Connect with us

Weird

የ16 ዓመቱ ታዳጊ 111 የሲሚንቶ ብሎኬቶችን በጭንቅላቱ በመስበር በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል

Binyam G-Kirstos

Published

on

የ16 ዓመቱ ታዳጊ 111 የሲሚንቶ ብሎኬቶችን በጭንቅላቱ በመስበር በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል

የ16 ዓመቱ ታዳጊ 111 የሲሚንቶ ብሎኬቶችን በጭንቅላቱ በመስበር በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል

 የ16 ዓመቱ ቦስኒያዊ ታዳጊ የማርሻል አርቲስት 111 የሲሚንቶ ብሎኬቶችን በጭንቅላቱ በመስበር በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል፡፡

ታዳጊው የቴኳንዶ ማርሻል አርቲስት ክሪም አህመትሳፓሂክ ይባላል፡፡

ከሪም በቪሶኮ ከተማ 111 የሲሚንቶ ብሎኬቶችን የመስበር ከፍተኛ ፈተና የቀረበለት ሲሆን ያለድካም ሰባብሯቸዋል፡፡

ከሪም ይህን ያደረገው በጭንቅላቱ ብሎኬቱን ከሰበረ በኋላ በቅጽበት ወደፊት በአየር ላይ በመስፈንጠር መሆኑ ድርጊቱን አስገራሚ አድርጎታል፡፡

በ16 ረድፍ የተደረደሩትን 111 ብሎኬቶችን በ35 ሰከንድ ውስጥ ሲሰባብር በሰውነቱ ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው የተነገረው፡፡

በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ የሰፈረ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀትም ተበርክቶለታል፤ ቤተሰቦቹን፣ አሰልጣኙን እና ጓደኞቹንም አመስግኗል፡፡

የሲሚንቶ ጠንካራ ድርድር ብሎኬቶችን የመስበር ልምድ ያልነበረው ከሪም በጠንካራ ወኔ እና በልዩ ችሎታው አሳክቶታል፡፡ FBC

READ  ደቡብ ኮሪያ ለኮሪያ ዘማቾች የሚሆን አንድ ማእከል በአዲስ አበባ ልትገነባ ነው
Continue Reading

Weird

አሜሪካዊው አዛውንት በስህተት ልጃቸው ያልሆነን ሰው ቀብረዋል

Binyam G-Kirstos

Published

on

አሜሪካዊው አዛውንት በስህተት ልጃቸው ያልሆነን ሰው ቀብረዋል

የልጃቸውን እርም ያወጡት አሜሪካዊው አዛውንት ከልጃቸው ጋር በድጋሚ ተገናኝተዋል።

በወሩ መጀመሪያ አካባቢ እርሳቸው በሚኖሩበትና ፋውንቴን ቫሊ በተባለው አካባቢ አንድ ሰው ሞቶ ይገኛል።

የአካባቢው ፖሊሶችም ህይዎቱ ያለፈውን ሰው አሻራ ካነሱ በኋላ ለአዛውንቱ ልጅዎት አርፏል በማለት ያረዷቸዋል።

እርሳቸውም መርዶውን ተቀብለውና ለዘመድ አዝማድ አሳውቀው ለቀብር ስነ ስርዓቱ ይዘጋጃሉ።

ሞተ የተባለው ልጃቸው በወቅቱ በዚያ አካባቢ ይኖር የነበረና የአዕምሮ ህመም ያለበት ጎዳና ተዳዳሪ ነበር።

አዛውንቱም አስፈላጊውን የቀብር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመድ ተሰብሰቦ እንዲፈጸም ያደርጋሉ።

እህቱም እርሱ ሞቶበታል በተባለው ስፍራ በመሄድ ፎቶግራፉንና የአበባ ጉንጉን ታስቀምጣለች።

በመርዶው ሳምንት ለተፈጸመው የቀብር ስነ ስርዓት ቤተሰብ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ አድርጓል።

