Ethiopia
ኢትዮጵያ በሎንሊ ፕላኔት ቀዳሚ አስር የቱሪስት መዳረሻዎች ዝርዝር ላይ መስፈሯ ተዘገበ

ኢትዮጵያ በሎንሊ ፕላኔት ቀዳሚ አስር የቱሪስት መዳረሻዎች ዝርዝር ላይ መስፈሯ ተዘገበ
የአለም የቱሪስት መዳረሻዎችን ደረጃ በየጊዜው ይፋ የሚያደርገው የጉዞ ጥቆማ ሰጪ ሎንሊ ፕላኔት ኢትዮጵያን ከ 2017 ቀዳሚ አስር የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል እንዳሰፈራት ተዘገበ፡፡ ሀገሪቱ በዚህ መዝገብ ላይ ስሟ ከቀዳሚዎቹ አስር ሀገራት ተርታ በመስፈር ከአፍሪካ ብቸኛዋ ናት ተብሏል፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ መስፈር ከቻሉ ሀገራት መካከል ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ፊንላንድ፣ ዶሚኒካን፣ ኔፓል፣ ቤርሙዳ፣ ሞንጎሊያ፣ ኦማንና ማይናማር እንደሚገኙበት የእንግሊዘኛው እለታዊ ጋዜጣ ኢትዮጵያን ሄራልድ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ የቅርስ ሀብቶች የዳበረች ሀገር ስትሆን የበዙ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ የቅርስ ሀብቶች እንዳላት ዘገባው ይገልጻል፡፡ ቱሪዝም የሀገሪቱን 5 በመቶ ኢኮኖሚ እንደሚሸፍንና በየአመቱ የ 10 በመቶ እድገት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ዘገባው ይገልጻል፡፡
በአፍሪካ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስ መዝገብ በማስመዝገብ ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት የፖለቲካ አለመረጋጋት ማስተናገዷን ተከትሎ የቱሪዝም ዘርፉ መጎዳቱ ሲነገር ቆይቷል፡፡
Read more: Ethiopia in Top Ten Lonely Planet 2017 List
The largest travel guide-book publisher, Lonely Planet, cataloged Ethiopia among the top ten 2017 world tourist destinations.
The travel publisher indicated that visitors would be overwhelmed by the beauty of country’s scenery. It also highlighted the rewarding attractions: “Whether they [tourists] are trekking in the Semien Mountains to watch wildlife that roams nowhere else on Earth, climbing to a church carved into a remote cliff face in Tigray or boating across the serene waters of Lake Tana to visit an age-old monastery.
The launch of new airline links in 2017 would make the country more accessible than ever and urges tourists to be one of the first to hop on board, it said.
Ethiopia being the only African nation to make it to the esteemed list, Canada, Colombia, Finland, Dominica, Nepal, Bermuda, Mongolia, Oman and Myanmar were also able to make the cut.
According to Ministry of Culture and Tourism, Ethiopia envisions becoming one of the best tourism destinations in the continent.
Tourism reportedly makes up five percent of country’s GDP, registers an average of ten percent growth every year and creats more than a million jobs.
-
Ethiopia4 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture4 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Entertainment23 hours ago
ሕጻኑ ሳይንቲስት የኢትዮጵያን ድብቅ ኮድ ተናገረ! ክፍል 2
-
Entertainment23 hours ago
‹‹ጠቅላያችን አንበሳ ጋር ፎቶ የሚነሱት መቼ ይሆን?››
-
Ethiopia16 hours ago
ታራሚው ተሞሸረ
-
Ethiopia4 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia1 day ago
ኢሳት አዲስ አባ: ግንቦት ሰባት ማርቆስ: በረከት እስር ቤት የገቡበት የካቲት 11
-
Ethiopia5 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን