Connect with us

Economy

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ሀያ በመቶ የሚጠጋ ድርሻ መውሰዷ ተዘገበ

Binyam G-Kirstos

Published

on

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ሀያ በመቶ የሚጠጋ ድርሻ መውሰዷ ተዘገበ

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ሀያ በመቶ የሚጠጋ ድርሻ መውሰዷ ተዘገበ – ባለፉት ቀናት ግንባታው ይፋ የሆነውንና በሶማሊላንድ የሚገኘውን የበርበራ ወደብ ዱባይ ፖርትሰ የተባለ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ለ30 አመታት በኮንትራት መውሰዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኢቨስትመንት ድርሻ መግዛቷን የሶማሊላንድ መንግስት አስታወቀ።

ከሶማሊያ ራሷን በመገንጠል ነፃነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ በማንም ሀገር እስካሁን እውቅና አልተሰጣትም።

ከ 444 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪየተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ዱባይ ፖርትሰ በተሸኘው ሳምንት የበርበራን ወደብ ተረክቧል።  ኩባን ያው 65 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ቀሪውን 35 በመቶ የሶማሊላንድና የኢትዮጵያ መንግስት ይወስዳሉ። የኢትዮጵያ ድርሻ 19 በመቶ ነው።

ዘግይቶ በተነገረ መረጃ ደግሞ ለኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ የሰጠው ዱባይ ፖርትሰ እንጂ የሶማሊላንድ መንግስት አይደለም ሲሉ አንዳንድ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ተከራክረዋል። የሶማሊላንድ ድርሻ 35 በመቶ ሲሆን ዱባይ ፖርትሰ ካለው 65 በመቶ ድርሻ 19 በመቶ ለኢትዮጵያ ሸጧል ብለዋል።

የጅቡቲን ወደብ የሚያስተዳድረው ራሱ ዱባይ ፖርትሰ በተደጋጋሚ በወደብ መጠቀሚያ ዋጋ ላይ ያደረገው ጭማሪ ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ሆነች ኢትዮጵያ ከራስ አገዟ ሶማሊላንድ መንግስት ጋር የሚያደርጉት ውል የሶማሊያ ፌደራል መንግስትን ሉዓላዊነት የሚዳፈርና ህገ ወጥ ነው በሚል የሞቃዲሾ መንግስት ተቃውሞውን አሰምቷል። የበርበራ ወደብ በተመረቀበት ወቅት የኢትዮጵያ ሚንስትር የሚመሩት የልዑካን ቡድን በቦታው ተገኝቶ ነበር – ዋዜማ ራዲዮ

READ  BREAKING NEWS: The Federal Government Has Declared a State of Emergency
Continue Reading

Business

በአዲስ አበባ የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት እድለኛ ለሆኑ ግለሰቦች በዛሬው እለት የቁልፍ ርክክብ ይደረጋል

Published

on

በአዲስ አበባ የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት እድለኛ ለሆኑ ግለሰቦች በዛሬው እለት የቁልፍ ርክክብ ይደረጋል

በአዲስ አበባ 972 የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት እድለኛ ለሆኑ ግለሰቦች በዛሬው እለት የቁልፍ ርክክብ ይደረጋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛጉዬ ህንጻ በሚገኘው ቅርንጫፍ ነው ለባለእድለኞች ርክክቡ የሚደረገው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሚኒኬሽን ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታከለ ለኤፍ.ቢ.ሲ እንደገለፁት፥ ከቁልፍ ርክክቡ ባሻገር እድለኞቹ ቤቶቹን በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲገለገሉባቸው ለማስቻልም የራሳቸውን ማህበር እንዲያደራጁም ይደረጋል።

በቁልፍ ርክክቡ ወቅት ከቤቶች ኢንተርፕራይዝ፣ ከማህበራት ማደራጃ እና ከባንኩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

READ  መርጡለ ማርያም ሙዚየም፤ የኢማም አህመድ /ግራኝ መሐመድ/ ካባ በክብር የተቀመጠበት ስፍራ
Continue Reading

Business

ከ100 በላይ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የፋይናስ መመሪያ በመጣስ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርገዋል

Published

on

ከ100 በላይ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የፋይናስ መመሪያ በመጣስ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርገዋል

ከ100 በላይ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የፋይናስ መመሪያ በመጣስ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸው ተገለፀ።

የተቋማቱ የውስጥ ኦዲተሮች ተጠሪነታቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከሆኑ በኋላ በ10 ወራት ውስጥ በቀረበለት የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ነው ጥስቱ የተገኘው።

በ2009 ዓ.ም ነው ተጠሪነታቸው ለፌደራል መንግስት የሆኑ ተቋማት የውስጥ ኦዲተሮች ለተቋሙ የስራ ሃላፊ የነበራቸውን ተጠሪነት በማንሳት ለገንዝብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንዲሆኑ መንግስት የወሰነው።

በገንዝብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኢንስፔክሽን ዳሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር ለለኤፍ.ቢ.ሲ እንደተናገሩት፥ አሰራሩ ለውጥ አምጥቷል።

በዚህም የፋይናስ መመሪያ የጣሱ 122 ተቋማት ተገቢ እርምት እንዲያደረጉ ማስጠንቀቂያ ተጽፎባቸዋል ብለዋል።

በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጠቅላላ አስተዳደር ላይ ከሚገኙት ከእነዚህ ተቋማት የተወሰኑት ማስጠንቀቂያው ተከትለው ማስተካከያ አድረገዋል።

