Connect with us

Ethiopia

የእጅ ጣቶቻችን ለተለያዩ በሽታዎች እና አላስፈላጊ ለሆኑ ስሜታዊ ባህሪያት መፍትሄ ይሆናሉ ተባለ

Binyam G-Kirstos

Published

on

የእጅ ጣቶቻችን ለተለያዩ በሽታዎች መፍትሄ ይሆናሉ ተባለ

የእጅ ጣቶቻችን ለተለያዩ በሽታዎች  መፍትሄ ይሆናሉ ተባለ – በኢትዮፒካ ሊንክ የሬድዮ ፕሮግራም ከወደ ጃፓን የተገኘ መረጀ ነው ተብሎ የቀረበው ጠቃሚ ምክር የእጅ ጣቶቻችንን ከተለያዩ ባህሪዎቻችን እና አካላዊ ህመሞች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ወይም የእጅ ጣቶቻችን ያሉብንም ህምሞች ለማቅለል እና የሚታዩብንን አላስፈላጊ ስሜታዊ በሀሪያት ለማረጋጋት እንደሚጠቅሙ ተጠቁሟል፡፡

ይህ የእጅ ጣቶችን በመጠቀም  ከበሽታ እና ከአጉል ስሜታዊ ባህሪ ራስን የማውጣት ዘዴ የጃፓናዊያን ባህል ከመሆን ባለፈ በሳይንሳዊ ምርምርም መረጋገጡ በመረጃው ተገልጿል፡፡

ይህ ዘዴ በሁሉም አይነት የካንሰር ታማሚዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል ይላል መረጃው፡፡

ይህን ለማድረግ በጥልቀት አየር እየሳብን  ጣቶቻችንን ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ ጫን በማድረግ እና  በመልቀቅ የሚሞከር ነው፡፡ እስቲ አምስቱ ጣቶች ያላቸውን የስሜት እና የአካላዊ ትስስር እና የሚያመጡትን መፍትሄ እንመልከት፡፡

  1. ትንሿ ጣት

ይህ ጣት ከትንሿ አንጀት እና ከልብ ጋር ይያያዛል የተባለ ሲሆን በራስ የመተማመን ስሜታችን ሲወርድ ፣ መረጋጋት ሲያቅተን  ስንቻኮል ከትንሿ ጣታችን ጋር ይያያዛል፡፡

በተጨማሪ ከደም ግፊት ፣  ከልብ ህመም ፣ ከጉሮሮ ህመም ፣ ከሆድ መነፋት  እንዲሁም ከአጥንት እና ከነርቭ ችግሮችም ጋር ይህ ጣታችን ትስስር አለው፡፡

በመሆኑም እነዚህን የስሜት እና አካላዊ ችግሮች ለማቃለል ወይም ከጅግሮቹ ለመዳን ይህን ትንሹን ጣት ጫን ጫን እያደረጉ በተመስጦ ከ ሶስት እስከ አምስት ደቂቃ አየር መሳብ እና ማስወጣት መፍትሄ ነው ተብሏል፡፡

  1. አመልካች ጣት

ህ ጣት ከኩላሊት እና ከፊኛ ጋር ትስስር አለው፡፡

ግራ መጋባት እና ተስፋ መቁረጥ ፣  ፍርሃት ከመሳሰሉ   ስሜታዊ ባህሪያት  እንዲሁም ከካላዊ ህመም የጡንቻና እና የጀርባ ህመም ፣ የጥርስ ህመም እና ሱስ ለሚያስቸግረው ብሎም ለምግብ መፈጨት በተመሳሳይ ከሶስት አስከ አምስት ደቆቃ አመልካች ጣትን ጫን ጫን በማድረግ እና አየር በመውሰድ ወደ ተሻለ ስሜት እና የጤና ሁኔታ መመለስ ያስችላል ተብሏል፡፡

  1. የቀለበት ጣት

ይህ ጣታችን ከሳምባ እና ከትልቁ አንጀታችን ጋር ግንኙነት ያለው ስሜታዊ ሲሆን ከስሜታዊ ባህሪያት ማለትም ሀዘን እና ንዴት ሲያጋጥም በተመሳሳይ ይህን ጣት መጫኝ እና ትንፋሽ ማውሰድ ከመሰል ሲሜታዊ ባህሪያት ሊረጋጋ ይችላል ተብሏል፡፡

የቆዳ ህመም አስም እና የምግብ መፈጨት ችግር ላለበትም እፎይታን ለማግኘት ይረዳል ፡፡

  1. አውራ ጣት

አውራ ጣት ሆድ እና ጣፊያ  ጋር ግንኙነት አለው ፡፡ፍርሃት ፣ ንዴት እና ጭንቀት ለመሰሉ ስሜታዊ ባህሪያት እንዲሁም ከሆድ ህመም ከራስ ምታት እና ከቆዳ ችግር እፎይታን ለማግኘት ይረዳል፡፡

  1. መሃል ጣት

ከየሃሞት ከረጢት እና ከጉበት ጋር ይገናኛል ተብሏል፡፡ ቶሎ ቱግ የማለት ወይም ከፍተኛ ንዴትን ለማረጋጋት ብሎም ከራስ ምታት፣  ከወር አበባ ጋር የሚፈጠር ህመም እንዲሁም ከአይን ህመም ራስን ለማዳን ይጠቅማል ተብሏል፡፡

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close