በለንደን በደረሰው የእሳት አደጋ ከ13 የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም

0
በለንደን በደረሰው የእሳት አደጋ ከ13 የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም
በለንደን በደረሰው የእሳት አደጋ ከ13 የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም
በለንደን  ከተማ ግሪንፌል ህንጻ  በደረሰው የእሳት  አደጋ ምክንያት  አስራ ሶስት  ትውልደ ኢትዮጵያውያን እስካሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ  ።

ብርክቲ ሃፍቶም የተባለች እናትና  ብሩክ  ሃለፎም  የተባለ ልጇ   በግሪንፌል  ህንጻ ነዋሪ መሆናቸው የተረጋጋጠ ሲሆን    በህንጻው   ላይ  ከደረሰው  አሰቃቂ የእሳት  አደጋ  በኋላ   እስካሁን   የት እንዳሉ  አልታወቀም ።

በምዕራብ ለንደን  ከተማ  በግሪንፌል ህንጻ  ከደረሰው የእሳት አደጋ በኋላ በርካታ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው  ትውልደ ኢትዮጵያውያን እስካሁን  የት እንደሚገኙ የማይታወቅ መሆኑን  በእንግሊዝ የሚገኘው  የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል ።

እስካሁን  ድረስ በተደረገው ማጣራት ከእናትና ልጅ ሟቾች  በተጨማሪ በአሰቃቂው የእሳት አደጋው ምክንያት  ሃሺም ከድር  የተባለ የህንጻው ነዋሪ ሚስቱና ሦስት ልጆቹን ጨምሮ ህይወታቸው ያጡ ሲሆን    ሌላው  ኢሳቅ ሻዎና ሌሎች  አምስት   ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህይወት  እንደማይገኙ ተረጋግጧል ።

በለንደን ከተማ በግሬንፌል ህንጻ በደረሰው የእሳት አደጋ  እስካሁን  30 ሰዎች  መሞታቸው  የተረጋጋጠ ሲሆን   12 የሚሆኑት   በከፍተኛ ህክምና ላይ ይገኛሉ ።

የለንደን  ፖሊስ  በሠጠው መግለጫ  እሳቱ  ሁን ተብሎ  የተነሳ ስለመሆኑ  የሚያሳይ  መረጃ  አልተገኘም ብሏል ።

በእንግሊዝ  የኢትዮጵያ አምባሳደር አበራ አፈወርቅ በበኩላቸው በአደጋው  ጉዳት  የደረሰባቸውን  ቤተሰቦች  በጎበኙበት  ወቅት እንደገለጹት በአደጋው ባደረሰው ጉዳት  የተሰማቸውን  ጥልቅ  ሃዘን  ገልጸዋል ።

የብርክቲ ሃፍቶም ጓደኛ የሆነው  ደጀን አርአያ ሁኔታውን  ሲገልጽ  “ከእሳት  አደጋው በኋላ ብርክቲን  ለማግኘት  በየሆስፒታሉ   እንደተንከራተቱና   በኋላ መሞቷን ሲያውቁ  ልባቸው   መሰበሩን ” ተናግረዋል ።

በእሳት አደጋው ወቀት  ከብርክቲ ጋር  የተወሰነ  በስልክ  ለመገናኘት  እንደሞከረም   ደጀን  ገልጿል – Walta

READ  የአዲስ አበባን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል የ850 የአዳዲስ አውቶቡሶች ግዥ ሊፈጸም ነው

NO COMMENTS