Connect with us

Environment

በመንገድ ሥራ ምክንያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ

Binyam G-Kirstos

Published

on

በመንገድ ሥራ ምክንያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ

በመንገድ ሥራ ምክንያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ – ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ

ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ አራት ዓመታት መቆጠሩን አርሶ አደሮቾ ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸውም በምሬት ይናገራሉ።

በደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመንገድ ሥራ ምክንያት ከመሬታቸው መፈናቀላቸው፣የእርሻ መሬታቸው ከነ እርሻ ሰብሉ መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸው ገለጹ። ይህንን አቤቱታ ለአራት ዓመታት ለሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ ገልፀው ከሥራቸው ተፈናቅለው ለጎዳና ሊዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

ከፌደራል መንገዶች ባለሥልጣንና የተጠቀሰው አቤቱታ እንደቀረበለትና አጥኒ ቡድን ልኮ ጉዳቱ ትክክለኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ገልፆ በቀጣይ ካሳ እንደሚከፈል አስታውቋል።

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው እንዲህ ዓይነት ምላሽ ከዚህ ቀደም ማግኘታቸውን ነገር ግን በወረዳውም ሆኑ በክልሉ በኩል ምንም የተደረገላቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። VOA Amharic

READ  የኦሮሚያ ከተሞች የሰሞኑ አመጽ እና አንዳንድ ያልተገቡ ክስተቶች
Continue Reading

Africa

ስለግድቡ በግብፅ መገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ ተፅእኖ አይፈጥሩም-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Published

on

ስለግድቡ በግብፅ መገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ ተፅእኖ አይፈጥሩም-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እና የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት በኩል እየወጡ ያሉ አፍራሽ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ አንዳች ተፅእኖ እንደማይፈጥር የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አትፈልግም ብለዋል።

ከ60 በመቶ በላይ የደረሰው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ብቻ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፥ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ከማፋጠን ጎን ለጎን ከግብፅ እና ሱዳን ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እና የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት እያራመዱት ያለው አቋም ግን ከመርሆች መግለጫ ስምምነት ጋር የሚጣረስ፤ አፍራሽ ድርጊት ነው ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኳታር ይፋዊ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸውን እና በቅርቡ ካይሮ ውስጥ ሶስቱ ሀገራት 17ኛውን ድርድር አድርገው ያለ ስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ።

በተለይ የግብፅ የተወሰኑ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴን ግድብ ግንባታ ለማፋጠን ከኳታር ገንዘብ አግኝታለች የሚል መረጃ አሰራጭተዋል።

ከዚህ ባለፈም እየተካሄደ ያለው ድርድር ፍሬ ቢስ እየሆነ መምጣቱን እና ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ መድረክ ለመውሰድ ያላቸውን ፍላጎት በግልፅ አንፀባርቀዋል።

የተወሰኑ የሀገሪቱ ፖለቲከኞችም ባገኙት መድረክ ሶስቱ ሀገራት ካርቱም ውስጥ ከተስማሙት የመርሆች መግለጫ ወይም ያፈነገጠ አስተያየት በተደጋጋሚ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ አቶ መለስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ለማጠናቀቅ ከኳታር ገንዘብ አግኝታለች በሚል የዘገቡ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ፍፁም ተቀባይነት የሌሌው ሀሰተኛ እና የሌላ አጀንዳ ማስቀየሻ አድርገው ያቀረቡት መሆኑን ተናግረዋል።

READ  ኢትዮጵያ፣ኬንያና ጂቡቲ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት ላይ ድጋፋቸውን ገለጹ ተባለ

“የግድቡ ግንባታ እየተከናወነ ያለው ሁላችንም እንደምናውቀው ያለ አንዳች ሀገር ድጋፍ፤ ያለ አለም አቀፍ ተቋም የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያዊያን ጉልበት፣ እውቀት እና ገንዘብ ነው” ብለዋል።

የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ 70 በመቶ የገፀ ምድር ውሃ፣ ሁለት ሶስተኛው የውሃ ሃይል የማመንጨት አቅም ከመያዙ ባሻግር፥ ከዘጠኝ ክልሎች ስድስቱን በሙሉ እና በከፊል የሚሸፍን ሲሆን፥ ይህም ከ36 በመቶ በላይ የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፤ 45 በመቶ የሚሆን ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ነው።

