Connect with us

History

የዐፄ ምኒልክ ቀኝ እጆች-አራቱ የኢትዮጵያ ዋርካዎች፤

Published

on

የዐፄ ምኒልክ ቀኝ እጆች-አራቱ የኢትዮጵያ ዋርካዎች፤

የዐፄ ምኒልክ ቀኝ እጆች-አራቱ የኢትዮጵያ ዋርካዎች፤
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የአድዋን በዓልን ምክንያት በማድረግ የታሪክ ማስታወሻዎችን፣ ታሪካዊ መስህቦችንና ኢትዮጵያዊ ቀድምት ጀግኖቻችን እያስተዋወቀን ነው፡፡ ዛሬ ለኢትዮጵያ አንድነት ታላቅ መስዕዋእትነትን የከፈሉ አራት ታላላቅ ሰዎችን ዋርካዎች ሲል እንዲህ ያስተዋውቀናል፡፡) (ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ)

እኔ ስለ አንድ ዘመን ዋርካዎች ላወራ ነው፡፡ ሀገር ስለ አስጠለሉ ዋርካዎች፡፡ ደግሞ የየሰፈርህን ዋርካ ሳትጠራልኝ ብሎ ሆ የሚለውን ስሙልኝ፡፡ ቀጥለናል፡፡ አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ከሆነ መሪው ንጉሠ ነገሥት የጥቁር ህዝቦች የነጻነት መሪ፣ የቅኝ አልገዛም ባይነት ሙሴ ናቸው ማለት ነው፡፡

አድዋ ድል የእኛም ድል ነው ካልን የጋራ ሀገር አለችን ማለት ነው፡፡ ለዚህች የጋራ ሀገራችን ዋርካ የሆኑ የአንድ ዘመን ጌጦችን አድዋን አስታከን ልናወድስ ነው፡፡ ወልደጊዮርጊስ አቦዬ ቀዳሚው ዋርካ ናቸው፡፡ አባ ሰጉድ ወልደጊዮርጊስ ወይዘሮ አያህሉሽም ከሚባሉት እና የንጉሥ ሣህለ ስላሴ የልጅ ልጅ ከሆኑት እናት እና ከስመ ጥሩው አቦዬ የሚወለዱ ናቸው፡፡

በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምኒልክ ዘንድ ልዩ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ንጉሠ ነገሥቱ ሲያልሙ ካፋ ሊሙ ኦሞና ቱርካና ድረስ የዘመቱ፣ ጦር የመሩ እና እስከ ነጭ አባይ ድረስ ገስግሰው ኢትዮጵያን በአንድ ጎን ያስከበሩ የዚያን ዘመን ዋርካ ናቸው፡፡ የጎንደር ንጉሥ ተደርገው ተሾመው የንግሥና ህይወትን በቅጡ ሳያጣጥሟት የካቲት 24 ቀን 1910 ዓ.ም. ዋርካ ከሆኑላት ሀገር በሞት ተነጠሉ፡፡ ሌላው ዋርካ ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ናቸው፡፡ አባ ቃኘው፡፡

ከዶባው ባላባት ከታወቁት ወልደሚካኤል ጉዲሳ ከወይዘሮ ተናኘ ወርቅ ሳህለ ስላሴ የተወለዱት ልዑል የወንድምን ያክል በዐፄ ምኒልክ ቤተ መንግስት ቅቡል የሆኑ መስፍን ነበሩ፡፡

ባላምባራስ ሆነው የገቡበት የዐፄ ምኒልክ ሹመት ራስ አድርሶ ልዑል ሲያስብላቸው ምስራቅ ኢትዮጵያን ዋርካ ሆነው ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ውለታ የዋሉ፤ በአድዋ ጦርነት ለኢትዮጵያ ነጻነት የዘመቱ፤ ሞታቸው የንጉሠ ነገሥቱ ቀኝ እጅ ተቆረጠ ያስባለ ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡ ሶስተኛው ዋርካ አባ ጥጉ ናቸው፡፡

ራስ ጎበና ዳጬ፤ ምናልባትም እኒህ ዋርካ ባይፈጠሩ ኖሮ ዐፄ ምኒልክ አንድ ማድረግ የተመኟት ሀገር በምኞት ብቻ በቀረች፡፡ ራስ ጎበና ግን ጀግነታቸውን መሬት ለመናጠቅ እና ራስን ለማንገስ ሳይሆን ውላ አድራ የአድዋ ድል ባለቤት ለመሆን ለበቃችው ሀገር አንድነት ገበሩት፡፡ ኢትዮጵያዊው ጄነራል ታላቅ የጦር መሪ እና ጥቁሩ ናፖሊዮን ተብለው የተሞካሹ ጀግና ናቸው፡፡

ሥነ-ቃል ተግባራቸውን ማሸነፍ ያልቻለ፤ ገጣሚና አዝማሪ ለጀግንነታቸው መወድስ ቃል እስኪያጥረው ያስጨነቁ ጀግና፤ አራተኛው ዋርካ አባ መላው ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ናቸው፡፡

የንጉሠ ነገሥቱን ያክል ተክበረው የኖሩ፤ በምክራቸው ሀገር ያጸኑ፣ በስል ሀሳቦቻቸው ሚኒልክ የተመኟትን ኢትዮጵያ እውን ያደረጉ፤ በታማኝ ጦራቸው በአድዋ የድል ታሪክ ያስመዘገቡ፡፡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንዲሁ በየዘመናቱ ድንቅ ሰዎች ነበሯት፡፡ በአድዋ ድል በብርቱ ክንዳቸው የጥቁሮችን የነጻነት ውልደት እውን ያደረጉ እነ ባልቻ አባ ነፍሶን እነ ራስ አሉላ አባነጋን እያነሳን እናወድሳለን፡፡ DIRETUBE

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close