አስከሬኑም “ሞቷል” የተባለው ወላጅ እናት ካረፉበት መካነ መቃብር አካባቢ ባለ ስፍራ እንዲያርፍ ይደረጋል።

የቀብር ስነ ስርዓቱ ከተፈጸመ ከ11 ቀናት በኋላ ግን ለ82 አመቱ አዛውንት በስልካቸው ልጃቸው እንዳለ ይነገራቸዋል።

ሁኔታውን ያላመኑትና የተደናገጡት አዛውንትም እውነት ከሆነ ደዋዩ ልጃቸውን ያገናኛቸው ዘንድ ይጠይቃሉ።

ከወዲያኛው ማዶ ያለው ድምጽም “ሃሎ አባዬ” በማለት ይመልስላቸዋል።

ከዚህ በኋላም ልጃቸውን አግኝተውት መኖሩን አረጋግጠዋል፤ በሁኔታውም ዘመድ አዝማድ ተረብሿል።

ሞቷል የተባለው ልጃቸው ግን ቤተሰቦቹን ካገኘ በኋላ ወደ ነበረበት የጎዳና ህይዎት መመለስን መርጧል።

ቤተሰቡ ግን ከዚያ ድንጋጤና ሃዘኑ ከፈጠረው ድባብ እስካሁን አልወጣም ነው የተባለው።

የቤተሰቡ ጠበቃም ይህን መሰል ትልቅ ስህተት የፈጸሙት ፖሊሶች ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን ገልጿል።

የአካባቢው ፖሊስ በበኩሉ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታን ጠይቋል፥ ችግሩ በአሻራ መመሳሰል የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሷል – FBC From associated press

READ  Bemnet Sues Canadian Company for Compensation over Forced Labour

Continue Reading

Weird

በየእለቱ ወደ ትምህርት ቤት በበሬ፣ በአህያ እና በፈረስ የሚጓዘው ህጻን…

Binyam G-Kirstos

Published

on

በየእለቱ ወደ ትምህርት ቤት በበሬ፣ በአህያ እና በፈረስ የሚጓዘው ህጻን…

በትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ቅንጡ ህይወታቸውን ለመግለፅ እና የብዙዎችን ቀልብ ለመሳብ በስፖርት መኪና ወይም በሊሞዚን ከቦታ ቦታ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ቻይናዊው የሶስት ዓመት ህጻን ወደ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ሁልጊዜ የሚሄደው በበሬ፣ በፈረስ ወይም በአህያ ጀርባ ላይ ሆኖ ነው፡፡

አባቱም በእግራቸው እየሄዱ ልጃቸው የሚጓዝበትን እንስሳ እየጎተቱና እየመሩ የሚያደርሱት ሲሆን፥ ይህ ዘወትራዊ የመጓጓዣ መንገድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እያነጋገረ ነው፡፡

በደቡባዊ ቻይና የሲቹዋን ግዛት ዋና ከተማ ቼንግዱ የሚኖሩት አባት እና ልጅ ከቤታቸው 3 ኪሎሜትር ወደሚርቀው ትምህርት ቤት የሚጓዙት በእንዲህ መልኩ ነው፡፡

በሬ፣ አህያ እና ትንሽ ፈረስ በየእለቱ እየተቀያየሩ ህጻኑን ወደ ትምህርት ቤት ይወስዳሉ፡፡

ሶስቱም እንስሳት የቻይና ስልጣኔ አድናቂ እና አስቀጣይ በሆኑት የህጻኑ አባት ሊ ሊ፥ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡

ሊ ሊ ጥንታዊው “የሀገራችን ስልጣኔ እና ባህል የዕለት ተዕለት ህይወታችን አንድ አካል መሆን አለበት” የሚል አቋም አላቸው፡፡

“ልጄ በበሬው ወይም በአህያዋ ወደ ትምህርት ቤት ሲጓጓዝ ለህጻናት ያለው ፍቅር ይጨምርለታል” ነው ያሉት ሊ፡፡

ህፃኑ በፈረስ፣ በሬ ወይም አህያ ጀርባ ላይ ሆኖ በየዕለቱ መጓዙ አባት ለልጃቸው ስለቻይና ስልጣኔ፣ ስለ ወቅታዊ ነገሮች እና የዛፍ ተከላ እንዲያስተምሩት እድልን ፈጥሯል፡፡

ሆኖም እናት የልጃቸውን በእንስሳቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤት መጓዝን ወድቆ ይጎዳብኛል በሚል አልወደዱትም፡፡

ሊ ሊ ደግሞ ሁኔታውን በሌላ መንገድ ነው የሚገልጹት፤ “በሬ እና አህያ የተረጋጉ የመጓጓዣ እንስሳት በመሆናቸው በልጄ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስም” በማለት፡፡

ህጻናት በአሁኑ ጊዜ ጥንታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን እየረሱ የማንነት ቀውስ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ዘመናዊውንም ሆነ ባህላዊውን ህይወት እያሳወቁ ማሳደግ ይገባል ነው የሚሉት ሊ፡፡

