Connect with us

Health

ጸጉራችንን ሊጎዱ የሚችሉ አምስት አላስፈላጊ ልምዶች እና ሁኔታዎች

Binyam G-Kirstos

Published

on

ጸጉራችንን ሊጎዱ የሚችሉ አምስት አላስፈላጊ ልምዶች እና ሁኔታዎች

ጸጉራችንን ሊጎዱ የሚችሉ አምስት አላስፈላጊ ልምዶች እና ሁኔታዎች – የሴቶችን እና ጸጉራቸውን የሚያስረዝሙ ወንዶች ጸጉርን ሊጎዱ የሚችሉ ልምዶችን እና ሁኔታዎችን የኢትዮጲካ ሊንክ መረጃ አምስት የሰኘው የሬድዮ ፕሮግራም አቅርቧል፡፡ ይህ መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

  1. ጸጉርን ሳይሸፍኑ መተኛት

የምንጠቀማቸው ትራሶች በተለይም ከጥጥ የተሰሩ ትራሶች ወይም አንላዎች ጸጉርን የመጎተት እና የመንቀል ፣ ጸጉድን የማየያዝ እንዲሁም ማድረቅን ስለሚያመጡ በእንቅልፍ ወቅት ጸጉርን ሸፍኖ መተኛት ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሃር የሆኑ ጨርቆጭ ላይ መተኛት ጸጉራችን እና ቆዳችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ያደርጋሉ

2. ለጸጉራችን የምንጠቀመውን ቅባቶች አለመለየት

ለጸጉራችን  ቅባቶች ፣ የንጽህና መጠበቂያዎች እና ማስዋቢያዎች በምንጠቀምበት ግዜ የመጠቀሚያ ጽሁፋቸውን ማንበብ እና ከጸጉራችን ጋር ያላቸውን ተስማሚነት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ቤት ውስጥ ግዜ የሚያሳልፉ ከሆነ ቤት ውስጥ በሁለት ሳምንት አንዴ ሶስት እንቁላል እንድ አቦካዶ እና አንድ ማንኪያ ማር በንጹህ ጸጉር ላይ በመቀባት ለሰላሳ ደቂቃ ቆይቶ መታጠብ ለጸጉር ጠቀሜታ አለው፡፡

3. ጸጉርን ወደ ላይ ቆንጥጦ ማስያዝ

ይህን ማድረግ ጸጉር እንዲጨናነቅ እና እንዲሰባበር ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ጸጉርን ለላ አድርጎ ማስያዝ ያስፈልጋል፡፡

4. በሙቅ ውሀ መታጠብ ፣ በየቀኑ መታጠብ ፣ እርጥብ ጸጉርን ማበጠር

ጸጉርን በየቀኑ መታጠብ በጸጉራችን ያሉትን ንጥረ ነገሮች እንዲወደጉ ስለሚያደርግ በ የ አምስት ቀን አንዴ መታጠብ ይመከራል፡፡

ከታጠቡ ቧላም ጸጉርን ለማድረቅ በፎጣ ማሸት እና ሳይደርቅ ማበጠር ጸጉርን ይጎዳል፡፡በሙቅ ውሃም መታጠብ ጸጉራችንን ለጉዳት ይዳርገዋል፡፡

5. ጸሃይ

በብዛት ለጸሃይ መጋለጥ ጸጉርን አመዳማ እና ደረቅ እንዲሆን ስለሚያደርግ ከዚህ ራስን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close