Connect with us

Tech & Science

ተመራማሪዎች ከመደበኛው ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን የሚያሳድግ ሰው ሰራሽ ማህፀን ሰሩ

FanaBC

Published

on

ተመራማሪዎች ከመደበኛው ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን የሚያሳድግ ሰው ሰራሽ ማህፀን ሰሩ

ተመራማሪዎች ከመደበኛው ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን የሚያሳድግ ሰው ሰራሽ ማህፀን ሰሩ – የፊላደልፊያ የህጻናት ሆስፒታል እና የኤደንብራ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ከመደበኛው የወሊድ ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን በፅንስ መልኩ እንደ አዲስ በመደበኛ ሁኔታ የሚሳድግ አዲስ ሰው ሰራሽ ማህፅን ሰርተዋል፡፡

http://www.youtube.com/watch?v=-oCCqqeYPxM

ተመራማሪዎቹ “ባዮ ባግስ” የተባለውን ማህፀን የ23 ሳምንት እድሜ ካለው የሰው ጽንስ ጋር እኩል እድሜ ያለው የበግ ሽል እንዲያሳድግ ሞክረውት ውጤታማ ሆኗል ብለዋል።

ሽሉ ባግስ ከተሰኘው ሰራሽ ማህጸን ውስጥ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ቪዲዮም ተመራማሪዎቹ ለቀዋል፡፡

ሙከራውም ያለ እድሜያቸው ከ21 እስከ 23 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚወለዱ እና መደበኛ የአካል እድገት የማይታይባቸው ህጻናት ከእናታቸው ማህፀን ውጭ በቂ የሆነ እድገት እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ከመደበኛው የእንስሳት ሽል ማሳደጊያ ወይም ኢንኩቤተር የተለየ ሆኖ የተሰራው ሰው ሰራሽ ስነህይወታዊ ማህፀን፥ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ወይም በእድገት አለመመጣጠን ምክንያት ህመም ውስጥ ያሉ ፅንሶችን በእንክብካቤ ለማሳደግ ይረዳል ተብሎለታል፡፡

ሰው ሰራሽ ማህፀኑ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም ወደ ሙከራ ተግባር እንደሚገባ ነው የተተነበየው፡፡

ማህፀኑ ሙሉ የእርግዝና አገልግሎቶችን ወይም ሙሉ ፅንስ የማሳደግ አገልግሎት የማይሰጥ ሲሆን፥ ከመደበኛው ወሊድ ጊዜ ቀድመው የተወለዱ ህጻናትን እንደገና በፅንስ መልኩ የቀራቸውን እድገት እንዲያሟሉ የማድረግ ተግባር ነው የሚሰጠው፡፡

በሰውሰራሽ ማህፀኑ ውስጥም ህጻኑ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለት አይኖቹን እንዲገልጥ፣ እንደማንኛውም ፅንስ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲተነፍስ እና ምግብ እንዲገኝ ሆኖ የተሰራ ነው – FBC

READ  ዘንድሮ በደብሊን በተካሄደው በምስጠራ ቴክኖሎጂ ውድድር የ16 ዓመቱ ታዳጊ ተሸላሚ ሆኗል
Continue Reading

Business

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም

Published

on

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም እስከ መስከረም 14 ቢባልም ቁጥር የሌላቸው ሞባይሎች በተሰጠው ቀነ ገደብ ተጠቅመው አልተሳካላቸውም፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

ኢትዮ-ቴሌ ኮም የስልክ ቀፎአችንን ልመዝገብ ብሎ ሲያውጅ ጉዳዩ ብዙም አልገባን ነበር፡፡ አንዲት ጓደኛዬ ደውላ እስክታስረዳኝ እና ባታስመዘግቢ ይዘጋል እስክትለኝ መልዕክቱ በደንብ አልገባኝም ነበር፡፡ ያው አሁን በስራ ላይ ያሉ ስልኮች በሙሉ በአሉበት ተመዝግበዋል ተባልን፡፡

