Connect with us

World

ከ6ነጥብ 7 እስከ 9 ሚሊዮን እድሜ ያለው የጉማሬ ቅሪተ አካል ተገኘ

Binyam G-Kirstos

Published

on

ከ6ነጥብ 7 እስከ 9 ሚሊዮን እድሜ ያለው የጉማሬ ቅሪተ አካል ተገኘ

በኢትዮጵያ በምዕራብ ሐረረጌ ዞን ጮሮራ በተባለ ሥፍራ ከ6ነጥብ 7 እስከ 9 ሚሊዮን   የሚገመት  ዕድሜ ያለው  የጉማሬ ቅሪተ አካል  መገኘቱን  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ ።

የባለሥልጣኑ  የዓለም  አቀፍ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለዋሚኮ እንደገለጹት   በምዕራብ ሐረረጌ በጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ጮሮራ በተባለ የአርኪዮሎጂ መካነ ቅርስ ሥፍራ ከ6ነጥብ7  እስከ 9 ሚሊዮን እድሜ ያለው የጉማሬ ቅርተ አካል አግኝተዋል ።

ከአዲስ አበባ በ170 ኪሎሜትር ርቀት በሚገኘው ጮሮራ በተባለ ሥፍራ ላይ እልህ አስጨራሽ ጥናትና ምርምር  ሲያካሄድ  የቆየው የተመራማሪዎች  ቡድን  እንደገለጸው  አሁን  የተገኘው   ቅሪተ አካል የጉማሬ  ጥርስንና  ማንቀሳቀሻ  አካላትን  ያካተተ ነው ።

የቅሪ አካሉ መገኘቱ  ቀደምሲል  በህይወት  የነበሩና  ከዓለም የጠፉ የአጥቢ እንስሳት ሁኔታን  ሳይንቲስቶች  እንዲረዱ የሚያስችል  መሆኑን  የተመራማሪዎች ቡድኑ  ጠቁሟል ።

በጮሮራ የተገኘው  የጉማሬ  ቅሪተ አካል ጮሮራትሪዩምሮቢ  የተባለ አዲስ የዘር ግንድ  ስያሜ ተሠጥቶታል ።

የቅሪተ አካሉ ስያሜ የተሠጠው ቅሪተ አካሉ ከተገኘበት የጮረራ ቦታና በኦሮምኛ ቋንቋ  የጉማሬ እንስሳ  መጠሪያ ስም ከሆነው ሮቢ  የተወሰደ ነው – Walta

READ  የስፖርት ማዕድ- ስፖርታዊ መረጃዎች እና የዝውውር ወሬዎች
Continue Reading

Africa

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን ተገለጸ

Published

on

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት በቴክኒክ ደረጃ በሶስትዮሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ውይይት ወቅት ያልተቋጩ ጉዳዮች ዙሪያ በሶስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመግባባት መንፈስ ላይ የተመሰረተ ገንቢ ውይይት ተደርጎ በስኬት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም በተመለከተ ካላት በጋራ ተጠቃሚነት፣ ፍትሐዊነት፣ምክንያታዊነት እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች በመነሳት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ አገራት ጋር ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

እንደ አቶ መለስ ገለጻ የሶስቱ አገራት የውሃ ሚ/ሮች ቀጣይ ውይይታቸውን በቅርቡ በሚገለጽ ጊዜና ቦታ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን ትናንት (ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም.) የተደረገው ውይይት በበለጠ መግባባትና በግልጽ ወንድማማችነት መንፈስ የተካሄደ ነበር።

የሶስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ጋባዥነት ያደረጉት ጉብኝት ታሪካዊ እንደሆነም አቶ መለስ ተናግረዋል።

ለዚህም ማሳያዎቹ በአገሮቹ መካከል ግልጽነትና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር እድል መፍጠሩ፣ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ መሬት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማየት ማስቻሉ፣ ከጉብኝቱ በኋላ ከግድቡ የቴክኒክ ጉዳዮች አንጻር ሚኒስትሮቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በፕሬጀክቱ ጽ/ቤት በኩል የተሰጠውን አርኪ ማብራሪያ መጥቀስ ይቻላል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ ይህንን ጉብኝት በማዘጋጀቷ አመስግነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶቹ በኩል በ 2009 በጀት ዓመት አራት ነጥብ ዘጠኝ ስምንት (4.98) ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቦንድ ሸጧል፡፡ ከፍተኛው ተሳትፎ የተገኘውከመካከለኛ ምስራቅ ነው። በ2010 ዓ.ም የበጀት ዓመት አምስት ነጥብ አንድ (5.1)ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ታቅዷል፡፡

የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተሟሟቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አትዮጵያውያን በግድብ ግንባታ በገንዘብ የማይተመን የአርበኝነት መንፈስ እየተረባረቡ ናቸው።

READ  ኖኪያ 3310 ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብጽና ሱዳን ጋር በወንድማማችነት መንፈስ ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች፣ ይህም ትብብር ብቸኛው አማራጭ ነው ብላ ስለምታምን ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 09 ቀን 2010 ዓ.ም.