ቀሪዎቹ ከ100 በላይ ተቋማት ግን ማስተካከያ አላደረጉም ብለዋል።

የፋይናስና የግዥ መመሪያ በመጣስ የመንግስት ገንዘብ ከመጠቀም ጀምሮ የጥሬ ገንዘብና ሌሎች ጉድለቶች የታየባቸው መሆኑንም አቶ ፍቃዱ አንስተዋል።

በ18 ተቋማት ከ2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት በውስጥ ኦዲት ተረጋግጦባቸዋል።

ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን፥ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ 2 ሚሊየን ብር የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ነው የተገኘበት ብለዋል።

በህግ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረጉና አሁን በህግ ጉዳያቸው እየታዩ ያሉ አሉም ነው ያሉት የኢንስፔክሽን ዳሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር።

በ41 ተቋማትም በጊዜው መወራረድና መስብስብ የሚገባው ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በውስጥ ኦዲት መገኝቱን አቶ ፍቃዱ ያነሳሉ።

ለጥቃቅን ውጪ በመስሪያ ቤቶች በካዝና 100 ሺህ ብር እንዲያዝ በፋይናንስ መመሪያ ቢቀመጥም የመንግስት ሃብት ለአደጋና ብክንት በሚያጋልጥ መልኩ መያዙም ተረጋግጧል።

READ  Ethiopia: OPDO sacks chairperson, deputy

በ9 ተቋማት ከ7 ሚሊየን 431 ሺህ ብር በላይ ከተፈቀደው መጠን ውጪ በካዝና በመያዝ ተገኝቷል።

አራት ተቋሞች በገቢ ግብር፣ ቀረጥ እና አዋጅ ደንብና መመሪያ መሰረት ግለሰቦችና ተቋማት ከሚያገኙት ገቢ መስብሰብ የነበረበት ከ9 ሚሊየን 875 ሺህ ብር በላይ ሳይሰበስቡ ቀርተዋል።

ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እና ንብረት በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያሳትመው ደረሰኝ ገቢ መስብሰብ ሲኖርበት ይህን ባለማድረግ አራት ተቋማት በሚሊየን የሚቆጠር ገንዝበ የመስብሰብና ንብረት አስገብተዋል ነው ያሉት ዳሬክተሩ።

ተቋማት ለሚያወጡት ወጪ ተገቢውን ማስረጃ ወይም የወጪ ምክንያት መዝግበው መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

በ16 ተቋማት ግን ለወጪው የተማሏ ማሰረጃ ሳይቀርብ 60 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ በውስጥ ኦዲተሮች በተደረገ ማጣራት ተረጋግጧል።

መንግስት ለሀገሪቱ ከሚመድበው 69 በመቶ ለግዥ እንደሚውል የሚናገሩት አቶ ፍቃዱ፥ የውስጥ ኦዲተሮች ከፍተኛ ክትትል እንዲያድረጉ መመሪያ በሚኒስቴሩ ተሰጥቷል።

በዚህም በ14 ተቋማት በ100 ሚሊየን የሚቆጠር ገንዝብ የግዥ መመሪያ ጠብቆ መከፈል ሲገባው ይህ ሳይሆን ቆይቷል ብለዋል።

ከግዥ በተጨማሪም በ13 ተቋማት ከ8 ሚሊዮን 412 ሺህ ብር በላይ መከፈል ከሚገባው በላይ ክፍያ ተፈፅሞ ተገኝቷል።

እነዚህ ተቋማት 13 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ፥ ሐዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ብርሃን፣ ጎንደር፣ አዳማ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውም ታውቋል።

የፋይናስ እና የግዥ መመሪያ በመጣስ ጉድለት የታየባቸው ተቋማት ግድፈቱን እንዲያስተካክሉ ተጠይቀዋል።

ይሁንና የተወሰኑት ብቻ ሲያስተካክሉ በርካታዎቹ የእርምት እርምጃ ባለመውሰዳቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቤኔ ተልኮ ውሳኔ እየተጠባበቀ ይገኛል ተብሏል። ኤፍ.ቢ.ሲ

Continue Reading

Business

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል – ጠ/ሚ ኃይለማሪያም

Published

on

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ እንደሚቀጥል እና ኢትዮጵያ ለአካባቢዋ አበክራ እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒሰትር ኃይለማሪያም ገለፁ፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከሚስዮን መሪዎች እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ጋር ትናንት ባደረጉት ውይይት ዲፕሎማቶች በሁለተኛው እድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተቀመጠው መሰረት በተመረጡ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ባለሃብቶችን ለማፈላለግና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማሳለጥ የተጠናከረ እቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የማስፈፀም አቅሙን መገንባት እንደሚኖርበት እና በበቂ ጥናት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለበትም ጠ/ሚ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ከሌሎች ከፍተኛ እና የምርምር ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት አለበት ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቷን ግንኙነት የውጭ እቅስቃሴ በተመለከተ ምሁራን፣ ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች በአጠቃለይ ህብረተሰቡ በቂ መረጃ እንዲኖራቸው የኮሚኒኬሽን እና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራ መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን በኢጋድ ጥላ ስር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚስዮን መሪዎች እና የመስሪያ ቤቱ የበላይ አመራር ነሀሴ 25 እና 27 በአዲስ አበባ እንዲሁም ከነሀሴ 28 አስከ ጳጉሜ 3/2009 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ በባለፈው በጀት ዓመት በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች እና በዚህ ዓመት መከናወን በሚገባቸው አንኳር ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ይታወሳል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
መስከረም 2 ቀን 2010 ዓ.ም.

READ  የሌላ ሰውን ስራ በሽያጭ ወይም በኪራይ ቅጂን የማካፈል እና የማብዛት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እሥራት ተቀጣ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close