ አስረክቦ ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡

ዛሬም እንደተለመደው በመታፈኔ የተነሳ ደጅ ላይ ተቀምጨ እንደ ልቤ የምትነፍስበትንና ሌባ የሚመጣትን ሰዓት ነቅቼ እየጠበኩኝ እንዳለ… እያንዳንዷን ሌሊት ከተለያዩ ሴቶች ጋር ለማሳለፍ ቀበቶውን አጥብቆ የተነሳው ወንደ-ላጤ የአንዷን ኮረዳ ወገብ አቅፎ እየተንኳተተ ሲመጣ አየሁት፡፡ መቼም እንደዚህ ወንደላጤ የአዲስ አበባን ሴት የጨፈጨፈ ሰው በከተማው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ የሰፈራችንን ሴቶች በማዋለዱና በማስወረዱ የሚታወቀው የህክምና ባለሙያው ጋሽ ወልዱ እንኳን የእሱን ያህል ሴቶች ጭን ውስጥ የመግባት እድሉን ያገኘ አይመስለኝም፡፡ ዘወትር ምሽት ወደ ቤቱ ሲመጣ በቀኝ እጁ ‹‹የሸዋ ዳቦና የለውዝ ቅቤ›› የያዘ ፔስታል ሳያንጠላጥል… የግራ እጁን የሴት ወገብ ላይ ጣል ሳያደርግ ይታያል ማለት ዘበት ነው፡፡

በግሌ የዚህን ውርጋጥ ተግባር ከመጠየፌ የተነሳ ልጁን ከብሎካችን ላይ ለማባረር ያላደረኩት ነገር አልነበረም፡፡ ለምሳሌ የኮንዶሚንዬሙ ማህበረሰብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ ‹‹በየሌሊቱ ከሚገትታቸው ምንነታቸው ከማይታወቁ ሴቶች መሃከል አንዷ ንብረታችንን መንትፋ ብትሄድ የማን ያለህ ይባላል?›› በማለት ስሞታዬን ባቀርብም ብሎኩ ላይ የሚኖሩት ሴቴ-ላጤዎች ‹‹በገዛ ቤቱ የፈለገውን ቢያደርግ ማን ከልካይ አለበት?›› በማለት ስለተቃወሙኝ ጩኸቴ ሳይሰማ ቀረ፡፡

READ  የአረብ አገር ባርነት = የእኛ አገር ገረድ ሲደላት

በጊዜው ከተቃወሙኝ ሴቶች መሃከል ሚስቴም ተቀላቅላ ስለነበረ የተቃውሟውን መነሻ ለማወቅ ማእከላዊ ከሚደረግ ድብደባ በከፋ መልኩ ከባድ አካላዊ ጥቃት ገላዋ ላይ መፈጸሜን አስታውሳለሁ፡፡

ወንደ-ላጤው እጇን እየሰባ የሚገትታትን ሴት አርፎ ይዞ እንደመግባት እኔ የተቀመጥኩበት ብሎክ ላይ ሲደርስ መጠጥ ባወላከፈው አንደበቱ ‹‹አንቱ ሰውዬ ይሄን አስምዎን ቶሎ ካልታከሙት አንድ ቀን አፍኖ እንዳይገልዎትና ሚስትዎ ብቻዋን እንዳትቀር እፈራለሁ›› በማለት ስጋትና ትንቢት የቀላቀለ ንግግር ቀባጥሮብኝ ተፈተለከ፡፡ (መቼም አስሜ ሲለቀኝ ቀድሜ የምስበው ኦክስጂን ሳይሆን የእዚህን ሙልፍጥ የሸሚዝ ኮሌታ መሆን አለበት፡፡)

በልጁ ንግግር ተበሳጭቼ እየተንጎራደድኩ እንዳለ መኪና እንደ ልብስ በመቀያየር የሚታወቀው ጋሽ ተክሉ ‹‹ሃዩንዳ›› መኪናውን ፓርኪንግ ላይ አቁሞ ወዳለሁበት መጣ፡፡ ጋሽ ሃይሉ ወደዚህ ብሎክ የሚመጣው ቤት ገዝቶ ያስቀመጣትን ቅምጡን መጎብኘት ሲፈልግ ብቻ ነው፡፡

