Connect with us

Entertainment

“ሁሉም ሰው ‘ኢትዮጵያ’ ሲል ማየት ደስ ይላል” – ቴዲ አፍሮ

Binyam G-Kirstos

Published

on

“ሁሉም ሰው ‘ኢትዮጵያ’ ሲል ማየት ደስ ይላል” - ቴዲ አፍሮ

“ሁሉም ሰው ‘ኢትዮጵያ’ ሲል ማየት ደስ ይላል” – ቴዲ አፍሮ

ከሙዚቃ ሥራዎቹ በተጨማሪ በኢትዮጵያዊ ማንነት፣ በአንድነትና በፍቅር ዙሪያ አተኩሮ ስለሚሠራ በርካቶች ከዘፋኝነት በላይ አልቀው ይመለከቱታል። ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” የተሰኘውን አዲሱን አልበሙን በተመለከተ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርጓል።

“ጥቁር ሰው” የተሰኘው አራተኛ አልበሙን ካወጣ ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ በቅርቡ ይዞት የመጣው አልበም በቢልቦርድ የሙዚቃ ሰንጠረዥ በዓለም ሙዚቃ ዘርፍ በቁንጮነት ተቀምጧል፡፡ በመጀመሪያው የአልበሙ ሕትመት 600 ሺሕ ቅጂ በማሳተም በሀገሪቱ የሙዚቃ ኢንደስትሪም ሪከርድ ሰብሯል።

በኢንተርኔት አልበሞችን በሚሸጡ ድረ ገጾችም በከፍተኛ ቁጥር ከተገዙት ተርታ ተመድቧል፡፡ ይፋዊ የዩቲዩብ ገጹ ላይ የጫነው ነጠላ ዜማው ተመልካች ብቻ አራት ሚሊዩን ተሻግሯል።

ቴዲ ይህንን “ኢትዮጵያ” የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም ከማውጣቱ ዋዜማ ጀምሮ የነበረውን የአድናቂዎቹን ጉጉት እንዲሁም በርካቶች ከዘፋኝነት አልቀው እንደሚመለከቱት ለተጠየቀው ፤ “የተደከመበት ነገር ውጤት አምጥቶ፣ የምትፈልጊው መልዕክት ሰዎች ጋር ደርሶ፣ የሚፈጥረውን ነገር እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም። ይሕ የእግዚያብሔር ፀጋ ነው በዚህ አጋጣሚ ሁሉንም ላመሰግን እወዳለሁ” ሲል ምላሹን በምስጋና ጀምሯል።

ቴዲ በአድናቂዎቹ በጣም መጠበቅ በኪነጥበብ እና በፈጠራ ሥራ ላይ እንደሚጠመድ ሰው ጫናን አያሳድርብህም ወይ? ነፃነትንስ ይሰጥሃል? በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ደግሞ፤

“እውነቱን ለመናገር የሰውን የፍቅር መጠን ማየት በራሱ ያስፈራል። እንደዚህ መወደድ ያስፈራል። ይህን መወደድ የሚሰጥ እግዚያብሔር ነው። እኔ ይህንን ነው የማውቀው። ሁሉን ነገር የሚያደርገው እርሱ ነው። እግዚያብሔር ኢትዮጵያን አይተዋትም። ይሄ የትውልዱ የጋራ ድምጽ ነው። እኔም ደግሞ የትውልዱ አካል እንደመሆኔ የሁላችንም ድምጽ፣ አብረን አምጠን ያመጣነው ነገር ነው።” ካለ በኋላ “የጋራ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነገር ነው ። አብረን የምናዜመው እና ኢትዮጵያዊነት ከምንም በላይ አደጋ ላይ የወደቀበት ጊዜ ላይ ነው እንግዲህ እንደ ዕድል ኾኖ የደረሰን ለኛ…. እና እዚህ ጊዜ ላይ ሁላችንም ተባብረን ኢትዮጵያ የምንልበት ዕድል እግዚያብሔር ከፍቶልናል ብዬ አስባለሁ። በእውነት ለመናገር የሰው ምላሽ እኔ በሰጠኋቸው መጠን ነው ብዬ አላምንም። እዚህ ላይ የሚታየው አንድ ሰው ለሐገሩ ያለው ፍቅር፣ ለኢትዮጵያዊነት ያለው ፍቅርና በጋራ ለኖረው ነገር ያለው እምነት ነው። ይህን ስሜት የፈጠረው” ብሏል።

