Connect with us

Sport

ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች………

Juliet Tedla Asfaw

Published

on

ከስፖርት መዓድ

1-ኦሊቨር ዥሩድ በአረሰናል  የፕሪሚየር ሊግ አስራ አንድ ጨዋታዎችን በቋሚነት ቢጀምርም ዳኒ ዌልቤክከጉዳት ከተመለሰ በኋላ ግን ቦታውን ለማስጠበቅ ሲቸገር ታይቷል፡፡አሁን ደግሞ አርሰን ቬንገር አዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በአማራጭነት ይዘውቷል ተብሏል፡፡እናም በ87 ሚሊየን

ዩሮ ምባፔን ከሞናኮ ለመግዛት ያቀረቡት ሃሳብ ውድቅ የተደረገባቸው ቬንገር የ30 ዓመቱን ዥሩድን ጨምረው ለመደራደር አስበዋል ተብሏል፡፡

2-ሊዮኔል ሜሲ የባርሴሎና ዋና የዝውውር ኢላማ የሆነውን ማርኮ ቬራቲን በፎቶ በተደገፈ ማስረጃ አብረው እራት መብላታቸው የሚያሳየውን ዘገባ አስተባብሏል፡፡ሆኖም ግን ከዚህ ዘገባ በኋላ ቬራቲ ባርሳን ይቀላቀላል የሚሉ አስተያየቶች በሰፊው እየተሰራጩ ናቸው፡፡ የ24 ዓመቱ ቬራቲ ለፓሪሰን ዠርሜይን አመራሮች ውሉን በማፍረስ ወደ ባርሳ መሄድ እነደሚፈልግ ተናግሯል ተብሏል፡፡

3- አትሌቲኮ ማድሪዶች በዝውውር መስኮቱ ያጧቸዋል የተባሉትን አንቶኒ ግሪዝማንን እና ኮኬን ኮነትራታቸውን በማራዘም ለማስቀረት ችለዋል፡፡ አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ፈርናንዶ ቶሬዝ ማዞራቸው ታውቋል፡፡ በሜክሲኮ ክለብ የ12 ሚሊየን ዩሮ ለቶሬዝ የቀረበለት አትሌቲኮ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ የተነገረ ሲሆን ቢያንስ ለቀጣ አንድ አመት ተጫዋቹን ማቆየት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

4-ኤዲን ሃዛርድ በለንደኑ ክለብ ቼልሲ መቆየት እነደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ቤልጄሚዊው ከዴቪድ ድሂያ ጋር የዚንዲን ዚዳን የዝውውር ዕቅድ ውስጥ ዋነኛው እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ተጫዋቹም አማራጮችን እንደሚመለከት ከዚህ በፊት ተናግሮ ነበር፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ሃዛርድ በአለማችን ቁጥር አንድ ክለብ እንዳለ እንደሚሰማው ገልፆ በቼልሲ ቆይታው ደስተኛ መሆኑንና በምዕራብ ለንደኑ ክለብ እንደሚቆይ አስታውቋል፡፡

5-የቼልሲው ተከላካይ ጆን ቴሪ 22ዓመት የቆየበት ክለብ ጋር በመጪው ጁላይ ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ ሲሆንወደ ፈለገበት ሌላ ክለብ የመሄድ መብት ይኖረዋል፡፡ የበርሚንግሃም ክለብ አሰልጣኝ ሃሪ ሬድናፕም ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ሬድናፕ የቴሪ አድናቂ እንደሆኑና ወደ ክለባቸው ቢመጣ ደስተኛ እንደሆኑ ቢገልፁም ከአስቶን ቪላ ከበርንማውዝ እነዲሁም ከቻይና ክለቦች ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቃቸዋልተብሎ ይገመታል፡፡

READ  ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች………

6-ሌስተር ሲቲን ለፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮንነት ያበቁት ክላወዲዮ ራኒዬሪ የፈረንሳይ ሊግ አንድ ክለብ ለሆነው ናንቴስ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡

ዘ ቲንከር ማን ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር የሁለት ኣመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን ከቀድሞው የፈረንሳይ አሰልጣኝ ኮከብ ቆጣሪው ራይሞንድ ዶሚኒክ የፈረንሳይ ሊግ የአሰልጣኞች ህግ ጋር ተያይዞ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ራኒየሪ ግን ’’ ስራዬን በተገቢው መንገድና በትኩረት አሰራለው ከዛ በዘለለ ስለማንኛውም ሰው ትችት ቦታ አልሰጥም’’ ሲሉ ለዶሚኒክ ወቀሳ ምላሻቸውነወ ሰጥተዋል፡፡

Ethiopia

አቶ ተክለወይኒ በEthio FM 107.8 በሰጡት መግለጫ ውክልናቸው መነሳቱ ተገለፀ

Elias Tesfaye

Published

on

EthioSport EthioFM

የትግራይ ክልል አስተዳደር ክልሉን በመወከል የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዚዳንት የሆኑትን የአቶ ተክለወይኒ አሰፋን ውክልና ያነሳው