ለካ የተቀመጠ፣ ሱቅ የተደረደረ፣ ስጦታ መጥቶ ቻርጀር የጠፋለት ብዙ ብዙ ዓይነት ሞባይል ቀፎ የተባለው ካልተደረገ እንደሌለ ይቆጠራል፡፡ ይሄ ሲሰማ ሰው እንዴት ነው ብሎ መጠየቅ ጀመረ፡፡

ቴሌም በተገልጋዩ በቀረበው ጥያቄ መሰረት እስከ መስከረም 17 ቀን ተራዝሟል ሲል ማስታወቂያ ለቀቀ፡፡ አሁን ብዙ ሰዎችን ያሳዘነው በማስታወቂያው መሰረት እስከ ቀኑ እድላቸውን ለሞመከር ሲጥሩ ቀፎው መዘጋቱና አገልግሎት ለመስጠት አለመቻሉ ነው፡፡

ከተባለው ቀነ ገደብ በፊት የልቡን ያደረሰው ቴሌ ቃሉን ይጠብቃል ብለው ያመኑት ሜዳ ላይ ቀርተዋል፡፡ ምናልባት ሲስተም አሊያም ሌላ ምክንያት ወይም ቃሌን ለምን አከብራለሁ፡፡
ጎን ለጎን የቆመ ሰው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው ስል ኖሬስ የለም ውሸት ምኑ ያስፈራል አይነትም ይሆናል፡፡

በርካታ የሞባይል ቀፎ ነጋዴዎች ጉዳዩ አሳዝኖአቸዋል፡፡ አሁን ገና ሀዘን ላይ ናቸው፡፡ ከዚያ ደግሞ ኪሳር አለ፡፡ እንዲህ ለምን እንደሆነ ምላሽ የሚሰጣቸው እንኳን አላገኙም፡፡ ግን ሆኗል፡፡

ኢትዮ ቴሌ ኮም ቃል በገባው መሰረት አራዘምኩ ባለው ቀን ድረስ ምዝገባውን አላራዘመውም፡፡ ቀጣይ የሚሆነውን አብረን እናያለን፡፡

ሚሊዮኖች ይከስሩና አንጋፋው አትራፊ ድርጅት በትርፋማነቱ ቀጥሏል የሚለውን ዜና እናነብ ይሆናል፡፡ በበኩል አንድ ነገር ቢደረግ ደስ ይለኛል፡፡ ጉዳዮን ኢትዮ ቴሌ ኮም መልሶ ቢመለከተው እና እውን የተባለው ችግር ዝም ተብሎ የሚታለፍ ነው ብሎ ራሱን ቢጠይቅ፡፡ DIRETUBE

READ  ፈረንሳይ የሽብርተኞችን ድሮኖች የሚያድኑ አሞራዎችን አሰልጥና ልታሰማራ ነው

Continue Reading

Business

ጠቃሚ መረጃ ስለአዲሱ ሞባይል ምዝገባ | (አዲሱ ሲስተም) አሰራር የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

Published

on

ጠቃሚ መረጃ ስለአዲሱ ሞባይል ምዝገባ

1. የምዝገባው ጊዜ አልፎብኛል እስካሁን ያልተጠቀምኩበትን ቀፎ እንዴት ወደ አገልግሎት ማስገባት እችላለሁ ?

መልስ:- የተሰጠው የምዝገባ የጊዜ ገደብ በማለፉ ሲስተሙ ተግባራዊ ሆኗል በመሆኑም ከዚህ በኋላ ደንበኞችም ሆኑ በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪዎች፤ ሻጮች እና አከፋፋዮች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ መመሪያ አንቀፅ ስድስት ስለ መሣሪያዎች ምዝገባ እንደሚከተለው ይስተናገዳሉ፤ በመሆኑም ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ አሰራር ውስጥ ፍቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቶች በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡

1. አስመጪዎች ወይም አምራቾች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ለሚኒስቴሩ በማመልከት ማስመዝገብ አለባቸው፡፡

2. ከውጪ ሀገር በግለሰብ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ የሞባይል ስልክ ቀፎ በጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያዎች መመዝገብ አለበት፡፡

3. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎ ምዝገባ ማከናወን የሚችሉት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ሂደት ላይ እያሉ ወይም የማምረት/የመገጣጠም ሥራው ሲጠናቀቅ ብቻ ነው፡፡

4. የምዝገባ ሥርዓቱ የ IMEI ቁጥራቸው በጥቁር መዝገብ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር የሮሚንግ አገልግሎት ስምምነት ባላቸው ግለሰቦች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

5. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም በሀገር ውስጥ የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ለማስመዝገብ ሲያመለክቱ የሚከተሉትን ሰነዶች ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሀ/. የሞባይል ስልክ ቀፎዎቹ የገቡበትን ወይም የተመረቱበትን/የተገጣጠሙበትን ቀን፣ የመሣሪያዎቹን ስሪት፣ ሞዴል እና ብዛት የጠቀሰ እንዲሁም ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት የማመልከቻ ደብዳቤ፣
ለ/ የንግድ ፈቃድ
ሐ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
መ/ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን፣
ሠ/ የኤርዌይ ቢል ወይም የማስጫኛ ሰነድ፣
ረ/ የተመረተበት ሀገር ሠርተፊኬት፣
ሰ/ ኮሜርሻል ኢንቮይስ፣
ሸ/ ፓኪንግ ሊስት፣
ቀ/ የመሣሪያ ምዝገባ ስርዓቱ በሚቀበለው የኖትፓድ ፋይል ፎርማት መሠረት የተዘጋጀ የ IMEI ቁጥሮች ዝርዝር የያዘ CD ወይም ፍላሽ ዲስክ፣

READ  “2 ጊዜ 4”... ተማሪዎችን እያስጨነቀ ነው!

6. በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡

ጥያቄ:- በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡና በአከፋፋዮች መጋዘን ወይም በችርቻሮ መሸጫ መደብሮች የሚገኙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች እንዴት ይስተናገዳሉ?
መልስ:- በመመሪያው መሠረት በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡና በአከፋፋዮች መጋዘን ወይም በችርቻሮ መሸጫ መደብሮች የሚገኙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች የ IMEI ቁጥራቸው ተመሳስሎ ያልተሰራ፣ ያልተባዛ ወይም ትክክለኛ ሆኖ ከተገኘ በነጭ መዝገብ ይመዘገባሉ፡፡ አከፋፋዮች ወይንም ቸርቻሪዎች ግዚ በፈጸሙባቸው ህጋዊ አስመጪዎች ወይም አምራቾች በኩል ጥያቄያቸውን ለፈቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቶች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን ማነጋገር ይችላሉ፡፡

ጥያቄ:- የሞባይል ቀፎ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በሱቃችን ያሉ አዳዲስ ቀፎዎች የወደፊት እጣ ፋንታ ምንድነው?
መልስ:- ከላይ በተመለከተው መመሪያ መሠረት ያለህጋዊ አሰራር በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም ከነዚህ ተቋማት በህጋዊ አሠራሩ መሠረት መስተናገድ ይችላሉ

ጥያቄ:- አዲስ ቀፎ መግዛት የሚፈልጉ ደንበኞች ቀፎው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?
መልስ:- አዲስ የሞባይል ቀፎ ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ሲገዙ በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ለማወቅ :-
· ሲም ካርድ አስገብተው ለሙከራ መጠቀም
· *868# ደውለው 3ኛ ቁጥር ላይ የሚገኘውን የመለያ ቁጥር ሁኔታ ማወቂያ (Check Status) የሚለውን መምረጥ ፤ በመቀጠል by IMEI የሚለውን መርጠው፤ ሊገዙ ያሰቡትን የቀፎ መለያ ቁጥር /IMEI/ አስገብተው ቀፎው በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
· የሚገዙትን ቀፎ የIMEI ቁጥር ለማወቅ፡
· *#06# ይደውሉ
· ከቀፎው ማሸጊያ ካርቶን ላይ ይመልከቱ፡፡
እዚህ ላይ የሚታዩ ስታተሶች
· የተሳሰረ/Locked – ከዚህ ቀደም ተመዝግበው አገልግሎት ላይ ያሉ ሁሉም የሞባይል ዲቫይሶች ሎክድ የሚል ስታተስ ያሳያሉ ይህም አሁን የሚገለገሉበት ሲም ካርድ እና ቀፎ መተሳሰሩን ያሳያል፡፡
· ያልተሳሰረ/Un-Locked – ቀፎው አሁን ካለበት ሲም ካርድ ጋር ያልተሳሰረ እና ሌላ ሲም ካርድ መቀበል የሚችል
· የተፈቀደ/Autorized – መመሪያውን ተከትለው ፈቃድ ያገኙ ቀፎዎች ሆነው በማንኛውም ሲም ካርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ
· ያልተፈቀደ/Unautorized – ፈቃድ ያላገኙ አና የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ላይ መስራት የማይችሉ ቀፎዎች

