Connect with us

Entertainment

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተፈጥሯል

Binyam G-Kirstos

Published

on

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተፈጥሯል

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አስተዳደር ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ጉዳዮች ቡድን፣ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ የዕርዳታ ምግብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መፈጠሩን በይፋ አስታወቁ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ፣ በድርቁ አካባቢዎች ከመደበኛ ምግብ በተጨማሪ በተለይ ፅኑ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መፈጠሩ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል፡፡ በሰኔ ወር መጨረሻ ደግሞ አሁን ያለው የአስቸኳይ ዕርዳታ ምግብ እንደሚሟጠጥ አስታውቋል፡፡

በመግለጫው መሠረት ከለጋሾች የሚጠበቀው ዕርዳታ በማሽቆልቆሉ ሳቢያ፣ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጉ በድርቅ የተጎዱ ወገኖች የዕለት ዕርዳታ ጠባቂዎች ለፅኑ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፡፡ ለአስቸኳይ ዕርዳታ የሚውል ምግብ መጠንም በአሳሳቢ ደረጃ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

ከሐምሌ ወር ጀምሮ 500 ሚሊዮን ዶላር ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ግዥና ለትራንስፖርት እንደሚያስፈልግ፣ 55 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ድርቁ በከፋባቸው ቦታዎች ፅኑ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች በአስቸኳይ እንደሚፈለግ በመግለጫው ተካቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ድርቁ በስፋት በሚታይባቸው ደቡባዊና ምሥራቃዊ የአገሪቱ ክፍሎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረቱ መጠን በጣም ከፍ ማለቱን መግለጫው ጠቁሞ፣ ለዚህ መንስዔው ደግሞ የበልግ ዝናብ አነስተኛ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ በሴፍቲኔት ፕሮግራም የታቀፉ 7.9 ሚሊዮን ዜጎች የዓመቱን የመጨረሻ ኮታቸውን የሚወስዱት በሰኔ ወር መጨረሻ በመሆኑ፣ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የችግሩ መጠን ሊሰፋ እንደሚችል ይጠበቃል ተብሏል፡፡

በበልግ አብቃይ አካባቢዎች ዝናቡ በማነሱ ምክንያት የአስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከ5.6 ሚሊዮን ወደ 7.78 ሚሊዮን ማሻቀቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ቁጥር በሚቀጥሉት ወራት ሊጨምር እንደሚችል የተመድ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት መግለጫ ያስረዳል፡፡

READ  ክፈት በለው በሩን...

ከዚህ ቀደም ለድርቁ ተጎጂዎች ያስፈልጋል የተባለው ዕርዳታ 948 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም፣ አሁን ግን 550 ሚሊዮን ዶላር ነው የሚፈለገው፡፡ ከለጋሾች የሚጠበቀው ዕርዳታ በሚፈለገው መጠን እየተገኘ ባለመሆኑ፣ አሁንም የተጠናከረ ዕርዳታ መቅረብ እንዳለበት እየተጠየቀ ነው፡፡ በተለይ የዕለት ደራሽ ምግቦች፣ የተመጣጠኑ ምግቦችና ንፁህ የመጠጥ ውኃ አንገብጋቢ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ድርቁ የከፋባቸው ሥፍራዎች በጣም የራቁ በመሆናቸውና የውኃ ጉድጓዶችም በመድረቃቸው የውኃ እጥረት ፈተና መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ድርቁ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ የተለያዩ ሥፍራዎች 7.8 ሚሊዮን ዜጎችን ያጠቃ ሲሆን መንግሥት የውኃ፣ የምግብ፣ የጤናና የትምህርት ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ይናገራል፡፡ ችግሩን ለማቃለልም የተለያዩ ሚኒስቴሮችን አቀናጅቶ በመሥራት ላይ መሆኑንና 98 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ምግብ ለተረጂዎች ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያና በሶማሊያ አሥር አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ጉብኝት አመቻችቷል፡፡ ‹‹ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፓርትነርሺፕ ሚሽን›› የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው የልዑካን ቡድን ከሰኔ 1 ቀን እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በሁለቱ አገሮች ለደረሰው አስከፊ ድርቅ ዕርዳታ ለማሰባሰብ የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ጉብኝት ያደርጋል ተብሏል፡፡

በልዑካን ቡድኑ ውስጥ አሥር የዓረብ ባህረ ሰላጤ አገሮች፣ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶችና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች መካተታቸው ተጠቁሟል፡፡ በኢትዮጵያ ከሐሙስ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በዋርዴር ዞን ከከፍተኛ የአገሪቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ጉብኝት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡ ዋርዴር ዞን ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች ዋነኛው ነው፡፡ በዚህ ዞን በድርቁ ምክንያት በርካቶች ለአስቸኳይ ዕርዳታ ተጋልጠው፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ይታወሳል፡፡

