የመንገዶች ባለሥልጣን ነገ ምሽት የጃክሮስ አደባባይን ማፍረስ እጀምራለሁና አማራጭ ተጠቀሙ ብሏል

0
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ነገ ምሽት የጃክሮስ አደባባይን ማፍረስ እጀምራለሁ
የአደባባዮቹ መፍረስ መጨናነቆቹን ቀንሷል ያለው ባለሥልጣኑ በቀጣይም የቦምማርሌ አደባባይ ፈርሶ በትራፊክ መብራት እንደሚተካ ከባለሥልጣኑ የመረጃና ኮሙኒኬሸን ቡድን መሪ ከአቶ እዮብ በቀለ ሰምተናል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ነገ ምሽት የጃክሮስ አደባባይን ማፍረስ እጀምራለሁና አሽከርካሪዎች የምሽት መንገዳችሁ እንዳይዘጋባችሁ አማራጭ ተጠቀሙ ብሏል፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ እክል ፈጥረዋል ያላቸውን አደባባዮች በማፍረስ በምትኩ በትራፊክ መብራት መቀየር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

እስካሁንም የ18፣ ጀሞንና ለቡ የሚገኙ አደባባዮችን አፍርሶ በምትኩ የትራፊክ መብራቶችን አቁሟል፡፡

ነገ ምሽት ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ ደግሞ የጃክሮስ አደባባይን አፍርሼ በትራፊክ መብራት እተካዋለሁ ብሏል፡፡

በመሆኑም በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ ስለሚፈጥር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ ተጠቀሙ ተብላችኋል፡፡

የአደባባዮቹ መፍረስ መጨናነቆቹን ቀንሷል ያለው ባለሥልጣኑ በቀጣይም የቦምማርሌ አደባባይ ፈርሶ በትራፊክ መብራት እንደሚተካ ከባለሥልጣኑ የመረጃና ኮሙኒኬሸን ቡድን መሪ ከአቶ እዮብ በቀለ ሰምተናል፡፡
SHEGER FM 102.1 RADIO

READ  ብሔራዊ የጋራና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ

NO COMMENTS