Connect with us

Ethiopia

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተከሳሾች መልስ ሰጡ

VOA Amharic

Published

on

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተከሳሾች መልስ ሰጡ

የኢትዮጵያ መንግሥት በመድረክና ኦፌኮ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ሲራጅ ላይ ከትናንት በስቲያ ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

የክሱ ጭብጥ አስመልክቶ የግንቦት ሰባት መሪዎች፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ጠበቃ በክሱ ላይ አስተያየታቸውን ሰጠዋል፡፡
ግንቦት ሰባት ክሱን
“ቧልት” ሲለው፤
“ሕግና ሕገ¬-መንግሥት የሌለበት ሃገር፡፡” በማለት አስተዳድሩ በህወሃት የሕግና የሕገመንግሥት የበላይነት የሚንቀሳቀስ ሲል ክሱን አጣጥሏል።
ከትናንት በስቲያ ሦስቱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የመገናኛ ብዙኃን መሪ የተመሰረተባቸው ክሶች የወንጀል ክሶች ናቸው። የመገናኛ ብዙሃኑ ኢሳትና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የፀረ-ሽብር ሕጉ ተጠቅሶ ነው ክስ የተመሰረተባቸው ሲል ትላንት ማምሻውን የአሜሪካ ድምጽ ሲዘግብ ዶቼቬሌ በበኩሉ ከትናንትና በስቲያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን ጨምሮ ሁለት ግለሰቦችና ሁለት ተቋሞች ላይ የወንጀል ክስ መሥርቷል።

ዶክተር መረራ ከኅዳር 21 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ እስር ላይ ይገኛሉ። ሌሎቹ ማለትም ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመነበር እና የፖለቲካ እና የመብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ጀዋር መሃመድ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሳትላይት ቴሌቪዥንና የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ በሌሉበት አቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባቸዋል።

ሦስቱም ተጠርጣሪዎች «ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል እንናስወግዳለን» በማለት እንደተንቀሳቀሱ የወንጀል ዝርዝሩ ያመለክታል። ሁለቱ ተቋሞች ደግሞ ለሦስቱም ግለሰቦች «ልሳን» በመሆን በአገሪቱ ዉስጥ የነበረዉን ተቃዉሞ አባብሰዋል፣ ለንብረት መዉድምና ለሰዉ ሕይወት መጥፋትም ምክንያት ሆኖዋል በሚል ተከሰዋል።

ዶክተር መረራ በማዕከላዊ እስር ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩት ጠበቃቸዉ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ደንበኛቸዉ በወንጀል መቅጫ መከሰሳቸዉ ይናገራሉ።

መንግሥት «የሽብርተኛ» የሚለዉ ቡድን አመራር መሆንን ጨምሮ በተመሳሳይ ክስ የተመሠረተባቸዉ ሁለተኛዉ ተከሳሽ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፤ እንዲህ ዓይነት ክስ ለእኔ መጀመርያ አይደለም ይላሉ። እሳቸዉ በሚመሩት ድርጅት ላይ የቀረበዉን ዉንጀላም መሰረተ ቢስ ክስ መሆኑን ይናገራሉ።

«ስርዓቱ የኔን ስም ተጠቅሞ ዶክተር መረራን ለመጉዳት ያሰበበት ክስ ነዉ» የሚሉት ደግሞ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ጀዋር መሃመድ ናቸዉ።
አቶ ጀዋር በአምስተኛ ደረጃ ላይ ክስ የተመሰረተበት የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ (OMN) ሥራ አስኪያጅም ናቸዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ግዜያት «ሲወነጅለን ነበር» የሚሉት አቶ ጃዋር የሚመሩትን ተቋም ከክሱ ነፃ መሆኑን ይናገራሉ።

ዶክተር መረራ እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸዉ ለ85 ቀናት በእስር እንደቆዩ ጠበቃቸዉ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ገልጸዋል። ከትላንት በስቲያ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ስምንት ሰዓት ላይ ቀጠሮ ነበራቸዉ። ይሁን እንጂ የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት «ጠዋት ሁለት ሰዓት ላይ ሦስት ዳኞች ባሉበት እሳቸዉ ብቻ ቀርበዉ ክሱ እንዲነበብላቸዉ ሲጠየቁ ጠበቆቼ ሳይቀርቡ አይቻልም በማለታቸዉ ለትላንት ሳምንት ቀጠሮ» እንደተሰጣቸዉ አቶ ወንድሙ አመልክተዋል ዶቼቬሌ ዘግባል።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close