READ  ዘንድሮ በደብሊን በተካሄደው በምስጠራ ቴክኖሎጂ ውድድር የ16 ዓመቱ ታዳጊ ተሸላሚ ሆኗል

5. የሞባይል ቀፎዬን ወደሌላ ለማዛወር (ሌላ ሲም ካርድ ለመጠቀም) ምን ማድረግ አለብኝ?
አማራጭ 1
· ደንበኞች በቀላሉ ስልካቸውን በማጥፋት ወይም ስዊች ኦፍ በማድረግ ሌላ ሲም ካርድ አስገብተው መጠቀም ይችላሉ
አማራጭ 2
· በ USSD *868# በመደወል (በ5 ቋንቋዎች በአማርኛ እንግሊዝኛ ትግርኛ ኦሮምኛ እና ሶማልኛ) አገልግሎት ይሰጣል
· Unlock/ ቀፎ ነጻ ማድረግ የሚለውን በመምረጥ ማላቀቅ እና በሌላ ሲም ካርድ መጠቀም ይችላሉ
· በአጭር የጽሁፍ መልእክት ወደ 868 A ወይም ባዶ መልእክት በመጻፍ መላክ
ሆኖምተመሳስለው የተሰሩ፣ የተባዙ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የ IMEI ቁጥሮች ያላቸው የሞባይል ስልክ ቀፎዎች አሁን ባለበት ሲም ካርድ ብቻ መስራት ይችላሉ (ሌላ ሲም ካርድ መቀበል አይችሉም)

6. ተመሳስለው የተሰሩ/የተዳቀሉ ቀፎዎች ቀጣይ እጣፈንታ ምንድነው?
· ተመሳስለው የተሰሩ፣ የተባዙ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የ IMEI ቁጥሮች ያላቸው የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ይህ መመሪያ ከጸናበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በትክክለኛ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች መተካት ይኖርባቸዋል።

ምንጭ:- ኢትዮ ቴሌኮም

Continue Reading

Ethiopia

ከውጭ መጥተው ያልተከፈቱ ስልኮች የጉምሩክ ስነስርዓት ከፈጸሙ ወደ አገልግሎት መግባት ይችላሉ

FanaBC

Published

on

By

ኢትዮ ቴሌኮም

(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በኢትዮጵያ ኔት ወርክ ላይ እንዲመዘገቡ የሰጠው ጊዜ አነስተኛ መሆን በጥገና ላይ ያሉ እና ከውጭ ሀገራት መጥተው ያልተከፈቱ ስልኮችን ከጥቅም ውጭ በማድረጉ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ በመርካቶና በተለምዶ አውቶብስ ተራ በመባል በሚታወቀው አካባቢ በሞባይል ሽያጭና ጥገና ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ናቸው።

የቅሬታቸው መነሻም ሰሞኑን ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ያደረገው አሰራር አዲስ ወይም ካለ ጥቅም የቆዩ የተንቀሳቃሽ የስልክ ቀፎዎች በአራት ቀናት ውስጥ ባለቤቶቻቸው በሞባይል ቀፎዎቹ፥ ሲም ካርድ በመክተት በኢትዮጵያ ኔትወርክ ላይ የስልክ ቀፏቸውን እንዲያስመዘግቡ የሚያደርግ ነው።