READ  ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኤምባሲ ከፈተች

ቴዲ የአድናቂዎቹና የሙዚቃ አድማጩ ስሜት በከፍተኛ ሁኔታ ለመነቃቃቱ ዋነኛ ምክንያት ከሀገር ፍቅር የመነጨ እንደሆነ ገልፆታል እንደ ቴዲ አፍሮ በጉልህ ስለመወደዱ ለተጠየቀው ግን “እንደ ቴዲ ላልሽኝ በእውነት እኔንጃ የምለው ነገር የለኝም ከባድ ነው………ከባድ ነው…… ” ሲል በረጅም ትንፋሽ ጨርሶታል።

ቴዲ “ኢትዮጵያ” በተሰኘው አልበሙ አተኩሮ የሰበከው አንድነትና ለኢትዮጵያዊ ማንነት በጋራ መቆምን ነው። “የሀገር ሕልውና የራስ ህልውና ነው። ሀገራችን መዳን የምትችለው ኢትዮጵያዊ እንደቀደመው መንፈስ በአንድነት ኾነን በፍፁም ቅንነት ለመቀጠልና ለማስቀጠል በጋራ ስንጥር ነው። ምክንያቱም ይሄ ቢሆን ደስ ይለኛል የሚባል አይደለም። መሆን ያለበትና የሕልውናችን መሰረት ነው።” ብሏል።

ከሐሳብ ፍጭትና በጋራ ጉዳይ ላይ ከመመካከር ይልቅ ብዙሐኑንም ባይወክል በተወሰነ መልኩ በቋንቋና በጎሳ ያለ ማተኮር እንዳለ ጠቁሞ “ይህን ደግሞ በተቻለ ሁኔታ አስተካክለን ወደ ጋራ ጉዟችን ለመሄድ መጣር አለብን ብሏል።” ቴዲ የረሃብን ጉዳይም በመቆጨት መንፈስ አንስቷል “ብዙ መብላት ያለባቸው ሰዎች አሉ፣ ብዙ የተራቡ ሰዎች አሉ ታሪካችን በረሃብ ተበላሽቷል በዚህ እራሱ መቆጨትና መናደድ አለበን። ቁጭት ከሌለም ወደ ለውጥ ለመሄድ ሃይል አናገኝም” ሲል ኢትዮጵያውያን ስሜታቸውን ዋጥ አድርገው ረሃብንም ጭምር ለማጥፋት መተባበር እንዳለባቸ መክሯል።

“እኛ ሰላምና ፍቅር አንድነት እንፈልጋለን ኢትዮጵያ ዋስትናችን ናት። ሕልውናችን ነው እና ለዚህ ሕልውናችን የጋራ ስሜታችን የተገለጠበት አጋጣሚ ነው።” ያለው ቴዲ “ብዙ የሚያግባቡን አብረን ያደረግናቸው ጥሩ ነገሮች አሉ ወደ ላይ ነው መሄድ ያለብን ወደ ትንሹ መስመር ከተሰበሰብን አስቸጋሪ ነው።” ብሏል።

ዘፈኖቹ ለፖለቲካዊ ትርጉም ክፍት መሆናቸውን …. የሠራውስ አስቦበት እደሆነ ተጠይቆ ፤ “እያንዳንዱ ዘፈኖች….የጋራ…. ሕይወታችንን አንድነታችንን አብረን የኾናቸውን አብረን ያዘንባቸውን አብረን የተደሰትንባቸውን ብዙ አብረን ያደረግናቸውን ነገሮች እንዲገልጹ አድርጌ አስቤበት ነው የሠራሁት” ብሏል።

READ  76ኛው የድል በዓል በድምቀት ተከበረ

ቴዲ በነገስታት ላይ ለምን ትኩረት ታደርጋለህ? ተብሎ ሲጠየቅ “ምልክት የሌለው ሕዝብ ይጠፋል። ራዕይ የሌለውም ሕዝብ ይጠፋል ለዚህ ነው እዚህ የደረስነው ። ስለዚህ እንዲህ የጎሉ ምልክቶቻችንን ደግሞ ከነተግባራቸው ከነሥራቸው ሊወደሱና ሊጋቡብን ይገባል።” ብሏል።

አድናቂዎቹ ለሰጡት ምላሽ “በእውነት ለመናገር የሰዉ ምላሽ እኔ በሰጠኋቸው መጠን ነው ብዬ አላምንም። እዚህ ላይ የሚታየው አንድ ሰው ለሐገሩ ያለው ፍቅር፣ ለኢትዮጵያዊነት ያለው ፍቅርና በጋራ ለኖረው ነገር ያለው እምነት ነው። ይህን ስሜት የፈጠረው” ብሏል – VOA Amharic 

