Connect with us

Health

የስፐርም ህዋስን በመጉዳት ለማህንነት የሚዳርጉ ስድስት ነገሮች

Binyam G-Kirstos

Published

on

የስፐርም ህዋሳትን በመጉዳት ለማህንነት የሚዳርጉ ስድስት ነገሮች

የስፐርም ህዋሳትን በመጉዳት ለማህንነት የሚዳርጉ ስድስት ነገሮች –  በርካታ ወንዶች ስለሚያመነጩት የስፐርም ህዋስ ብዛት እንጂ ስላለው አቅም ወይም ጥራት ብዙም ሲጨነቁ አይስተዋልም፡፡  የወንድ ማህንነት በስፐርም አመራረት እና አካሄድ ችግሮች እንዲሁም በከፍተኛ አልኮል ተጠቃሚነት እና ሲጋራ አጫሽነት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ነው፡፡

ከፍኛ አልኮል መጠቀም እና ሲጋራ ማጨስ የሚመረተውን የስፐርም ህዋስ መጠን እንዲቀንስ እና ጽንስ የመፍጠር አቅሙን እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ሌሎች አካባያዊ እና ባህሪያዊ የሆኑ ነገሮችም ለወንድ ልጅ ማህንነት ሊያጋልጡ እንደሚችሉ የህክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

ከዚህ በታች የቀረቡት ስደስት አካባያዊ እና ባህሪያዊ ክስተቶች በርካታ ወንዶች የማያስተውሏቸው ቢሆንም የስፐርም ህዋስን የሚጎዱ እና ለማህንነት ሊዳርጉ የሚችሉ ናቸው፡፡

  1. ፕሮሰስ የተደረገ ስጋን መመገብ

ይህ ስጋ ምንም እንኳ ጣፋጭ ቢሆንም ጥናቶች ይህን ምግብ መመገብ የስፐርም ህዋስን እንደሚጎዳ ያስረዳሉ፡፡

በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በ150 ወንዶች ላይ የተካሄደ ጥናት ፕሮሰስ የተደረገ ስጋ ፣ ቀይ ስጋ ፣ ነጭ ስጋ ፣ የዶሮ ስጋ እንዲሁም አሳ የመመገብ ልምድ ባላቸው ወንዶች እና የፍቅር/የትዳር አጋሮቻቸው ላይ ናሙና ወስዷል፡፡

በዚህም በቀን ከግማሽ እና ከዚያ በላይ ፕሮሰስ የተደረጉ /  የሱፐርማርኬት እድሚያቸውን ለመጨመር ሳይበላሹ እንዲቆዩ በእንፋሎት የተጠበሱ በከፍተኛ የጨው መጠን የታሹ/ ምግቦችን የሚመገቡት ወንዶች ያስመዘገቡት 5.5 በመቶ የሆነ መደበኛ የስፐርም ህዋስ ቅርጽ ሲሆን ከተጠቀሰው በታች ፕሮሰስ የተደረጉ ስጋ ነክ ምግቦችን የሚመገቡት ወንዶች ማስመዝገብ የቻሉት የስፐርም ህዋስ ግን 7.7 በመቶ ነው፡፡

በሌላ በኩል በምግባቸው ላይ አሳን የሚያዝወትሩት መደበኛ የሆነውን የስፐርም ሴል ቅርጽ ብዛት ማሻሻል እንደቻሉም በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡

የጥናት ቡድኑ መሪ ዶ/ር አፊቼ ፕሮሰስ ከተደረጉ ስጋዎች ይልቅ አሳን መመገብ ለስፐርም ሴል ጤናማነት ጠቃሚ ነው ሲሉ መክረዋል፡፡

  1. ሳውና ባዝ አጠቃቀም

በሰውነት ውስጥ ያለውን አላስፈላጊ ፈሳሽ በላብ መልኩ ማስወጣት ለጤናማ ህይወት የሚመከር ቢሆንም ይህንን በሳውና ባዝ ውስጥ ማድረግ ግን የስፐርም ሴልን ለጉዳት ይዳርጋል፡፡