 

Continue Reading

Law or Order

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞች እገዳ ዳግም ውድቅ ሆነባቸው

Published

on

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞች እገዳ ዳግም ውድቅ ሆነባቸው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስምንት ሃገራት ስደተኞች ላይ ለመጣል ያቀዱት አዲስ ማዕቀብ በሀገሪቱ የፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

ማዕቀቡ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

የፌደራል ዳኛው ዴሪክ ዋትሰን የጉዞ እገዳው የአሜሪካንን ጥቅም በምን መልኩ ማስጠበቅ የሚያስችል አሳማኝ ማስረጃ የለውም ነው ብለዋል፡፡

ዳኛው ዴሪክ ዋትሰን ከሃዋይ ግዛት የተወከሉ ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ህግ መሰረት እንዲህ አይነቱን ማዕቀብ ለመጣል ስልጣኑ የላቸውም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሃገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ሳይሆን በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው የገቡትን ቃል ለማሟላት እየተጠቀሙ ነው በማለት የሃዋይ ግዛት እየከሰሰች ትገኛለች፡፡

አዲሱ የስደተኞች ማዕቀብም ሰሜን ኮሪያንና ቬንዙዌላንም ያካተተ ሆኗል፡፡

ሌሎች ግዛቶችም የሃዋይን ፈለግ በመከተል ማእቀቡን ለመቀልበስ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ቢቢሲ

READ  የቱርኩ ቸኮሌት ፌስቲቫል የትራምፕንና ታዋቂ ሰዎችን መልክ ይዞ ብቅ አለ
Continue Reading

Business

USAID የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የሚያግዝ የ181 ሚሊዮን ዶላር መርሀ-ግብር ይፋ አደረገ

Published

on

USAID የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የሚያግዝ የ181 ሚሊዮን ዶላር መርሀ-ግብር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6፤2010 ዓ.ም.፤- የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የሚያግዙ አራት መርሀ-ግብሮችን ይፋ አደረገ፡፡

እነኚህ የተሻለ ለውጥን የሚያበረታቱ መርሀ-ግብሮች፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ለመከላከል የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ይደግፋሉ፡፡ እ.አ.አ እስከ 2022 ድረስ USAID ለመርሀ-ግብሮቹ 181 ሚሊዮን ዶላር (ወደ 4.9 ቢሊዮን ብር) ወጪ የሚያደርግ ሲሆን፤የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት (KOICA) ለአራቱ መርሀ-ግብሮች ትግበራ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

አራቱ መርሀ-ግብሮች፤- የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ክብካቤ፤ የአዳጊ ክልሎች ጤና ስርዓት፤ የዋሽ (WASH) መርሀ-ግብር እንዲሁም የክትትል፤ ግምገማ፤ ተመክሮና ስርጸት ስራዎች ላይ ያተኩራሉ፡፡

የለውጥ መርሀ-ግብሮቹን እውን ለማድረግ፤ በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ እመርታ ለማምጣት ከተከናወኑ የጤና ዘርፍ ማሻሻያዎች፤ የእናቶች፤ የጨቅላ ህጻናት እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቶች አቅርቦት፤ እንዲሁም፤ ከአቅም ግንባታ ስራዎች የተገኙ ልምዶች ተቀምረዋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፤ የጤናውን ስርዓት የማጠናከር፤ የአገልግሎት አቅርቦትን፤ የቤተሰብና የኅብረተሰብ ጤና ልማዶችን ማጠናከር ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

መርሀ-ግብሩ በትግራይ፤ አማራ፤ ኦሮሚያ እና ደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች በ400 የገጠር ወረዳዎች የሚገኙ 42 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

በአዳጊ ክልሎች የሚተገበረው የጤና ሥርዓት፤ ኅብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ እና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የእናቶች፤ የጨቅላ ሕጻናት እና የሕጻናት ጤና አገልግሎቶችን በስፋት መጠቀም የሚያስችል ሲሆን፤ በአራቱ አዳጊ ክልሎች ማለትም፤ በአፋር፤ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፤ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ዋሽ (WASH) ለንጽህና ይበልጥ ትኩረት በመስጠት እና በቀላሉ የሚገኙ የዋሽ ምርቶችና አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማስፋት የተቅማጥ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ ያለመ ነው፡፡

READ  ከ663 ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ዛሬም ንጹሕ የመጠጥ ዉኃ ሰለጠንኩ በምትለዉ ዓለማችን እያገኘ አይደለም

በአምስት ዓመቱ የትግበራ ጊዜ፤ የዋሽ መርሀ-ግብር በስምንት ክልሎች በሚገኙ 40 ወረዳዎች ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በመሥራት የዋን-ዋሽ (OneWASH) አገር አቀፍ መርሀ-ግብርን የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡

የክትትል፤ ግምገማ፤ ተመክሮና ስርጸት ስራዎች፤ የለውጥ መርሀ-ግብሮችን በተሻለ መንገድ ለመገንዘብ እና ለመምራት የሚያስችል ከፍተኛ ጥራት ያለው የክትትል እና ግምገማ ስርዓትን ይፈጥራል፡፡

በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር እንደገለጹት፤ “በአዲስ መልክ ይፋ የተደረጉት መርሐ-ግብሮች፤ በአርሶ አደር እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ክብካቤ አገልግሎን ለማሻሻል፤ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና ንጽህና አገልግሎትን ለማስፋፋት እንዲሁም፤ ስኬቶችን ለመለካትና ለመገምገም ያግዛሉ” ብለዋል ፡፡

USAID በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የለውጥ መርሐ-ግብሩ ትግበራ እውን እንዲሆን ከፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል፤ አምረፍ፤ ፖፑሌሽን ሰርቪስ ኢንተርናሽናል፤ ዘ ሚቼል ግሩፕ እና 12 ሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር የሚሰራ ሲሆን፤ ቁልፍ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችም የአመራር ሚና ይኖራቸዋል፡፡ @

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close