Continue Reading

Art and Culture

በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ

Published

on

በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ

በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም መስቀልን መናፈቅ በሚል የመስቀልን ድባብ እየተረከልን ነው፡፡ ከዳሞታ ተራራ ግርጌ ከወላይታዎች ጊፋታ የጀመረው ትረካ ዛሬ ወደ ጎፋዎች መንደር ገብቷል፡፡ የጎፋ ጋዜ ማስቃላን ገጽታዎች እንዲህ ይተርክልናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

አልባ ትልቁ ተራራ፣ የካዎቹ ሞገስ ዘመናት ሲሻገር የተመለከተው ባለ እድሜ፤ አሁን የጎፋዎችን መንደር ናፍቆኛል፡፡ ልቤ ማዜ ወንዝ እስኪጎድል ጠብቆ ለመሻገር ትእግስት የለውም፡፡ የውርጭ ተራሮች በልምላሜ በሚያሸበርቁበት በዚህ ወቅት ሳውላ መሆን መታደል ነው፡፡ በዚህ ወቅት ብልቂ መግባት መባረክ ነው፡፡

ከጎፋ ጋር አብሮ ዮ! እንደማለት የዘመን አጋጣሚ የለም፡፡ እዚህ ከሁሉ የሚበልጠው ቀን ማስቃላ ነው፡፡ ዱዛ የሰው ቀልብ የሚስብበት የልምላሜው ወቅት ነው፡፡ የዛላ ዛዬ ሹቻ ናፍቆት ያላዩት ሀገር የሚለውን ይቃረናል፡፡

ያላ ሳውላ የትም ያለን በትዝታ የምትጎትት ከተማ ናት፡፡ የሆሴ ዜማ ጆሮን ሰላሳ ጊዜ ቢያራግፉት ደጋግሞ ማቃጨሉን አያቆምም፡፡ የጋሼ ባህላዊ ጨዋታ ኦ ሆያ ጋሼ ከአብሮነት ትዕይንቱ ጋር ከዓይን ላይ ሳይጠፋ ስለሚኖርበት ምድር ሳስብ ማስቃላን እናፍቃለሁ፡፡

ጎፋ ጋዜ ማስቃላ አይሰለችም፡፡ ዘለዓለም አብሮ የሚኖር ትዝታ ነው፡፡ የጎፋዎች ምርቃት ማስቃላን ዘለዓለም ከመኖር ጋር ይተሳሰራል፡፡

ምኞታቸው በበረከት የተሞላ ነው፡፡ አህያ ቀንድ እስክታበቅል፣ ልጃገረዶች አግብተው እስኪያልቁ፣ ያ ተራራ የኖረውን ዘመን በመኖር መስቀልን ለማየት የሚመኝ ባህል ውስጥ መኖር ጸጋ ነው፡፡

አንድ ቀን በኢትዮጵያ ትልቁ ኩነት ጎፋ ጋዜ ማስቃላ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ያኔ ሩቅ የለም፡፡ ለጋዜ ማስቃላ የመጣ ጎብኚ በዎምባ ፏፏቴ ይጠበላል፡፡ የሊዲ ፏፏቴ ውበት የካሜራ ብርሃኖች ያብረቀርቁበታል፡፡

READ  ኢትዮጵያ በ 2025 ባለመካከለኛ ገቢ ሀገር አትሆንም ተባለ

 

ግንድ አንሳን የሚሳለም፣ ጋልጣ ማርያም ደጃፍ እልል የሚል ብዙ ነው፡፡ በመሎኮዛ ቅመም ያበዱ ምግቦችን እየተመገበ የሀገሬ ሰው መስከረምን እንደ አደይ ጎፋ ላይ ያብባል፡፡ ጎፋ ጋዜ ማስቃላ ይናፍቃል፡፡

ከተራሮች አናት እስከ ማዜ በርሃ መንፈሱ ሁሉ አንድ ነው፡፡

በቶ፣ ጋልማ፣ ቡልቂ፣ ላሃ…..የትም ይሁን ብቻ ማስቃላን አብሮ መሆን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ከዚያ ማስቃላ ገባ ተብሎ ወጣ የለም፡፡
ጎፋ በጊያ ካንሶ አድምቆ ይሸኘዋል፡፡

ማስቃላን ለማሰናበት ባህላዊ ክንዋኔው ሲደምቅ ደቦጭ በና ሆኖ አብሮ በጊያ ካንሶ ትዕይንት በደስታ እንደማበድ መልካም እድል የለም፡፡ የመስቀል ናፍቆት ሩቅ ተጓዥ ነው፡፡