1) ከትላንት ወዲያ በEthio FM 107.8 ኢትዮ ስፖርት ፕሮግራም ከጋዜጠኛ Tadele Assefa ጋር በነበራቸው ቆይታ ያደረጉት ንግግር እና
2) ዛሬ በኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር የክልሉን መንግስት አቋም እንደማያንጸባርቅ ስለታመነበት መሆኑን ሁለት የከፍተኛ አመራር አባላት ገልጸውልኛል።

ከኤፍ ኤሙ ጋር ያደረጉት ንግግር ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩን የሚቃረን በመሆኑ ከሳቸው የቀረበ ቅሬታ ነበረ ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረብኩ ሲሆን፤ “ከጠ/ሚኒስትሩ የቀረበ ነገር የለም፣ እንዲቀርብም አትጠብቅም፣ የክልሉ ውሳኔ መነሻ የተክለወይኒ ንግግር የክልሉን አቋም የማያንጸባርቅ መሆኑ ብቻ ነው” ብለኛል።

READ  ከስፖርት መዓድ -ትኩስ ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ እና የዝውውር ወሬዎች.........
Continue Reading

Ethiopia

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ለአዲሱ ትውልድ ሊራራለ ይገባል

Elias Tesfaye

Published

on

(ዳን አድማሱ ለፌደሬሽኑ ያስተላለፈው መልዕክት)

  • የኢትዮጵያ አንዱ ትኩሳት

ልጅ እያለው ለእግር ኳስ የነበረኝ ፍቅር በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት መልስ ቅዳሜና እሁድ በተለይም ክረምት እግር ኳስ ከአመት እስከ አመት ከህይወቴ ጋር ተሰፍቶ ነበር ሙዚቃ በጣም ብወድም ለራሴ አንድ ቀን የሀገሬን ማሊያ ለብሼ ያን ወርቅ የኢትዮጵያ ደጋፊ ከጫፍ እስከጫፍ ሳስጨፍር በህልሜ እያየው እንቅልፍ ሳልተኛ ያደርኩባቸው ሌሊቶች ቁጥር አይገልፃቸውም ለእናቴ የቀረኋት አንድ ልጅ እኔ ስልሆንኩ ከፍተኛ ቁጥጥር ቢኖርብኝም አንዳንዴ በመስኮት እየዘለልኩ ወይም አልጋ ውስጥ ትራስ በማስተኛት የተለያየ ዘዴ በመፍጠር ከሜዳ አልቀረም

አንድ ግዜ እጄ ዞሮ በከፍተኛ ስቃይ በንጋታው ሜዳ ሄጄ እናቴ ሜዳ ድረስ መጥታ ስትወስደኝ የመረረ ለቅሶዬን ያዩ አንድ እናት መነኩሴ እንዳትገርፊው ገዝቼሻለው ብለው ያስጣሉኝን መቼም አረሳውም አንዳንዴም ጠዋት እንደወጣው ምግብ ሳልበላ እዛው ሜዳ አምሽቼ እመለስ ነበር ምክኒያቱም ለምሳ ከገባው መውጣት የለም ቀጭን ብሆንም በጣም ጎበዝ አጥቂ ነኝ በሁለቱም እግሬ እጫወታለው በጣም ጥሩ ትንፋሽ አለኝ ፈጣን ነበርኩ ኳስ ካገኘው ከመረብ ማገናኘት በጣም ቀላል ነው አብረውኝ ከሚጫወቱ የትምህርት ቤት ጎደኞቼ አንዱ ጀግና play maker ነበር ክለብ ጥሪ አድርጎ ወደ ጃንሜዳ ሄደ ጎደኛዬ አይደለም ለኢትዮጵያ እግርኳስ ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓ የሚመጥን ብቃት ነበረው

በደስታ ሸኘሁት ትንሿ ልቤ በመንፈስ አብራው ነበረች ጎደኛዬ ጃንሜዳ ደርሶ ከታየ በሁላ የ3 ወር ደሞዙንና በዛን ጊዜ እንኳን አይተን ሰምተን የማናቀውን ገንዘብ እንደተየቀ በደስታ ለምትዘለው ልቤ በሀዘን በሚዘንበው እንባው ነገረኝ በንጋታው ወደ ጃንሜዳ ለመሄድ የተቁነጠነጠው እግሬ ከዳኝ ልቤ ቀጥ አለች ውስጤ ሞተ እንደኔ አንድ ድሀ እናት ብቻ ላለው ኢትዮጵያዊ ልጅ የእግር ኳስ ፍቅር ብቻ ምንም አያደርግለትም ከዛች ቀን ቡሀላ ትንሿ ልቤ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ቂም ያዘች (በማን ላይ እንዳልኩ ይገባችኋል ) የአውሮፓን እግር ኳስ በጣም እከታተላው እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ እግር ኳስን የሚወድ ያለ አይመስለኝም ህዝቤ ስለሆነ አይደለም

READ  ጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ከጠያቂ የተጋባበት ጉንፋን ለሞቱ መፋጠን ምክንያት ነው ተባለ

