Connect with us

Africa

ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ

VOA Amharic

Published

on

ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ

ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ

ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡

ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡የኢዮጵያው ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በበኩላቸው የሱዳንና የኢትዮጵያ ግንኙነት ለአካባቢው ሀገሮች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ገልፀው እነዚህ የአካባቢው ሀገሮች በአስቸኳይ ውህደት እንዲፈጥሩ አሳሰቡ፡፡

ሁለቱ መሪዎች ትናንት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገኝተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫቸው በሁለትዮሽ ግንኙነታቸውና በአካባቢው ግንኙነታቸው አተኩረዋል፡፡ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው አኳያ በንግድ ለመተሳሰር ስምምነት መፈራረማቸውን ገልፀዋል፡፡ VOA Amharic 

READ  Ethiopia declares mourning for loss of lives at Irecha Festival
Continue Reading

Africa

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፓርላማ የጉድኝት ሰነድ ተፈራረሙ

Published

on

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፓርላማ የጉድኝት ሰነድ ተፈራረሙ

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የኢጋድ ፓርላማ ህብረት (IPU-IGAD) የወቅቱ ሊቀመንበር በአቶ አባዱላ ገመዳ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከመስከረም 6-8/2010 ዓ.ም ድረስ በካርቱም በተካሄደው የኢጋድ ፓርላማ ህብረት ስብሰባ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።

በስብሰባው ወቅት በድርቅ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላም እና በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በኢጋድ አባል አገራት ልማት፣ ሰላም እና ዲሞክራሲ እንዲመጣ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ እና እየታዬ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥ ጫና፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ግጭት አሁንም ቀጣናው ያልተሻገራቸው ፈተናዎች መሆናቸውን አቶ አባዱላ ገልጸዋል።

እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እና ለመቅረፍ የየአገራቱ ፓርላማ አባላት እንዲሁም ፈጻሚ የመንግስት አካላት ቁርጠኝነትና ትብብር ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲወገድ፣ ልማት እንዲፋጠን በጋራ መረባረብ፣ በመሠረተ ልማት የተጀመረው ትስስር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱማሊያ በፓርላማ ልዑካን ቡድን ሲሳተፉ ኬንያ እና ኡጋንዳ ደግሞ የፓርላማ ልዑክ ባለመላካቸው በሱዳን ባሉ የአገራቱ አምባሳደሮች በኩል ተሳትፎ አድርገዋል።

የቀጣይ የኢጋድ ፓርላማ ህብረት ስብሰባ በጅቡቲ እንዲካሄድ ተወስኗል።

ከብሰባው ጎን ለጎን በኢትዮጵያ እና በሱዳን ያለው የኢትዮ-ሱዳን ፓርላማ ወዳጅነት ቡድን በኢፊዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ እና በሱዳን ሪፐብሊክ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ፕሮፌሰር ኢብራሂም አህመድ ኡመር አማካኝነት የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

አፈ ጉባኤዎቹ ስምምነቱ ለዘመናት የቆየውን የሁለቱ አገራት ጠንካራ ወዳጅነት በአስተማማኝ ደረጃ ለማስቀጠል ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን በመግለጽ ለተግባራዊነቱ ትኩረት ሰጥተን መንቀሳቀስ አለብን ብለዋል፡፡

READ  ቆሻሻስ ሞራል የሌለው ሰው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም.

Continue Reading

Africa

የኦማን ሞተር ሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባለው ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ

Published

on

የኦማን ሞተር ሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባለው ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ

የኦማን ዜግነት ያላቸው ሀገር ተሻጋሪ ሞተርሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባሉ የቱሪዝም መስህቦችና ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ የገቡት ዘጠኝ ሞተር ሳይክለኞች ሲሆኑ ‹‹የኦማን የጋላቢዎች ክለብ›› በሚል የሚታወቅ ማህበር አባል ናቸው ተብሏል፡፡

የሞተር ሳይክለኞቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በሀገሪቱ የእንግዳ አቀባበል ባህል፣ ሰላም እና ታሪካዊ መስህቦች መደነቃቸውን በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ውብ የሀገሪቱ ገጽታዎች በተገቢው መንገድ ለሌላው አለም ሊተዋወቁ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ሞተር ሳይክለኞቹ በቀን ከ500 እስከ 800 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ጉዞ በማካሄድ በአጠቃላይ 14 ሺህ ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ ተብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ድረስ የሚዘልቀው የሞተረኞቹ ጉዞ 14 ሀገሮችን የሚሸፍን መሆኑ ተመልክቷል፡፡

READ  Ethiopia Set to Fund New Infrastructure
Continue Reading

Africa

አደገኛ ዕጾችን ሲያዘዋውር የተያዘዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

Published

on

አደገኛ ዕጾችን ሲያዘዋውር የተያዘዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

ተከሳሽ ሚስተር ሲሞን ፆኪር በፈፀመዉ የተከለከሉ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬከቶሬት ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጣ::

ተከሳሽ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሲሆን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግቢ ውስጥ ከብራዚል ሳኦወፖሎ በተነሳው አውሮፕላን ትራንዚት ላይ ከቶጎ ሎሜ ተነስቶ ወደ ሮዋንዳ ኪጋሊ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትራንዚት ሲያደርግ በተደረገ ፍተሻ መጠኑ 2,690 ግራም የሚመዝን የኮኬን እፅ በላስቲክ የተጠቀለለ በልብስ ሻንጣ ውስጥ አድርጎ ለማለፍ ሲሞክር የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው የተከለከሉ እጾችን ማዘዋወር የወንጀል ህግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ለተከሳሹ ክሱ ደርሶት እና በችሎት ተነቦለት በአስተርጋሚ እየታገዘ እንዲረዳዉ ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ የተጠየቀዉ ተከሳሽ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክራል::

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ለጉዳዩ ያስረዱልኛል ያላቸዉን ምስክሮች ቀርበው እንዲሰሙ እና የሰነድ ማስረጃው ተገናዝቦ ብይን እንዲሰጥ በማለት ለችሎቱ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመመልከት ተከሳሹን በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል::
የቅጣት አስተያያት የተጠየቀዉ ዐቃቤ ህግም የወንጀሉ አፈፃፀምና ይዞ የተገኘዉን የኮኬን ዕፅ መጠኑ ሲታይ ደረጃዉ መካከለኛ ተይዞ ተከሳሹን ሊያስተምር ሌሎችንም ሊያስጠነቅቅ የሚችል ¸ቅጣት እንዲወሰን ሲል አቅርቧል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ድርጊቱን ማመኑ ሪከርድ የሌለበትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በማቅለያነት በመቀበል ነሀሴ 18 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ10 አመት ጽኑ እስራትና በሃያ አምስት ሺ ብር /25000 ሺ ብር/ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል ሲል የመረጃ ምን ጫችን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቦአል፡፡ DIRETUBE

READ  በለንደን የአለም ሻምፒዮና ተሳታፊ የሚሆነው የኢትዮጵያ ቡድን አባላት ከሆቴላቸው ውስጥ ተዘረፉ

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close