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ዓለም አቀፍ ህግን አክብራ የአባይን ወንዝ የህዝቧን የአሁን እና የወደፊት ትውልድ ፍላጎት ለማሳካት መጠቀሟን አጠናክራ እንደምትቀጥልም በመግለጫቸው ላይ አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት 17ኛው የካይሮው የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሀብት ሚኒስትሮች ድርድር ያለ ውጤት የተበተነው ግብፅ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን በተለይ የ1929/1959 ስምምነቶች የድርድሩ አካል ይሁኑ በማለቷም እንደሆነ ነው ያነሱት።በስላባት ማናዬ  ኤፍ ቢ ሲ

Continue Reading

Environment

60 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ የግል መፀዳጃ ቤት የለውም- ተመድ

Published

on

60 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ የግል መፀዳጃ ቤት የለውም- ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዓለም ህዝብ መካከል 60 በመቶ ያክሉ በቤታቸው መፀዳጃ ቤት እንደሌላቸው አስታወቀ።

የመንግስታቱ ደርጅት ትናንት የተከበረው የዓለም የመጸዳጃ ቤት ቀን ምክንያት በማድረግ፥ ከመጸዳጃ ቤት የሚለቀቅ ውኃ አያያዝን ላይ ትኩረት መስጠት አንዳለበት አሳስቧል።

ይህንን ሁኔታም “ዓለም አቀፍ የንፅህና ጉድለት” በማለት በተለያዩ መረጃዎች አስደግፎ አቅርቧል። መረጃው እንደሚያመላክተው በመላው ዓለም 892 ሚሊየን የሚሆነውን ህዝብ ሜዳ ላይ ይፀዳዳል።

በተጨማሪም በአለም ዙሪያ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ከመፀዳጃ ቤት የሚለቀቅ ውኃ ሳይታከም ተመልሶ ወደ ተፈጥሮ ሃብት ይፈሳል።

መረጃው እንደሚያሳየው በቂ መፀዳጃ ቤት እና በቂ የንጽህና መጠበቂያ ስፍራ አለመኖር ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ባሉት እንደ ቻይና እና ህንድ ባሉ አገሮች ውስጥም እንድ ትልቅ ችግርነት ይነሳል።

ለዚህም እንደማሳያ በምሥራቅ የቻይና ግዛት የሻንዱንግ ከተማ የሆቴል ፅዳት ሠራተኞች የመኝታ ፎጣዎች ተጠቅመው ሽንት ቤት ስያፀዳዱ መታየታቸው አስቀምጧል።

በተጨማሪም ህንድ ውስጥ የሚገኘው ቦሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪ፥ “መፀዳጃ ቤት” በተባለ የፍቅር ታሪክ ፊልሙ ባለፈው በአገሪቱ ያለውን ደካማ የማፀዳጃ ቤት አያያዝ ጉድለት በሚመለከት እንደማሳያ ማቅረቡን ተጠቁሟል።

ከዚህ በመነሳት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከመፀዳጃ ቤቶች የሚወጡ ቆሻሻዎች አወጋገድ ሰርዓትን በተመለከተ አራት ደረጃዎች አስቀምጣል።

ማጠራቀም፥ ከመፀዳጃ ቤቱ የሚወጣ ቆሻሻ ከሰዎች ንክኪ አርቆ በጽዳት እቃዎች እና በታንከር ውስጥ መቀመጥ አለበት ብሏል።

ማንሳት፥ ከመፀዳጃ ቤቱ የሚወጣ ቆሻሻ በቱቦ በማድረግ ወደ ማከሚያ ስፍራው ማጓጓዝ።

ማከም፥ ከመፀዳጃ ቤቱን የሚወጣ ቆሻሻ ወደ ውሃ ማከሚያ አከባቢ በመውሰድ የአከባቢውን ደህንነት በጠበቀ/በማይበክል ሁኔታ ማከም ያስፈልጋል።

READ  የቱርክ ተማሪዎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ኢትዮጵያ ገቡ

ማስወገድ ወይም እንደገና ጥቅም መጠቀም፥ በተገቢው መንገድ የታከመ ቆሻሻ ለኤሌትሪክ ኃይል ወይም ለምግብ ምርት እንደ ማዳበሪያ ሊያገለግል ይችላል ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ እንዳሰፈረው ብዙ አገሮች የአካባቢ ንፅህናን ለማሳደግ ሰፊ ሀብቶችን አፍስሰዋል። ለአብነት በቻይና “የመጸዳጃ አብዮት”፥ አካባቢን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ አነፍናፊዎችን (sensors) መጠቀም እንደ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ መሳርያ ተደርጎ ተወስዷል።

በተመሳሳይ በህንድ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2019 በእያንዳንዱ ቤት፥ ሽንት ቤት ለመገንባት የሚያስችል እቅድ መያዙን ተነግሯል።

 

 

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን.

Continue Reading

Business

ሃይኒከን ገብስ አምራች ገበሬዎችን ለመርዳት የነደፈው ፕሮጀክት ውጤት እያስገኘ ነው አለ

Published

on

ሃይኒከን ገብስ አምራች ገበሬዎችን ለመርዳት የነደፈው ፕሮጀክት ውጤት እያስገኘ ነው አለ

ሃይኒከን ኢትዮጵያ የአርሶ አደሩ የቢራ ገብስ ምርት በብዛትና በጥራት እንዲያድግ ባለፉት አራት ዓመታት ባደረገው ጥረት የአርሶአደሩ ምርት ከሶስት እስከ አራት እጥፍ እንዲያድግ ማስቻሉን አስታወቀ፡፡

ሃይኒከን ኢትዮጵያ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ የአገር ውስጥ የቢራ ገብስን መጠቀም ላይ ትኩረት ሰጥቶ ከኢዩኮርድ፣ ከእርሻ ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ እርሻ ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጥምረት መስራት የጀመረው እ.ኤ.አ በ2013 መሆኑን አስታውሷል፡፡

 

ፕሮጀክቱ ለአርሶአደሮች ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር የቢራ ገብስ በምርት ብዛትና ጥራት እንዲያድግ ለማድረግ ያስቻለ ሲሆን የአርሶአደሮችን ገበያ የማግኘት ችግርንም ለመቅረፍ ችሏል፡፡

ሃይኒከን የአርሶአደሩ ምርት እንዲጨምር ያስመጣቸው ሁለት ዓይነት ምርጥ ዘሮች ማለትም ትራቭለር ኤንድ ግሬስ (Traveler & Grace) በመባል የሚታወቁ ሲሆን የፕሮጀክቱ ቀትተና ተጠቃሚ የሆኑ 20 ሺህ 894 አርሶአደሮች በተጨማሪ 30 ሺህ አርሶአደሮች የምርጥ ዘር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን መግለጫው ያስረዳል፡፡

ሃይኒከን የጀመረው ፕሮጀክት ከውጭ የሚገባውን የገብስ ምርት በአገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪ የማዳንና የአርሶአደሩን ሕይወት የማሻሻል ዓላማ ያለው መሆኑን መግለጫው ጠቁሞ በእስካሁኑ ሒደትም የበርካታ አርሶአደሮች ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዲያድግና የቤተሰቦቻቸው የኑሮ ደረጃ ከፍ እንዲል ማስቻሉን ጠቅሷል፡፡

በተያያዘም ዜናም በደሌ ቢራ እና የሃይኒከን አፍሪካ ፋውንዴሽን በጋራ በመሆን በ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የበደሌ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ማስረከቡን፣ በሐረር ለሚገኘው ለፈንቀሌ ጤና ጣቢያ የህክምና መሳሪያዎችና የአምቡላንስ ደጋፍ ማድረጉን፣ በቂሊንጦ 12 ለሚደርሱ እድሮች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን፣ በዚያው በቂሊንጦ ለወረዳ አምስት ጤና ጣቢያ የእናቶችና ሕጻናት ህክምና ክፍል ለማቋቋም፣ የአንቡላንስ ዕርዳታ ለመስጠት ማቀዱን አብራርቷል፡፡

READ  ቤቶች ኮርፖሬሽን በመሀል ከተማ ሰፋፊ ይዞታዎቹ ላይ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ዝግጅት ጀመረ

በተጨማሪም በዋልያ ቢራ ስም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን 56 ሚሊየን ብር እና በሶፊ ማልት ስም ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ30 ሚሊየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሷል፡፡

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close