ብራዚሎች ሮናልዲኒሆ እንግሊዞች ጋስኮይ ጣሊያኖች ፔርሎ ወይም ፈረንሳዬች ዚዳን ስፔኖች ኢኔሽታ እና አርጀንቲናውያን ሜሲ አላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ፔሌ ወይ ማራዶና አልነበረውም ሜሲ ና ሮናልዶ ወይም ቡፎን የለውም( ይህን ስል ብዙ ጀግኖቻችንን መቼም አረሳቸውም ከድሮም ከአሁንም ) ታዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን ኳስ ይወዳል ምክኒያቱም እያንዳንዱ ሰፈር ሜዳ ላይ ሜሲ ሮናልዶ ካንቴ ዣቪ ካንቶና ሄነሪ ላምፓርድ ጄራርድ ቤካም ነይማር ጊግስ ትልቁሮናልዶ … አሉ ምንአልባትም ሜዳ ላይ እንደማይክል ማይክ ሳይሆን ኳስ ይዞ የሚያዝናናው ሮናልዲኒሆን ስንት ጓዳ አቅፎ እንደመከነ ቤት ይቁጠረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከይድነቃቸው ተሰማ ቡሀላ እንደእኔ ምንም የሰራ አይመስለኝም የኛ ህልም ቅዠት ሆኗል የኛ ብቃት ባክኗል ምኞታችን መክኗል እንጀራችን ሻግቷል ሳቃችን ተነጥቋል ቢያንስ ለእነዚ ልጆች እራሩላቸው የኢትዮጵያን እግር ኳስ አድኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ እርግማን ምን እንደሆነ ባላውቅም አንድ መሲህ ግን ሁልጊዜ እጠብቃለው እግርኳስ በእውቀትና በፍቅር እንጂ በጡንቻ አይመራም

ወደ ኋላ ነው እንጂ ወደ ኋላ ፊት የለም

ዳን አድማሱ

Continue Reading

Ethiopia

የ2010 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ – በ2010 ዓ.ም. የአትሌቶች የውድድር ሽልማት በእጥፍ ጨመረ

Published

on

የ2010 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ - በ2010 ዓ.ም. የአትሌቶች የውድድር ሽልማት በእጥፍ ጨመረ

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ በዘንድሮው የ2010 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ ለሚወዳደሩ አሸናፊ ወንድና ሴት አትሌቶች የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት በእጥፍ ጨምሮ ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የሽልማት መጠን ማስተካከያው የተደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለብዙ ጀማሪ አትሌቶች የወደፊት አለማቀፋዊ ተሳትፎ ፈር ቀዳጅ መድረክ መሆን አንዱ አላማው እንደመሆኑ አትሌቶችን ለማበረታታት ታስቦ የተደረገ ነው፡፡

ይህ ሽልማት ባጠቃላይ የዘንድሮው የሽልማት መጠንን ከ300 ሺ ብር በላይ እንደሚያደርሰውም ታውቋል፡፡

በተጨማሪም የዚህ አመት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ውድድሩን ለመሳተፍ ከሚለብሱት የሩጫ ቲ-ሸርት በተጨማሪ የመሮጫ ቁጥር በደረት ላይ ማድረግ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ መሆኑንም የሩጫው አዘጋጆች
አስታውቀዋል፡፡

ይህም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን እንደሌሎች አለም አቀፍ ውድድሮች ያለውን ደረጃውን ከፍ ከማድረጉም በተጨማሪ ሃሰተኛ የሆነ ቲ-ሸርትን ለማስወገድ ታስቦ የተደረገ ነው፡፡

የመሮጫ ቁጥር እያንዳንዱ ባር ኮድ ሲኖረው ማንኛውም ተሳታፊ ያለ መሮጫ ቁጥር ለመሳተፍ ቢሞክር ከውድድሩ ውጪ እንደሚሆን
ተገልጧል፡፡

30 ቀናት የቀሩት የ17ተኛው ዙር ታላቁ ሩጫ ባለፈው አመት የጀመረውን የሁለት ማእበል መነሻ ሩጫ ዘንድሮም የሚቀጥለው ሲሆን ከተሳታፊዎች በተሰጠ አስተያየት መሰረት ውድድሩን ከአንድ ሰዓት በታች ለሚጨርሱ መነሻን ቀይ ከማድረግ ይልቅ አረንጓዴ(በተለምዶው አረንጓዴ ከትራፊክ መብራት ጋር ተያይዞ ቀድሞ መሄድን ስለሚያመላክት) ተደርጓል፡፡

ከአጠቃላዩ 44ሺህ ተሳታፊ 7ሺው ፈጣን ሯጮችን ሲያሳትፍ ቀሪው 37ሺህ ቀይ ቲ- ሸርት ለሚለብሱና ዘና ብለው ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሯጮች የሚሆን ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሕሊና ንጉሴ 0911601710 ኢሜል፡ hilina@ethiopianrun.org

READ  በዓለማችን እጅግ ሃብታም ሰዎች እነማን ናቸው? እነማን ከሰሩ እነማን ነሰሩ?
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close