ኩባንያው በተለያዩ መገናኛ ብዙሀንና በአጭር የጽሁፍ መልእክት ደንበኞቹ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ሲያስተዋውቅ ቆይቷል ።

ይሁን እንጂ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥገና ባለሙያዎች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተሟላ ግንዛቤ ስላልነበረን፥ ጥገና ላይ የሚገኙና ከውጭ ሀገራት መጥተው ሊከፈቱ የተዘጋጁ ስልኮች በኢትዮጵያ ኔትወርክ ባለመመዝገባቸው ለኪሳራ መዳረጋቸውንና ከደንበኞቻቸው ጋር ግጭት ውስጥ እንደከተታቸው ነው የተናገሩት።

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩን አቶ አብድራሂም አህመድ፥ የተተገበረው አሰራር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የሞባይል ህብረት ተቋም ውስጥ በአባልነት የምትገኝ በመሆኗ ዓለም አቀፉን አሰራር ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ነው ብለዋል።

ህገወጥነትን ለመከላከልና ሀገሪቱን ከኮንትሮባንድ ንግድ ለመከላከል ከዘርፉም ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላልም ሲሉ ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ የተሰጠው ጊዜ ምን ያህል በቂ ነው? በቀናት ጊዜ ውስጥስ በተጠቃሚው ህብረተሰብ ዘንድ ግንዛቤውን በመፍጠር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል ወይ? ስንል አቶ አብድራሂምን ጠይቀናል።

READ  የሰዎችን ስራ የሚወስዱ ሮቦቶች ግብር ሊከፍሉ ይገባል- ቢል ጌትስ

ነባር ተጠቃሚ ሆነው በኢትዮጵያ ኔት ወርክ ላይ የተመዘገቡትን 58 ሚልየን ደንበኞችን፥ አሰራሩ በራሱ ወደ ምዝገባ ስርዓት ያስገባቸው በመሆኑ የምዝገባ ስርዓቱ እንደማይመለከታቸው ነው የተናገሩት።

ሆኖም ግን ተጨማሪና አዲስ የስልክ ቀፎዎች በእጃቸው ያሉ ደንበኞች ግን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሲም ካርድ በመክተት በኢትዮጵያ ኔት ወርክ እንዲመዘገብ ጥሪ ቀርቧል ይላሉ አቶ አብድራሂም።

ለዚህ አገልግሎትም ደቂቃዎች በቂ በመሆናቸው ጊዜው አነሰ ሊባል አይችልም ብለዋል።

ይሁን እንጂ አሰራሩን ተከትሎ ጣቢያችን ያነጋገራቸውና በስልክ ቀፎዎች ጥገና የተሰማሩ ባለሙያዎች ጥገና ላይ ያሉና ሀገር ውስጥ የገቡ አዳዲስ ስልኮችን ማስመዝገብ ባለመቻላቸው ለኪሳራ ሊጋለጡ እንደሚችሉ መስጋታቸውን ጠቁመዋል።

አቶ አብድራሂም በምላሻቸው በጥገና ላይ ያሉት የተንቀሳቃሽ የስልክ ቀፎዎች አስቀድመው፥ በኢትዮ ቴሌኮም ኔት ወርክ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ከሆነ ከጥገና በኋላም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

ያልተከፈቱ ስልኮች ግን በኢትዮጵያ አገልግሎት እንዳይሰጡ የተዘጉ በመሆናቸው አልያም የጉምሩክ ስነስርዓት ያልፈጸሙ በመሆናቸው ወደ አዲሱ አሰራር እንዳልገቡ ነው የተናገሩት።

ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ ኢትዮጵያውያንም የተንቀሳቃሽ የስልክ ቀፎዎችን ይዘው ሲመጡ፥ የጉምሩክ ስነ ስርዓትን እስካልፈጸሙ ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ነው አቶ አብድራሂም ያስገነዘቡት።

የትኛውም የተንቀሳቃሽ ስልክ አንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ከተመዘገበ በኋላ፥ መሸጥም ሆነ በስጦታ መልክ መለዋወጥ እንደሚቻል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። FBC

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close