በጣሊያን ፓዶቫ ዩኒቨርሲቲ በ 10 ጤናማ የፊንላንድ ዜጎች ላይ ይህን ለማረጋገጥ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡

ጥናቱ እነዚህን አስር የሰላሳ ዓመት ወጣቶች በሳምንት ሁለት ግዜ ለአስራ አምስት ደቂቃ ሳውና እንዲጠቀሙ በማድረግ ለሶስት ወራት የተካሄደ ነው፡፡

ጥናቱ የተካሄደባቸው ሰዎች ጤናማ ስፐርም ህዋስ ያላቸው እና ላለፉት አመታትም ሳውናን ያልተጠቀሙ ነበሩ፡፡

በዚህም ጤናማ የስፐርም ህዋስ የነበራቸው የጥናቱ ተካፋዮች ሳውናን እየተጠቀሙ ቆይተው ከሶስት ወር በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ የስፐርም አመራረታቸው በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ በጥናቱ ታይቷል፡፡ የስፐርም ህዋስ ምርትም ወደ መደበኛ ደረጃው ለመመለስ ስድስ ወራትን ፈጅቶባቿል፡፡

በመሆኑም  ሳውናን መጠቀም የወንዶች የመውለድ እድልን ስለሚቀንስ ጠንቀቅ ማለቱ ይበጃል ባይ ናቸው ጥናት አድራጊዎቹ፡፡

  1. በህይወት ውስጥ ጭንቀትን ማብዛት

ጭንቀት በአጠቃላይ ጤና ላይ ጫና የሚያመጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የወንድ ልጅ ማህንነትንም እንደሚያመጣ ባለሞያዎች አረጋግተጠዋል፡፡

ከ38 አስከ 49 ዓመት ያላቸው 193 ወንዶች ላይ የተደረገ ጥናት በህይወታቸው ጭንቀታም የሆኑት የስፐርም ህዋስ ምርት ሂደታቸው አዝጋሚ እንደሆነ ለመለየት የተቻለ ሲሆን በስራ ቦታ ላይ የሚኖር የስራ ጫና እና ጭንቀት ግን የህዋሱን ጥራት አይዳም ተብሏል፡፡

ይሁንና በስራ ላይ የሚኖር ጭንቀት ዝቅተኛ የቴስቶስትሮን መጠን እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል፡፡

  1. ላፕቶፕ መጠቀም / ዋይፋይ

29 በሚደርሱ እና በየቀኑ ኢንተርኔትን ለአራት ሰዓታት በሚጠቀሙ ወንዶች ላይ በተደረገ ጥናት ዋይፋይ ኢንተርኔትን የሚጠቀሙት ከማይተቀሙት የስፐርም ሴላቸው የተጎዳ እንደሆነ ደርሰውበታል፡፡

የላፕቶፕ ሙቀት ብቻ ሳሆን የምንጠቀመው ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎትም ለስፐርም ህወስ መመረት ችግር እና ለዲኤንኤ መጎዳት ሊዳርግ ይችላል፡፡

5.    ለነፍሳት ማጥፊያ ለሚያገለግለው ኬሚካል መጋለጥ

ለነፍሳት መግደያ የምንጠቀምበት በተለምዶ ፍሊት የምንለው እና ሌሎች ተመሳሳ ኬሚካሎች በርካታ የጤና እክሎች የሚያደርሱ ቢሆንም በዋሽግተን ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት ለዚህ መሰሉ ኬሚካል መጋለጥ የስፐርም ህዋስን እንደሚጎዳ እና ለማህንነት ሊያጋልጥ እንደሚችል አረጋግጧል፡፡

6.    ማሪዋና የተሰኘውን አደንዛዥ እጽ  መጠቀም

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ማሪዋና የሚጠቀሙ ወንዶች በግንኙነት ወቅት ስፐርም ሴላቸው የሴቷ እንቁላል ጋር ከመድረሳቸው በፊት መኮላሸታቸውን ያሳያሉ፡፡

ምንጭ –ሜዲካል ዴይሊ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close