ለንደን፤ በመኖሪያ ህንጻ ቃጠሎ የጠፉ እንደሞቱ ይቆጠራል፡ ፖሊስ

0
ለንደን፤ በመኖሪያ ህንጻ ቃጠሎ የጠፉ እንደሞቱ ይቆጠራል፡ ፖሊስ

በብሪታንያ መዲና ለንደን ውስጥ በሚገኘው ግሬንፌል በተባለው ግዙፍ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ከሦስት ቀን በፊት በደረሰ ቃጠሎ መጥፋታቸው የተገለጸው 28 ሰዎች እንደሞቱ እንደሚቆጠር የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከጠፉት ሰዎች ውስጥ ስምንቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል፡፡ የብሪታንያ የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ስቱዋርት ከንዲ ዛሬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፦ የጠፉ ሰዎችን ጨምሮ በአደጋው የሞቱ ሰዎች 58 ይደርሳል፡፡ እስካሁን መሞታቸው የተረጋገጠው ግን 30 ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከጠፉ ሰዎች ውስጥ ስምንቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አንዲት እናት ከአምስት ዓመት ልጇ እና አንድ አባወራ ከባለቤቱ እንዲሁም ከሦስት ልጆቹ ጋር ከአደጋው በኋላ መጥፋታቸው ከተነገረላቸው ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ኤምባሲው ጠቁሟል፡፡ ኤምባሲው በይፋዊ የትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ከጠፉት ውስጥ በኤምባሲው ውስጥ በሹፍርና የሚያገለግሉ ባልደረባ አንዲት ዘመድም ይገኙበታል፡፡ በሆስፒታል ህክምና እያገኙ ካሉ 24 ሰዎች ውስጥ አስራ ሁለቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ኤምባሲው አክሎ አመልክቷል፡፡source-DW

READ  አሜሪካ የሶማሊያና የኬንያ ዜጎችን ወደሀገራቸው መለሰች

NO COMMENTS