READ  Bemnet Sues Canadian Company for Compensation over Forced Labour

ቻይና በመንግስት ደረጃ ፈረስን፣ አህያን፣ በሬን ወይም ሌሎች እንስሳትን በመጓጓዣነት መጠቀምን ትፈቅዳለች።

ሆኖም በእንስሳት የሚጓጓዙ ሰዎች ተሸከርካሪ በማይሄድባቸው መንገዶች ሊጠቀሙ እንደሚገባ ትመክራለች፡፡

አንዳንድ ጊዜ በእንስሳት የሚጓዙ ሰዎች በተሸከርካሪ መንገድ ላይ በመግባት የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ እና የትራፊክ ፖሊሶችም በሌላ መንገድ እንዲጠቀሙ እንደሚያደርጓቸው ይነገራል፡፡

በቻይና ማህበራዊ የትስስር ገጽ በሆነው ወይቦ፥ “የህጻኑን በበሬ ጀርባ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እና በቻይና ስልጣኔ መካከል ግንኙነት አለን?” የሚል ጥያቄ ያነሱ አሉ።

ሌሎቹ ደግሞ የህጻኑ አባት ልጁን ስለ ጥንታዊ የቻይና ስልጣኔ ለማስተማር የተጠቀሙበትን መንገድ አድንቀዋል – FBC

Continue Reading

Weird

የመስሪያ ቤቱን የአለባበስ ስርዓት ለመቃወም ቀሚስ ለብሶ ስራ የገባው እንግሊዛዊ በመጨረሻም ተሳክቶለታል

FanaBC

Published

on

By

የመስሪያ ቤቱን የአለባበስ ስርዓት ለመቃወም ቀሚስ ለብሶ ስራ የገባው እንግሊዛዊ በመጨረሻም ተሳክቶለታል

እንግሊዛዊው ግለሰብ ቁምጣ ለብሶ ወደ መስሪያ ቤት ሲሄድ አትገባም ተብሎ ወደ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ልክ እንደ ሴቶቸቹ ቀሚስ ለብሷል።

ጆይ ባርግ የተባለው ይህ ግለሰብ የስልክ ጥሪ ማእከል ውስጥ የሚሰራ ሲሆን፥ ቁምጣ ለብሶ ሊገባ ሲል ነበር ከስራ ወደ ቤቱ እንዲመለስ የተደረገው።

ጆይ “ሴቶች በስራ ቦታ አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ከሆነ እኔስ አጭር ቁምጣ ብለብስ ምን ችግር አለው” ሲልም በትዊተር ገጹ ላይ ለጥፏል።

ከደቂቃዎች በኋላም ጆይ የድርጅቱን የአለባበስ ህግ ጥሰሃል በሚል ወደ ስራ እንዳይገባ መከልከሉን እና ወደ ቤቱ መመለሱን በትዊተር ገጹ ያስታውቃል።

ከቆይታ በኋላም ጆይ ሀምራዊ እና ብርቱካናማ ቀለማት ሰረዝ ያለበት ጥቁር ቀሚስ ለብሶ ወደ ስራ ቦታው ለመመለስ የወሰነ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ወደ ቤት እንደሚመልሱት ገምቶ ነበር።

ጆይ ወደ ቢሮ በሚገባበት ጊዜ ግን ያልጠበቀው ነበር ያጋጠመው ሲሆን፥ ቀሚስ ለብሶ በመሄዱ ይመልሱኛል ያለው ጆይ በተቃራኒው ሞቅ ያለ አቀባበል ነው የተደረገለት።

ይህ ብቻ አይደለም ሁሉም የመስሪያ ቤቱ ወንድ ሰራተኞች ባሰኛቸው ጊዜ ቁምጣ ለብሰው ወደ ስራ እንዲገቡ ኩባንያው ጆይ ባደረገው ጥረት ፈቅዷል።

“አሁን ላይ በከፊል አሸንፈናል” ሲልም ጆይ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ጆይ ይናገራል፥ “ለተቃውሞ ለብሼ የሄድኩትን ቀሚስ ቤት ገብቼ እንድቀይር ፈቃድ ተሰጥቶኝ ነበረ፤ እኔ ግን ቀኑን ሙሉ ለብሼው መዋልን መርጫለው” ብሏል –FBC

READ  ደቡብ ኮሪያ ለኮሪያ ዘማቾች የሚሆን አንድ ማእከል በአዲስ አበባ ልትገነባ ነው
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close