የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ ወጣ

0
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ ወጣ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ቶምቦላ ሎተሪ እጣ ትናንት ወጥቷል።

በዚህም መሰረት ባለሶስት መኝታ ክፍል መኖሪያ ቤት የሚያስገኘው አንደኛ እጣ ቁጥር 44 39 13 0 ሆኗል።

ባለ ሁለት ጋቢና ፒክ አፕ ተሽከርካሪ የሚያስገኘው ሁለተኛ እጣ ቁጥር ደግሞ 38 13 19 3 በመሆን ወጥቷል።

ከዚህ ባለፈም ባለሁለት ክፍል መኝታ ቤት የሚያሸልመው ሶስተኛ እጣ ቁጥር 48 52 94 4 ሆኖ መውጣቱ ተገልጿል።

ባለማቀዝቀዣ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ እድለኛ የሚያደርገው እጣ ቁጥር 20 41 26 1 ሲሆን፥ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ እድለኛ የሚያደርገው ቁጥር 27 88 13 4 ሆኖ ወጥቷል።

ሌሎች ከእርሻ ትራክተር እስከ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚያሸልሙ እጣ ቁጥሮችም ወጥተዋል።

የማስተዛዘኛ ቁጥሩ ደግሞ ሶስት ሆኗል።

ከሎተሪ ሽያጩ እስከ አንድ መቶ ሚለየን ብር ገቢ እንደሚገኝ ይጠበቃል- ኤፍ ቢ ሲ

READ  በኢትዮጵያ የታሠሩ ዐስራ ስድስት ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ

NO COMMENTS