‹‹አቶ አሳዬ እንዴት አመሸህ?››

‹‹ሲርርርር….››

‹‹ዛሬም ይሄ አስም አፈነህ ማለት ነው››

‹‹ሲርርር….››

‹‹ይሄን ሽንት-ቤቱና መኖሪያ-ቤቱ የተቀላቀለ ኮንዶሚንዬም ለቀህ ለምን ቪላ ነገር አትከራይም?››

‹‹ሲርርር….›› (እዚህ ላይ ከአስሜ በተጨማሪ ሳቄም ሲያፍነኝ ይታወቀኛል፡፡)

ከረዥም ጥበቃ በኋላ የንብ አርማ የተሳለበትን የቁልፉን ማቀፊያ እየወዘወዘ ‹‹ማር ብላበት!›› ሲለኝ ቆይቶ ወደ ቅምጡ አመራ፡፡

እንኳንም ሄደልኝ፡፡ (በጣቱ የሚያፍነኝን ይዞ ስለሚያድነኝ ነገር ማውራት ምን ይሉታል? ደግሞስ ‹‹አፋኝ›› ከመቼ ወዲህ ነው ‹‹አዳኝ›› የሆነው?)

.

በነገራችን ላይ እሱ ባይነግረኝም ማር መብላቱ የሚያድነኝ አልሆነም እንጂ ለረዥም ጊዜ ስሞክረው የኖርኩት ነው፡፡

እንደውም ‹‹ከአስም ያድነኛል›› ብዬ በማር ዋጋ እየገዛሁ የምበላው ስኳር ከህመሜ ሊያሽረኝ ቀርቶ እንደ ዳይኖሰር ከምድረ-ገጽ ጠፍቶ የነበረውን የወስፋት ዝርያ አንጀቴ ውስጥ በመፍጠሩ የተነሳ የደረሰብኝን ነገር ላጫውታችሁ፡፡

READ  የአፍሪካ ዋንጫና ፍትሐዊ ምርጫ

ህመሙ እንደጀማመረኝ አካባቢ ይሄንን የአንጀት ጥገኛ ለማጥፋት አስቤ ወደ መሸታ-ቤት በሄድኩበት ሰዓት ‹‹ማሩ›› የሚባል የቅርብ ጓደኛዬን አገኝና ‹‹ምን እግር ጣለህ?›› ሲለኝ ስለ ህመሜ ሹክ እለዋለሁ፡፡

እናም ይሄን ወሬ ካወራሁ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ገዋን ባጠለቁ ሀኪሞች ተከብቤ አንቡላንስ ውስጥ ተገኘሁ፡፡

‹‹ምንድን ነው እየሆነ ያለው?›› ብዬ ስጠይቅ ቅድም ስለ ህመሜ ያወራሁት ጓደኛዬ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ ‹‹ጠቁሜህ ነው›› አለኝ፡፡

‹‹ምን ብለህ?››

‹‹Gunie worm አለበት ብዬ! ደግሞም ፈጣሪ እረድቶን ህመምህ እሱ ይሁን እንጂ ጤና ሚኒስቴር የሚሸልመኝን ሽልማት ካንተ ተለይቼ የምበላ ሰው አይደለሁም›› እያለኝ እንዳለ አንቡላንሱ መጓዝ ጀመረ፡፡ (ለካስ በወቅቱ ‹‹ጤና ሚኒስቴር›› የሚባል ተቋም አሜሪካ አሸባሪዎችን ለመያዝ የምትጠቀምበትን ዘዴ በመጠቀም…. ይሄ ትል የታየበትን ሰው ለጠቆመ የሆነ ሺህ ብር እሸልማለሁ›› በማለት በቴሌቪዥን ሲያስነግር ከርሞ ኑሯል፡፡)

በጣም የሚገርማችሁ ነገር ከሆስፒታል ነጻ ሆኜ ከወጣሁ በኋላም ይሄ ቀባጣሪ ጓደኛዬ መሸታ ቤት ተቀምጦ ‹‹ባያውቁት ነው እንጂ… በሽታውስ እኔ ያልኩት ነበረ›› እያለ ሲቀባጥር መክረሙ ነው፡፡