ከደቡብ ስሜን የሚወረውር፣ የጨዋ ሰፈር ደመራን ከገነት ተራራ ስር ከጎንደር ልጆች ጋር እንለኩሳለን፡፡ ኢዮሃ መስከረም፡፡

DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

የካናዳው ፓርላማ አባል ቴዲ አፍሮን አስመልክቶ ለፕሬዝዳንት ሙላቱ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ

Published

on

የካናዳው ፓርላማ አባል ቴዲ አፍሮን አስመልክቶ ለፕሬዝዳንት ሙላቱ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ

“ኢትዮጵያ በየጊዜው ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ ከካናዳ መንግስትና ሕዝብ ታገኛለች። በቅድሚያ ያ እርዳታ በረሃብ አለንጋ ለሚገረፉት ለእነኚያ ለታሰበላቸው ተረጂዎች መድረሱንና የሰዎች መብት መጠበቁን ማረጋገጥ እንሻለን። በእርግጥ የምናየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ግን በተዘዋዋሪም ቢሆን ያን ዓይነት አመኔታ እንድናሳድር የሚያግዝ አይደለም።” ለኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉት የካናዳ ፓርላማ አባል አሌክስ ናዳል።

ድርጊቱ ከተፈጸመ ቀናት ቢያስቆጥርም አሁንም እያነጋገረ ነው። ከጉዳዩ ጋር የሚዛመዱ ሌሎች አዝማሚያዎችን ጨምሮም የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ሰሞኑን በሰፊው ለመዳሰስ የበቃ ርዕስ ነው።

የንግግር ነጻነት በማንም የማይቸር በማንም የማይደፈር ሰብዓዊ መብት ነው፤ ሲሉ ይንደረደራሉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት የቴዲ አፍሮን የሙዚቃ ኮንሰርት መሰረዝ ተንተርሶ ሰሞኑን ለኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉ አንድ የካናዳ ፓርላማ አባል ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት።

Canadian MP Writes Open Letter to President Mulatu in Support of Teddy Afro

The Canadian member of parliament, from Ottawa and serving the people of Barrie-Springwater-Oro-Medonte, wrote open letter to President Mulatu Teshome of Ethiopia in support of Laureate Teddy Afro and in protest against government’s last hour cancellation of the much awaited “Ethiopia” Album Launch that was scheduled for Sunday September 3, 2017. His letter was also for the prior denial of permission to have his concert at the Millenium Hall in Addis Ababa.

MP Alex Nuttall stated in his letter that “Music and arts are an important reflection on the mood a nation.” and concludes that Ethiopian government now stands against the “Canadian values of openness and freedom” by cancelling the concert and album launch party of artist Teddy Afro.

READ  ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኤምባሲ ከፈተች

Laureate Tewodros Kassahun aka Teddy Afro has visited Canada multiple times. At his last visit to Canada Teddy Afro received Ethio-Canadian Heritage Center’s 2017 Award on June 24, 2017 in Toronto, Canada.

Continue Reading

Art and Culture

ዓለም ቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ ለ30ኛ ጊዜ መከበር ጀምሯል

Published

on

ዓለም ቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ ለ30ኛ ጊዜ መከበር ጀምሯል

ሀገር አቀፍን ኩነት የሚያስተናግደው የኦሮሚያ ክልል ነው፡፡

የዓለም ቱሪዝም ድርጅት አባል ሀገር የሆችው ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት የተወሰነውን የዓለም ቱሪዝም ቀን ዘንድሮ ለ30ኛ ጊዜ እያከበረች ነው፡፡

በዓለም ለ38ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው የዘንድሮው የዓለም ቱሪዝም ቀን “ቱሪዝም ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል ይከበራል፡፡

ከዛሬ መስከረም 11 ቀን ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት እስከ መስከረም 16 ቀን 2010 የሚከበረው ይህ በዓል የኦሮሚያ ክልል መስህቦችን የመጎብኘት መርሃ ግብር ጨምሮ የፓናል ውይይቶችን ሌሎች ዝግጀቶችን ያካተተ ነው፡፡

በዓሉን ከቀናት በፊት ማክበር የጀመረው የደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ እና በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በመጎብኘት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ሲሆን አማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞን ላይ በተመሳሳይ መልኩ በዚህ ወር መጨረሻ ለማክበር ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡ DIRETUBE

READ  ለዓለሙ የተረፈው የሰው ኃይል እውን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቴሌቭዥን አንሶ ነው?
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close