READ  ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አሰጣጣቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንዲያቀርቡ ታዘዙ

በሌላ በኩል በጋምቤላ ክልል በቅርቡ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ የተፈናቀሉ 2,395 ሰዎች (475 ቤተሰቦች) አስቸኳይ የዕርዳታ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እንደሚያስፈልጓቸው ተገልጿል፡፡ በአምስት ቀበሌዎች ውስጥ ኗሪ የነበሩ ወገኖች ቤቶቻቸው በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው የቤት ዕቃዎቻቸው፣ ማብሰያዎቻቸው፣ ልብሶቻቸው፣ ምግባቸውና ምግብ ነክ ያልሆኑ ንብረቶቻቸው ወድመውባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 950 ተማሪዎች ደብተሮቻቸውና የመማሪያ መጻሕፍቶቻቸው ከጥቅም ውጪ ሆነውባቸዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ለሦስት ወራት አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውና መቋቋም እንደሚገባቸው ተገልጿል – Ethiopian reporter

Continue Reading

Entertainment

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት | ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት

Published

on

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት | ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ደባርቅ ነው፡፡ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 50ኛ ዓመት በዓል ላይ ታድሞ የዝግጅቱን ድባብ እየተረከልን ነው፡፡ ደባርቅ የደመቀችበት ጠዋት ሲል የጠዋቱን ውሎ እንዲህ ይነግረናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ከእነኚህ ረዣዥም ተራሮች፣ ሰማይ የነኩ ምድሮች ወዲህ ያለችዋ ከተማ ዛሬ ደምቃለች፡፡ ደባርቅ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በብሔራዊ ፓርክነት የተመዘገበበትን 50ኛ ዓመት እያከበረች ነው፡፡

ዩኔስኮ ቅርሱን ከዓለም ቅርስነት እስርዘዋለሁ ብሎ ለብዝኃ-ሕይወቱ ጥበቃ ዋስትና እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥያቄ ስሜኖች መስዕዋትነት ከፍለው አሳክተውታል፡፡

ስሜን በስሜኖች ያሳካውን ህልም ከ50ኛ ዓመቱ ጋር አብሮ እያጣጣመው ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክብር እንግድነት የተገኙበት ይህ በዓል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ ክብርት ሚኒስትር ደኤታዋ፣ የክልልና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች፣ ስሜንን በመታደግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን የቆሙ ሀገራት አምባሳደሮች ታድመውበታል፡፡

የስሜን ብሔራዊ ፓርክን ታሪክ እና የስሜነኞችን ወግ በሚያሳየው አውደ ርዕይ የተከፈተው የዛሬው ዝግጅት በጠዋት ፈረቃው መርሐ ግብር በጎንደሩ ፋሲለደስ ኪነት ቡድን ታጅቦ የደመቀ ነው፡፡

“ምንኛ ደግ ነው ስሜነኛ መሆን ከወገራ አልፌ አገኘሁ እንደሆን” በሚለው ሥነ-ቃል አጅበው እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉትን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የአቶ አምሳሉን መልዕክት ተከትሎ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፣ ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እና ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ንግግር አድርገዋል፡፡

ዝግጅቱ እስከነገ ይቀጥላል፡፡ ለስሜን ህልውና አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡ መሬታቸውን ለተፈጥሮ ሀብቱ ህልውና የሰጡ ባለ ራዕይ የስሜን ገበሬዎች የ50 ዓመቱ ባለ ታሪክ ሆነው ምስጋና ይቸራቸዋል፡፡ ወዳጅ ሀገራት ስለአበረከቱት አስተዋጽኦ ይመሰገናሉ፡፡

READ  ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አሰጣጣቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንዲያቀርቡ ታዘዙ

የኦስትሪያ መንግስት ትብብር እና የበርካታ አጋሮች አብሮነት ዳግም ለትንሳኤ ያበቃውን የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የመጎብኘቱ መርሐ ግብርም ይቀጥላል፡፡ የከሰዓቱን ዝግጅት ለመታደም ወደ ደባርቅ አዳራሽ እየገባሁ ነው፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

Published

on

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

በትላንትናው ዕለት የተካሄደው 7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች….

የአመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም – ዘመን
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ – አለምሰገድ ተስፋዬ (ያበደች የአራዳ ልጅ 3)
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት – ዘሪቱ ከበደ (ታዛ)
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ – ኢትዮጵያ (ቴዎድሮስ ካሳሁን)
የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ/ድምፃዊት – ዳዊት አለማየሁ
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ – ብስራት ሱራፌል (ወጣ ፍቅር)
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም – ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)/ኢትዮጵያ/
የአመቱ ምርጥ ፊልም -ታዛ
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ – ግርማ በየነ

SHEGER FM 102.1 RADIO

READ  በቻይና መንግሥት ዓለም አቀፍ ግዙፍ ዕቅድ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋነኛ ተዋናይ ሆና ተመረጠች ተባለ
Continue Reading

Entertainment

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ | ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት

Published

on

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ፡፡ ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት፤

አባይ በርሃ ውስጥ ነኝ፡፡ ከበረሃው መሀል ባለችዋ ገነት፤ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ስሜን አናት እየተጓዘ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ አባይ በርሃ ውስጥ መንገደኞች ከሚያርፉባት ቀዝቃዛ ቦታ ያደረገውን የጉዞ እረፍት የስሜን ትረካው መጀመሪያ አድርጎታል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

አባይን በርሃ የሚለው ማን ነው? አባይ በሁለት ልብስ እንዳለው ለማየት ይሄኔ ነው መምጣት፡፡ ቢጫ ጥለት ያለው አረንጓዴ ኩታ የለበሰ የሚመስለው መልካዓ ምድር በአደይ አበባ መዓዛ አሸብርቋል፡፡ ከፍልቅልቅ እስከ ደጀን ልጆች ጥንቅሽ ይዘው ዓለማቸውን እየቀጩ ነው፡፡ ወፍ እንዳሻዋ የማሽላ ፍሬ ላይ ትራወጣለች፡፡

አባይ በርሃ በዚህ ወቅት ምትሃት የሚመስል ተፈጥሮ ነው፡፡ ክረምት ይውረገረጉ የነበሩ ፏፏቴዎች አሁን በጋን በመቀበል መንፈስ ላይ ናቸው፡፡ ድፍርሱ ውሃ መጥራትም መጉደልም ጀምረዋል፡፡ ማሳው ጥርን ያስናፍቃል፡፡ ይሄ ሁሉ እጽዋት እየተወዛወዘም ይሞቃል፡፡

ከሚሞቀው በርሃ ውስጥ ከታላቁ አባይ ሸለቆ አንድ ጉያ፤ ድልድዩን ተሻግሬ አንዲት ዛፍን ተገን አድርጋ ታላቅ ዓለም ከሆነች ስፍራ አርፌአለሁ፡፡ የውሃ ድምጽ ከሚሰማበት፣ ዝንጀሮ ከሚቀላውጥበት፣ ጦጣ ዛፍ ላይ ሆና ከምትታዘብበት፡፡ ሰፈር የሚያስጠልሉ ዛፎች ከገደሉ አፏፍ ሆነው ቀዝቃዛዋን አየር ከፈጠሩበት ልዩ ስፍራ ነኝ፡፡

ሰብለወንጌል ካፌ ብለዋታል ማረፊያዋን፡፡ እንደ ማር እስከ ጧፍ ሁሉ የሀዲስ ዓለማየሁን የፍቅር እስከ መቃብርን መቼት ተከትላ የተፈጠረች ናት፡፡ እዚህ ነኝ፡፡ አየሯ ልዩ ነው፡፡ መንገደኛ የማያልፋት ስፍራ ናት፡፡

አረፍ ብሎ ሻይ ቡና ማለቱ ወግ ሆኗል፡፡ የፍቅር እስከ መቃብሯ ሰብለ ወንጌል አባይ በርሃን ስታቋርጥ ያረፈችባትን ቦታ መርጠው ዛሬ ማረፊያ ያደረጓት ወጣቶች ምናብ ተከትለው እውን የሆነ ነገር የፈጠሩ ጀግኖች ናቸው፡፡

READ  ክፈት በለው በሩን...

የአባይ በርሃ ወበቅ እዚህች ስፍራ እጣ ፈንታ የለውም፡፡ እዚህ ያለው እንደ ጎዣም ጠላ ሊያውም ጉሽ እንደሌለው ዝም ብሎ የሚሳብ ወደ ውስጥ የሚገባ አየር ነው፡፡

ቀዝቃዛ አየር፤ ከዛፎቹ ትንፋሽ የሚወጣ፣ በውሃ ድምጽ የታጀበ፣ ወደ ስሜን ጉዞ ላይ ነኝ፡፡ የተራሮች አናት ፓርክ ከሆነ ሃምሳ አመት ሞልቶታል፡፡ እሱን ለማክበር ደባርቅ እገባለሁ፡፡ እናም እዚህች ስፍራ ማረፍ እንጂ መኖር አይቻልምና ጉዞው ቀጠለ፡፡ DIRETUBE

 

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close