እናም ለአስም እያልኩ የምወስደው ማር ለጊኒ-ዋርም ካበቃኝ ‹‹ማሩ›› የሚባል ሰውና ‹‹ማር›› የሚባል ስኳር ተጠይፌ ቀረሁ እላችኋለሁ፡፡

DIRETUBE

Entertainment

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት | ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት

Published

on

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት | ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ደባርቅ ነው፡፡ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት በዓል ላይ ታድሞ የዝግጅቱን ድባብ እየተረከልን ነው፡፡ ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት ሲል የጠዋቱን ውሎ እንዲህ ይነግረናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ከእነኚህ ረዣዥም ተራሮች፣ ሰማይ የነኩ ምድሮች ወዲህ ያለችዋ ከተማ ዛሬ ደምቃለች፡፡ ደባርቅ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በብሔራዊ ፓርክነት የተመዘገበበትን 50ኛ ዓመት እያከበረች ነው፡፡

ዩኔስኮ ቅርሱን ከዓለም ቅርስነት እስርዘዋለሁ ብሎ ለብዝኃ-ሕይወቱ ጥበቃ ዋስትና እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥያቄ ስሜኖች መስዕዋትነት ከፍለው አሳክተውታል፡፡

ስሜን በስሜኖች ያሳካውን ህልም ከ50ኛ ዓመቱ ጋር አብሮ እያጣጣመው ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክብር እንግድነት የተገኙበት ይህ በዓል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ ክብርት ሚኒስትር ደኤታዋ፣ የክልልና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች፣ ስሜንን በመታደግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን የቆሙ ሀገራት አምባሳደሮች ታድመውበታል፡፡

የስሜን ብሔራዊ ፓርክን ታሪክ እና የስሜነኞችን ወግ በሚያሳየው አውደ ርዕይ የተከፈተው የዛሬው ዝግጅት በጠዋት ፈረቃው መርሐ ግብር በጎንደሩ ፋሲለደስ ኪነት ቡድን ታጅቦ የደመቀ ነው፡፡

“ምንኛ ደግ ነው ስሜነኛ መሆን ከወገራ አልፌ አገኘሁ እንደሆን” በሚለው ሥነ-ቃል አጅበው እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉትን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የአቶ አምሳሉን መልዕክት ተከትሎ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፣ ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እና ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ንግግር አድርገዋል፡፡

ዝግጅቱ እስከነገ ይቀጥላል፡፡ ለስሜን ህልውና አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡ መሬታቸውን ለተፈጥሮ ሀብቱ ህልውና የሰጡ ባለ ራዕይ የስሜን ገበሬዎች የ50 ዓመቱ ባለ ታሪክ ሆነው ምስጋና ይቸራቸዋል፡፡ ወዳጅ ሀገራት ስለአበረከቱት አስተዋጽኦ ይመሰገናሉ፡፡

READ  የአፍሪካ ዋንጫና ፍትሐዊ ምርጫ

የኦስትሪያ መንግስት ትብብር እና የበርካታ አጋሮች አብሮነት ዳግም ለትንሳኤ ያበቃውን የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የመጎብኘቱ መርሐ ግብርም ይቀጥላል፡፡ የከሰዓቱን ዝግጅት ለመታደም ወደ ደባርቅ አዳራሽ እየገባሁ ነው፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

Published

on

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

በትላንትናው ዕለት የተካሄደው 7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች….

የአመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም – ዘመን
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ – አለምሰገድ ተስፋዬ (ያበደች የአራዳ ልጅ 3)
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት – ዘሪቱ ከበደ (ታዛ)
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ – ኢትዮጵያ (ቴዎድሮስ ካሳሁን)
የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ/ድምፃዊት – ዳዊት አለማየሁ
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ – ብስራት ሱራፌል (ወጣ ፍቅር)
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም – ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)/ኢትዮጵያ/
የአመቱ ምርጥ ፊልም -ታዛ
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ – ግርማ በየነ

SHEGER FM 102.1 RADIO

READ  ገድሉ በተፈጸመበት ምሽት በታላቅ እርካታ የተጻፈ
Continue Reading

Entertainment

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ | ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት

Published

on

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ፡፡ ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት፤

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ፡፡ ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት፤ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ስሜን አናት እየተጓዘ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ አባይ በርሃ ውስጥ መንገደኞች ከሚያርፉባት ቀዝቃዛ ቦታ ያደረገውን የጉዞ እረፍት የስሜን ትረካው መጀመሪያ አድርጎታል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

አባይን በርሃ የሚለው ማን ነው? አባይ በሁለት ልብስ እንዳለው ለማየት ይሄኔ ነው መምጣት፡፡ ቢጫ ጥለት ያለው አረንጓዴ ኩታ የለበሰ የሚመስለው መልካዓ ምድር በአደይ አበባ መዓዛ አሸብርቋል፡፡ ከፍልቅልቅ እስከ ደጀን ልጆች ጥንቅሽ ይዘው ዓለማቸውን እየቀጩ ነው፡፡ ወፍ እንዳሻዋ የማሽላ ፍሬ ላይ ትራወጣለች፡፡

አባይ በርሃ በዚህ ወቅት ምትሃት የሚመስል ተፈጥሮ ነው፡፡ ክረምት ይውረገረጉ የነበሩ ፏፏቴዎች አሁን በጋን በመቀበል መንፈስ ላይ ናቸው፡፡ ድፍርሱ ውሃ መጥራትም መጉደልም ጀምረዋል፡፡ ማሳው ጥርን ያስናፍቃል፡፡ ይሄ ሁሉ እጽዋት እየተወዛወዘም ይሞቃል፡፡

ከሚሞቀው በርሃ ውስጥ ከታላቁ አባይ ሸለቆ አንድ ጉያ፤ ድልድዩን ተሻግሬ አንዲት ዛፍን ተገን አድርጋ ታላቅ ዓለም ከሆነች ስፍራ አርፌአለሁ፡፡ የውሃ ድምጽ ከሚሰማበት፣ ዝንጀሮ ከሚቀላውጥበት፣ ጦጣ ዛፍ ላይ ሆና ከምትታዘብበት፡፡ ሰፈር የሚያስጠልሉ ዛፎች ከገደሉ አፏፍ ሆነው ቀዝቃዛዋን አየር ከፈጠሩበት ልዩ ስፍራ ነኝ፡፡

ሰብለወንጌል ካፌ ብለዋታል ማረፊያዋን፡፡ እንደ ማር እስከ ጧፍ ሁሉ የሀዲስ ዓለማየሁን የፍቅር እስከ መቃብርን መቼት ተከትላ የተፈጠረች ናት፡፡ እዚህ ነኝ፡፡ አየሯ ልዩ ነው፡፡ መንገደኛ የማያልፋት ስፍራ ናት፡፡

አረፍ ብሎ ሻይ ቡና ማለቱ ወግ ሆኗል፡፡ የፍቅር እስከ መቃብሯ ሰብለ ወንጌል አባይ በርሃን ስታቋርጥ ያረፈችባትን ቦታ መርጠው ዛሬ ማረፊያ ያደረጓት ወጣቶች ምናብ ተከትለው እውን የሆነ ነገር የፈጠሩ ጀግኖች ናቸው፡፡

READ  በህገወጥ የቡና ንግድ ሃገሪቷን ከ3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በማሳጣት ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

የአባይ በርሃ ወበቅ እዚህች ስፍራ እጣ ፈንታ የለውም፡፡ እዚህ ያለው እንደ ጎዣም ጠላ ሊያውም ጉሽ እንደሌለው ዝም ብሎ የሚሳብ ወደ ውስጥ የሚገባ አየር ነው፡፡

ቀዝቃዛ አየር፤ ከዛፎቹ ትንፋሽ የሚወጣ፣ በውሃ ድምጽ የታጀበ፣ ወደ ስሜን ጉዞ ላይ ነኝ፡፡ የተራሮች አናት ፓርክ ከሆነ ሃምሳ አመት ሞልቶታል፡፡ እሱን ለማክበር ደባርቅ እገባለሁ፡፡ እናም እዚህች ስፍራ ማረፍ እንጂ መኖር አይቻልምና ጉዞው ቀጠለ፡፡ DIRETUBE

 

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close