ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመረጡ አትሌቶች ሐሙስ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመረጡ አትሌቶች ሐሙስ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

0
ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመረጡ አትሌቶች ሐሙስ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ
ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመረጡ አትሌቶች ሐሙስ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አገራቸውን እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች፣ ሐሙስ ሰኔ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ ሆቴል ገብተው ዝግጅታቸው እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በለንደን ከተማ በሚዘጋጀው የዓለም የአትሌቶች ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ለማሟያ ይረዳቸው ዘንድ፣ በኔዘርላንድ የማጣሪያ ውድድር ማድረጋቸውን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ከሰኔ 3 እስከ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በሔንግሎ በተዘጋጀው የማጣሪያ ውድድር ከተሳተፉ አትሌቶችና ሚኒማ ካሟሉ አትሌቶች በተጨማሪ፣ በተለያዩ ውድድሮች ያስመዘገቡትን ውጤት በመመልከት ቀነኒሳ በቀለ በማራቶን፣ እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ በ10 ሺሕ ሜትር ተሳታፊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ቀድሞ ለሚኒማ ሟሟያ ተብሎ 10 ሺሕ እና 5 ሺሕ ሜትር ተሳታፊ አትሌቶችን በማሳተፍ ውድድር ሲያደርግ የነበረው ፌዴሬሽኑ፣ ዘንድሮ በተለያዩ የአጭር ርቀት ውድድሮችና የረጅም ርቀቶች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን 1.5 ሚሊዮን ብር በመመደብ ማሳተፉን አስታውቋል፡፡

50 አትሌቶችን በመያዝ ወደ ሥፍራው ያቀናው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ካሳተፋቸው የረጅምና የአጭር ርቀት ሯጮች በ800 ሜትር ወንዶች ብቻ ሚኒማውን ሟሟላት አለመቻላቸውን፣ የተቀሩት ግን የተቀመጠውን ሰዓት ማሟላት መቻላቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ገብረ እግዚሐብሔር ገብረ ማርያም ገልጸዋል፡፡

በሔንግሌ በተከናወነው የሚኒማ ማሟያ የ10 ሺሕ ሜትር ውድድር በሴቶች ገለቴ ቡርቃ 30 ደቂቃ ከ40 ሰኮንድ ከ87 በማጠናቀቅ አንደኛ፣ ሰንበሬ ተፈሪ 30 ደቂቃ ከ41 ሲኮንድ ከ68 ሁለተኛ፣ በላይነሽ ኦልጅራ 30 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ ከ57 ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ሚኒማውን ማሟላት  የቻሉ ሲሆን፣ ደራ ዲዳ 30 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ48 መግባት በቀጥታ መመረጥ ችለዋል፡፡

READ  Ethiopia in Need of Food Aid in 2016

በማራቶን ውድድር ውጤታማ እየሆነች የመጣችው የቀድሞ የ10 ሺሕ እና የ5 ሺሕ ሜትር ርቀቶች አሸናፊ ጥሩነሽ ዲባባ በድጋሚ በ10 ሺሕ ሜትር ለንደን ላይ ትሳተፋለች ተብሏል፡፡ አትሌቷ ዝግጅቷን ከወዲሁ በአዲስ አበባ ስታዲየም እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በወንዶች 10 ሺሕ ሜትር አባዲ ሐዲስ 27 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ ከ28 በመግባት አንደኛ፣ ጀማል መኮንን 27 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ ከ08 ሁለተኛ፣ የኔው አላምረው 27 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ ከ86 ሦስተኛ፣ እንዲሁም አንዳምላክ በልሁ 27 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ86 በመግባት አራተኛ ሆኖ በማጠናቀቃቸው በዓለም ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ሥፍራው ለማቅናት ልምምዳቸውን ይጀምራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም ከብሔራዊ ቡድኑ ይልቅ በግል ልምምዳቸውን የሚያደርጉ አትሌቶችን በቡድኑ ውስጥ ተካተው እንዲሠሩ፣ ፌዴሬሽኑ የተቻለውን ጥረት እንደሚያደርግ አሳስቧል፡፡

ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ፌዴሬሽኑ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት፣ ወደ ሆቴሉ የገቡ አትሌቶች ምርጫ በተመለከተ ካመጡት ውጤት በተጨማሪም ዲስፕሊን ዋነኛ መሥፈርት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል አራተኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሰኔ 7 እስከ11 ቀን 2009 ዓ.ም. በአሰላ አረንጓዴው ስታዲየም እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡ በውድድሩ 31 ቡድኖች፣ 372 ወንዶችና 295 ሴቶች በድምሩ 667 አትሌቶች ተወዳዳሪ እንደሚሆኑ ተገልጿል – Ethiopian reporter

NO COMMENTS

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close